(መስከረም 18/2018 ዓ.ም) ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የአማራ ክልል የአንድ ማዕከል አገልግሎትን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።
በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዓለምአንተ አግደው፣ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ 14 ተቋማትን በውስጡ የያዘ ነው። 47 አገልግሎቶችን ይሰጣል። የአንድ ማዕከል አገልገሎቱ ተቋማትን እርስ በእርስ ያስተሳሰረ ነው።
የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኀላፊ ባንቺአምላክ ገብረ ማርያም የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በአጭር ጊዜ በፍጥነት ማጠናቀቅ መቻሉን ገልጸዋል።
የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ ሁሉንም ነገር ያሟላ ቀልጣፋ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተናግረዋል። በሌሎች ከተሞችም መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እንደሚቀጥል አንስተዋል።

