የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ አመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ የሴክተር ጉባኤ በባሕርዳር ከተማ እየተካሄደ ነዉ።
በጉባኤው ተገኝተዉ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ ዘዉዱ ማለደ እንደገለጹት ዘርፉን ማዘመን ወቅቱ የሚጠይቀዉ ተግባር ነዉ ብለዋል።
የአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪዎች መረጃ በቴክኖሎጂ መመዝገቡን ነው ያነሱት። ህዝብ የሚያገለግሉ የትራንስፖርት አሽከርካሪዎች በማህበር መደራጀታቸውን አንስተዋል።
በአሁኑ ጊዜ ዓለም ላይ እየደረሱ ካሉ አደጋዎች ሁሉ የመንገድ ትራፊክ አደጋ ከቀዳሚዎቹ ተርታ እንደሚመደብ የተናገሩት ኀላፊዉ በሰዉና በንብረት ላይ አያሌ ጉዳቶች መድረሳቸውን ነው የተናገሩት።
የዚህን ችግር ለመሻገርም በዘመናዊ መንገድ የስልጠና ማዕከላትን በቴክኖጅ አስደግፎ ስልጠና እንዲሰጡ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።
ተወዳዳሪ መሆን ያልቻሉና እና ለችግሩ መንስኤ የሚሆኑ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋማት ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑንም ነው የገለፁት።
ትርፍ የሚጭኑ አሽከርካሪዎችን ለመቆጣጠር በኢ-ትኬቲንግ ተግባሩን ለማከናወን እየተሰራ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።
በመድረኩ ተገኝተዉ መልዕክት ያስተላለፉት የማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽፈት ቤት ኀላፊ ክቡር አቶ ይርጋ ሲሳይ እንደገለጹት ክልላችን ባለፉት ሁለት ዓመታት ቀዉስ ገጥሞት መቆየቱን አስታውሰዋል።
በተደረገዉ እልህ አስጨራሽ ትግል ዜጎች በሰላም ወጠዉ ከመግባት ባሻገር የእለት ከእለት ተግባራቸዉን በሰላም እያከናወኑ መሆኑን ነዉ የተናገሩት።
በአሁኑ ሰአትም የክልሉ መንግስት እስከ ቀበሌ ባሉ መዋቅሮቹ በተሟላ ደረጃ መንግሰታዊ ተግባሩን እየፈጸመ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
መንግስት የዜጎችን ጥያቄ መመለስ የሚያስችሉ በርካታ የልማት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል ያሉት ኀላፊው የትራንስፖርት እና ሎጅስቲስ ዘርፍ እንደ ሀገር ትልቅ ትኩረት እንደተሰጠዉ ሁሉ ክልሉም ልዩ ትኩረት ሰጦ እየሰራ መሆኑን ነው የገለፁት።
በዚህም መናኸሪያን በማልማት እና ኢ-ትኬትን በመተግበር በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ነዉ ብለዋል።
በክልሉ ደረቅ ወደቦችን፣ የአዉሮፕላን ማሪፊዎችን በማልማትና በማዘመን አስፈላጊን ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አስተላልፈዋል።
የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ዘርፍ ለሁሉም የኢትዮጵያ ስኬቶች የጀርባ አጥንት ሁኖ እያገለገለ ነው ያሉት ደግሞ ሚኒስትር ክቡር ዓለሙ ስሜ (ዶ.ር) ናቸው።
እንደእርሳቸው ገለፃ ዘርፉ ጉባኤዎችን የሚያካሂደው ስኬቶችን ተከትሎ ነው። በባሕር ዳር የተካሄደው ጉባኤም የስኬታማነቱ ምልክት ጣናነሽ-2 ከጅቡቲ ወደብ ተነስታ ባህርዳር በመድረስ ጠና ላይ ስራዋን እንደጀመረች በማየታችን ነዉ ሲሉ ነው የተናገሩት።
ኢትዮጵያዉያን በጣናነሽ-2 ይመሰላሉ ያሉት ሚኒስቴሩ ጣናነሽ ባለፈችባቸዉ አካባቢዎች ሁሉ የድርሻቸዉን ለተወጡ ምስጋና አቅርበዋል።
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተቋሙን አስፈላጊነት በመረዳት አደረጃጀቱን ወደ ቢሮ ደረጃ በማሳደጉና ትኩረት በመስጠቱ ምስጋናቸውን ሚኒስትሩ ክቡር ዓለሙ ስሜ (ዶ.ር) አቅርበዋል።ክቡር ዓለሙ ስሜ (ዶ.ር)

