(ታሕሳስ 10/2018 ዓ.ም) የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በባሕር ዳር ከተማ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎችን እየጎበኙ ይገኛሉ።
በጉብኝቱ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል፣ የግብርና ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ፣ አምባሳደር ግርማ ብሩ የአምራች ኢንዱስትሪ ብሔራዊ ካውንስል ሰብሳቢ እና ሌሎች የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
ከጎበኟቸው አምራች ኢንዱስትሪዎች መካከል ሙሌ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ አንዱ ነው።
ፋብሪካው የጫጩት መኖ፣ የቄብ ዶሮ መኖ፣ የሥጋ ዶሮ መኖ፣ የእንቁላል ጣይ ዶሮ መኖ፣ የወተት ላም መኖ፣ የማድለቢያ መኖ እና የበግ እና ፍየል መኖ በማምረት ለተጠቃሚዎች ያቀርባል።
በባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር 273 ኢንዱስትሪዎች በማምረት ላይ ይገኛሉ።

