በመንግስት ሰራተኞች አዲሱ የደመዎዝ ጭማሪ አፈጻጸም መመሪያ ላይ ውይይት ተካሄደ
********
የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የመንግስት ሰራተኞች አዲሱ የደመዎዝ ጭማሪ አፈጻጸም መመሪያ ላይ ከክልልና ከተማ አስተዳደር ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ሃላፊዎች ጋር ተወያይቷል፡፡
በውይይት መድረኩ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር መኩሪያ ሃይሌ (ዶ/ር)፣ የክልልና ከተማ አስተዳደር ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ሃላፊዎች እንዲሁም የሚመለከታቸው ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡
የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ የመንግስት ሠራተኞች አዲሱ ደመዎዝ ከተያዘው ጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ማስታወቃቸው ይታወሳል ሲል የዘገበዉ ኤፍ ቢ ሲ ነዉ፡፡