የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት

ኢትዮጵያ ወደ ብልጽግና የምታደርገውን ጉዞ በማፋጠን ከተሞቻችን ከፍተኛ ሚና ናቸው፡፡

በአፋር ክልል ሰመራ – ሎጊያ ሲካሄድ የቆየውና ዛሬ በድምቀት ያጠናቀቅነው 10ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም የከተሞቻችንን የዕድገት ጉዞና ተስፋ በግልፅ ያሳየ ነው።

የመደመር መንግሥት የኢትዮጵያ የሥልጣኔ መሠረት የሆኑትን ከተሞቻችንን የብልጽግና ማሳያዎችና ማዕከላት አድርጎ ይመለከታቸዋል።

በብልጽግና ማዕከልነታቸው የብዝኃ ዘርፍ ኢንዱስትሪ ማበቢያ ቦታዎች ሲሆኑ፣ በብልጽግና ማሳያነታቸው ደግሞ የሁለይተናዊ የዕድገት ጉዟችንና የክትመት ማዘመን ሥራችን ወደ ገጠር እንዲሰፋ መሠረት እየሆኑ ይገኛሉ።

በመዲናችን አዲስ አበባ የጀመርነው ከተሞችን ለብልጽግና ጉዞ የማመቻቸት እንቅስቃሴ ዛሬ ወደ አነስተኛ የገጠር ከተሞች እየደረሰ ነው፡፡ የገጠር ኮሪደር ዋና ዓላማውም ገጠሩን በአስተዳደር፣ በመሠረተ ልማትና በክትመት ሥርዓት በማስተሣሠር ወደ ከተማነት ማሳደግ ነው፡፡

በቀጣይ በከተሞቻችን የመኖሪያ ቤት እጥረትን በተለያዩ አማራጮች ማቃለል፣ ጽዳትና አረንጓዴ ልማትን የሕዝብ ባህል ማድረግ፣ ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊና ታሪካዊ ሀብቶቻችንን ወደ ቱሪዝም ሀብትነት መቀየር፤ ወጣቶችን በእውቀትና ክህሎት ለሥራ ማብቃት ላይ ትኩረት ልንሰጥ ይገባል።

ለፎረሙ ስኬታማነት የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ያደረጋችሁ ሁሉ እና በተለይም የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴርን የአፋር ክልልና የሰመራ-ሎጊያ ሕዝብና አስተዳደርን በድጋሜ ማመስገን እፈልጋለሁ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top