የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተከትሎ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች በሰላማዊ መንገድ በመግባት ላይ ናቸው፤
የአማራ ፋኖ (አፋህድ) ከክልሉ መንግስት ጋር ያደረገውን ስምምነትን ተከትሎ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በኪንፋዝ በገላ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው በርካታ ታጣቂ ኃይሎች በሰላም ገብተዋል።
የኪንፋዝ በገላ ወረዳ ም/ዋና አስተዳዳሪ አቶ የሽወንድም ደሴ እንደተናገሩት፦ እንደ እናንተ ሁሉ ሰላምና ልማት ፈልገዉ የሚመጡ ቀሪ ታጣቂዎች ካሉ በቀጣይም ለመቀበል ዝግጅታችን እንደቀጠለ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው በሰላም የገቡት ታጣቂዎች በበኩላቸው፦ ሰላምና ልማት ናፍቆናል፤ እርስ በእርስ መገዳደልም ሰልችቶናል ከእንግዲህ ከህዝብና ከመንግሥት ጋር ተስማምተን ለመኖር ዝግጁ ነን ማለታቸውን የኪንፋዝ በገላ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመልክታል።

