*******
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አረጋ ከበደ እና በአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይ በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ለመጎብኘት ጎንደር ከተማ ገብተዋል።
የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጎንደር ከተማ ሲደርሱ በከተማ አሰተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘውና ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት በአፄ ቴዎድሮስ አየር ማረፊያ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በቆይታቸው በስራ ላይ የሚገኙ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመጎብኘት ግንባታቸው የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን መርቀው ስራ ያስጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
