በቀን 150 ሺህ ኩንታል ስሚንቶ የማምረት አቅም ያለው ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ መስከረም 18 ቀን 2017 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ተመርቆ ሥራ መጀመሩ ይታወሳል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኀላፊዎች በሰሜን ሸዋ እንሳሮ ወረዳ የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ተመልክተዋል።
