(ጥቅምት 1/2018 ዓ.ም) 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ሥብሠባውን ያካሄደው የአማራ ክልል መሥተዳድር ምክርቤት የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
መሥተዳድር ምክር ቤቱ ባካሄደው መደበኛ ሥብሠባው የመንግሥት ሠራተኞችን የደመወዝ ስኬል ማሻሻያ ማስፈጸሚያ መመሪያን መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
የመንግሥት ሠራተኞች እና የመንግሥት ተሿሚዎች የቀን ውሎ አበል አፈጻጸም መመሪያ ላይም በመወያየት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
በክልሉ የአሥፈጻሚ አካላት እንደገና ማቋቋሚያ ሥልጣን እና ተግባራት መወሰኛ አዋጅ መሠረት በአዲስ የተደራጁ የሦሥት ተቋማት ሥልጣን፣ ተግባራት እና አደረጃጀት መወሰኛ ረቂቅ ደንቦች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
መሥተዳድር ምክር ቤቱ የቀረቡለትን የክልሉን የኮንስትራክሽን ባለ ሥልጣን፣ የፕላን ኢኒስቲትዩት፣ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ባለሥልጣን ሥልጣን እና ተግባራት መወሰኛ ረቂቅ ደንቦችን መርምሮ በማጽደቅ መደበኛ ስብሰባውን አጠናቋል።
