የኢንዱስትሪ ከተማ

ኢኮኖሚያችን ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ለማሸጋገር የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። የዘርፉ ፈጣን እድገት ለሌሎች ዘርፎች እድገት ያለው ሚና ከፍተኛ ነው።

ዘርፉ ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማፋጠንና ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር አይነተኛ ሚና ይጫወታል። ለሀገር እድገትና ለሕዝብ ኑሮ መሻሻል መሠረቱ ልማት ነው። ልማት የሚረጋገጠው ደግሞ በስራ ነው።

የክልሉ መንግሥት የኢንዱስትሪ ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ ከፍተኛ መዋለ ንዋይ በማፍሰስ አስፈላጊ የመሠረተ ልማት ዝርጋታና ቴክኖሎጂ አቅርቦት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎችን እየሰራ ነው።

የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳድር ርዕሰ መዲና የሆነችው ደብረ ብርሃን ከተማ ወደ ኢንዱስትሪ ከተማነት እየተሸጋገረች ነው። ከተማዋ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ለኢንቨስትመንት ተመራጭና የኢንዱስትሪ ልማት ቀጠና ማዕከል እየሆነች ነው።

በከተማዋ በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ አቅም ያላቸው በርካታ ተፅዕኖ ፈጣሪ ባለሐብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ተሰማርተዋል።

በኮንስትራክሽ ግብአት አምራችነት፣ በምግብ ማቀነባበሪያ፣ በብረታብረት፣ በጋርመንትና በሌሎች ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ትልልቅ ኩባንያዎች በቀጠናው ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ምህዋር ላይ ከፍተኛ ሚና በመጫዎት ላይ ይገኛሉ።

ኩባንያዎቹ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል የፈጠሩ ናቸው። በተጨማሪም ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በማስቀረት ለሀገር እደገት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው።

የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፣ ኢኮኖሚያችን ለማሻሻልና በዘላቂነት ከድህነት ለመውጣት ኢንቨስትመንትን መሳብና በዘርፉ የተሰማሩ ኢንቨስተሮችን ማበረታታት ያስፈልጋል።

በክልላችን በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ተዋናኝ የሆኑ ባለሐብቶች በምርት ጥራትና አቅርቦት ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አስፈላጊ ድጋፍ እየተደረገ ነው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top