“እናንተ የሰላም ጀግኖች ናችሁ”- ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ

በክልሉ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ የቀድሞ ታጣቂዎች በጎንደር ከተማ በተቋቋመው የተሐድሶ ስልጠና ማዕከል የማስጀመሪያ መርሃግብር እየተካሄደ ነው።

በማስጀመሪያ መርሀግብሩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ በዚህ ወቅት እንዳሉት የፌዴራልም ሆኑ የክልላችን መንግስት ያደረጋቸውን የሰላም ጥሪዎች ተቀብላችሁ የመጣችሁ የቀድሞ ታጣቂዎች እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል።

ሰላም ይሻለናል ጦርነት አዋጪ አይደለም ብላችሁ ቅድሚያ ሰጥታችሁ የመጣችሁ ሁሉ የሰላም ጀግኖች ናችሁ ሲሉ አሞግሰዋቸዋል።

በቀጣይ በቆይታችሁ ያገኛችሁትን እውቀትና ግንዛቤ ተጠቅማችሁ በተለያየ ምክንያት የበደልነውን ህዝብ ለመካስ ልትዘጋጁ ይገባል ብለዋል።

በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይ፣ የብሄራዊ ታህድሶ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራል ደርቤ መኩርያው፣ የአማራ ክልል ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ አማረ ሰጤ፣ የአማራ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ፣ የርዕሰ መስተዳደሩ ልዩ አማካሪ አማኑኤል ፈረደ (ዶክተር) እና የምዕራብ እዝ ምክትል አዛዥ ጄኔራል ዋኘው አለሜን ጨምሮ የዞን አመራሮች እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top