(ታኅሣሥ 01/2018 ዓ.ም) የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በወቅታዊ፣ ክልላዊ እና ሀገራዊ የሰላም እና የልማት ጉዳዮች ላይ በኮምቦልቻ ከተማ ከወጣቶች ጋር ተወያይተዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎችም ወጣቶችን አሳታፊ ያደረጉ ሥራዎችን በማከናወን ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል ብለዋል። ከተማዋ ሰላም እንድትኾን ወጣቶች ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ማድረጋቸውን በማንሳት በቀጣይም ይህ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በመኾኑም መንግሥት ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የሥራ እድል ፈጠራዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሠራ ጠይቀዋል።
ሥራ አጥነት በመጨመሩ ወጣቶች ወደ ሱስ እየገቡ ይገኛሉ ያሉት ተሳታፊዎቹ የሥራ እድል እና የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታ ማመቻቸት ይገባል ብለዋል።
በልማት ምክንያት የሚነሱ አርሶ አደሮችን በዘላቂነት ለማቋቋም መሥራት እንደሚገባም አመላክተዋል።
ወጣቶች ለሀገር ሰላምም ኾነ ልማት መሰረት በመኾናቸው የሚስተዋሉ የመልካም አሥተዳደር ችግሮች እንዲፈቱላቸው ጠይቀዋል።
በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ፍስሀ ደሳለኝ ኮምቦልቻ ያላትን ጸጋ በመለየት እያከናወነችው ያለው የልማት ሥራ አበረታች መኾኑን ገልጸዋል።
በተለይም በተማሪ ምገባ እና ሰው ተኮር ፕሮጀክት ላይ የታየው ተግባር ተሞክሮ የሚኾን ነው ብለዋል።
የባቡር መንገዱን ጨምሮ በጦርነት ምክንያት ተጀምረው የተቋረጡ ፕሮጀክቶችንም በራስ አቅም ሕዝብን በማስተባበር ለማስቀጠል ጥረት እንደሚደረግ አንስተዋል።
ለዚህ ደግሞ ወጣቶች ሰላሙን አጥብቀው መጠበቅ አለባቸው ነው ያሉት።
በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ ወጣቶች በሀገር ግንባታ ሂደት ያሉ ምቹ ሁኔታዎችን በመጠቀም መሥራት አለባችሁ ብለዋል።
“ከወጣቶች ብዙ ተስፋ አለን” ያሉት አቶ ይርጋ የተከበረውን የአማራ ሕዝብ እሴት በመጠበቅ በጋራ መሥራት እንደሚገባ አመላክተዋል።
የኢትዮጵያ ህልውና በወጣቶች ላይ የተመሰረተ በመኾኑ ወጣቶች ለሀገር አንድነት እና አብሮነት መስዋዕትነት መክፈል አለባችሁ ብለዋል።
በወጣቶች የተነሱ የአገልግሎት አሰጣጥ እና የልማት ጥያቄዎችን በመያዝ በየደረጃው ለመፍታት እንደሚሠራ ገልጸዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጫኑ።
Facebook https://www.facebook.com/share/1ZfJoPFYV7/
Ticktock https://www.tiktok.com/@amhara.region.pre?_r=1…
Telegram https://t.me/ANRS_PresidentOffice
Twitter https://x.com/AmGovernoffice/header_photo
You Tube https://www.youtube.com/@amhararegionpresidentoffic1192
WhatsApp https://whatsapp.com/channel/0029Vb6ZZXk1t90V1p2qyV03

