ጎርጎራ ከታላቁ ጣና ሀይቅ በስተሰሜን አቅጣጫ የምትገኝ ታሪካዊ ከተማ ነች። ጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት በታሪካዊቷ ጎርጎራ ከተማ በድንቅ መልካም ምድር ላይ የተገነባ ግዙፍ ሪዞርት ነው።
ሪዞርቱ “በገበታ ለሐገር ፕሮጀክት” አማካኝነት የአካባቢውን ተፈጥሯዊ ይዘት በጠበቀ መልኩ በ40 ሔክታር መሬት ላይ የተገነባ ነው። የተገነባበት ቦታ ጥቅጥቅ ባለ ደን የተሸፈነ ነው።
የሪዞርቱ ሕንጻዎች ግንባታ የጥንታዊ የፋሲል ግንብ የግንባታ ሒደት በተከተለ መንገድ የተገነቡ ናቸው። ጥንታዊቷን ጎርጎራ ግርማ ሞገስ ያላበሰ ሪዞርት ነው።
ጎርጎራ ኢኮ ሪዞርቱ ሁለት ዘመናዊ ሪስቶራንቶች፣ 102 የደረጃቸውን የጠበቁ የእንግዳ ማረፊያ ክፍሎች፣ ሁለት ቅንጡ የፕሬዚዴንሺያል ሕንጻዎች አሉት።
ፕሬዚዴንሻያልና ፐብሊክ መዋኛ ገንዳዎች፣ ከከፍተኛ ቁጥር እስከ መለስተኛ ተሰብሳቢ የሚያስተናግዱና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመላቸው ሶስት የመሰብሰቢያ አዳራሾች አሉት።
እስከ 5መቶ 50 ተሰብሳቢ በላይ ማስተናገድ የሚችለው ጣና አዳራሽ ዘመናዊ የድምጽና የምስል ተክኖሎጂ የተገጠመለት ሁለገብ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ነው።
በተጨማሪም ዘመናዊ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ ሙሉ ስፖ፣ የብስክሌት እና የእግረኛ መንገዶች፣ የሕጻናት መዝናኛ ስርፍራዎች፣ አንፊ ትያትር፣ የቴንስ መጫዎት ሜዳ፣ ለባንክና ለሌሎች አገልግሎች የሚውሉ ዘመናዊ ሱቆችን ይዟል።
እንዲሁም የፍራፍሬና የአትክልት ልማት ስፍራዎች፣ የእጽዋት መንከባከቢያ፣ ተንሳፋፊ ወደብ፣ የነዳጅ ማደያና በቂ የተሽከርካሪ ማቆሚያና ለሌሎች አገልግሎት መስጫ ተቋማት አሉት።
ሰው ሰራሽ አሽዋማ የባሕር ዳርቻና ለሕጻናት ለታዳጊዎች አገልግሎት የሚሰጥ ጥልቀት የሌለው የውሃ ገንዳ የተዘጋጀለት ነው። ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል ፈጥሯል።
ጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ለአካባቢው የልማት እንቅስቃሴን የሚያሳልጥ ለጎርጎራ ከተማ እና አካባቢው ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻነት የመሆን እድል የፈጠረ ነው፡፡

