(ጥቅምት 06/2018 ዓ.ም) የአማራ ክልል ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር (ኢንሳ) ጋር በመተባበር 6ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደኅንነት ወር አስመልክቶ የፓናል ውይይት እያካሄደ ነው።
የሳይበር ደኅንነት ወር ” የሳይበር ደኅንነት- ዲጂታል ለኢትዮጵያ መሠረት” በሚል መሪ መልዕክት እየተከበረ ነው።
የአማራ ክልል ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮም ወሩን ምክንያት በማድረግ ነው የፓናል ውይይት ያካሄደው።
በፓናል ውይይቱ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
የፓናል ውይይቱ ዲጂታላይዜሽን፣ ስፓርት ሲቲ እና ሳይበር ደኅንነት ላይ ትኩረት ያደረገ እንደኾነ ተመላክቷል። የቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽንም ታይቷል።
