የአማራ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዛሬ ይጀምራል።

(መስከረም 18/2018 ዓ.ም) የአማራ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዛሬ ተመርቆ ሥራ ይጀምራል።

የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ 14 ተቋማትን በውስጡ የያዘ ነው። 47 አገልግሎቶችንም ይሰጣል።

የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ ተቋማትን እርስ በእርስ ያስተሳሰረ ነው።

አገልግሎቱ በሲስተም የተያያዘ ስለኾነ ተግባራትን በፍጥነት እና በጥራት ይሰጣል።

ደንበኞች በፍጥነት ጉዳያቸውን ፈጽመው ወደ መጡበት መመለስ የሚችሉበት ፈጣን እና ቀልጣፋ አሠራርን የያዘም ነውም ተብሏል።

በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ደንበኛ ለነገ የሚባል ቀጠሮ አይሰጠውም። ጉዳዩን በአንድ ቀን እና በአጠረ ጊዜ ጨርሶ ይመለሳል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top