11ኛው ጣና ከፍተኛ የሰላም እና የደኅንነት ፎረም በባህርዳር ተጀምሯል።

የአፍሪካ አህጉር ሀገራትን ሁለንተናዊ ቅርርብ እና ትብብር ለማጠናከር ከተቋቋሙት አህጉራዊ የምክክር መድረኮች “ጣና ከፍተኛ የሰላም እና የደኅንነት ፎረም ወይም ጣና ፎረም” አንዱ ነው።

የዘንድሮ 11ኛው ጣና ፎረም “አፍሪካ በተለዋዋጩ ሉላዊ ሥርዓት” በሚል መሪ ሃሳብ በባህርዳር ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

በፎረሙ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣ የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ.ር)፣ የተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት መሪዎች፤ አምባሳደሮች፤ ምሁራንና ተጋባዥ በመድረኩ ተገኝተዋል።

በመድረኩ በአህጉሪቷ ስለሚስተዋሉ የሰላም እና የደኅንነት ስጋቶች ለየሀገራቱ ፖሊሲ አውጭዎች እና መንግሥታት አማራጭ ሃሳቦችን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top