Revenue Department

Revenue

 

VISION/ራዕይ

“በ2022 ዘመናዊ የታክስ አስተዳደር ስርዓት ተገንብቶናየከተማ አስተዳደሩኢኮኖሚ ከሚያመነጨው የተመጣጠነ ገቢ ተሰብስቦ ማየት”

MISSION/ተልዕኮ

ብቃት ያለው የሰው ኃይል በማፍራት፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጅ በመጠቀም፣ ፍትሀዊ የታክስ አስተዳደር ስርዓት በመገንባት፣ ታክስን በፈቃደኝነት የመክፈል ባህልን በማዳበር ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ መሰብሰብ::

CORE VALUES/እሴቶች

ሀ. ተገልጋይ ተኮር ምርጥ አገልግሎት መስጠት፣

ቀልጣፋ፣ ውጤታማ፣ ፍትሃዊና ምቹ አገልግሎት በመስጠት ተገልጋዮችን በማገዝ ግልጽነትንና ተጠያቂነትን የሚያጎለብት አሠራር መከተል፣

ለ. ከብልሹ አሠራር የፀዳ የሥራ አካባቢ መፍጠር፣

ተገልጋዮችን በቅንነት በማገልገል በሥራ ላይ ያሉ ሕጐችን ያለአድልዎ በመፈጸም ታማኝና ግልጽ በሆነ መልኩ መተግበር፡፡ ከመንግስትና ከህዝብ ጥቅም ጋር የሚጋጭ የግል ፍላጎትና ጥቅምን አለማስተናገድ ፣ ጉቦንና ማናቸውንም ዓይነት ሙስና ማውገዝ፣ መከላከልና መዋጋት፣ ግብር ከፋዩን በንቃት ማሳተፍ ፣ የግልፅኝነትና የተጠያቂነት አሠራር ማስፈን፣

ሐ. ሙያና ክህሎትን ለተጨባጭ ውጤት መጠቀም /Proffessionalism/፣

ማንኛውንም ተግባር ወደ ከፍተኛ ስኬት በሚያደርስ መልኩ ሙያና ክህሎትን በተላበሰና ቀጣይነት ባለው መሻሻል መፈፃፀም፣

መ. ህግን ማስከበር፣

የሕግ ማስከበር አቅምን በየወቅቱ በማሳደግ መልካም ስነ-ምግባርን በመላበስ ሕገ-ወጥነትን  መከላከል፤ ሕጋዊ የንግድ እንቅስቃሴ የሚያካሂዱትን ማገዝ፣ የግብር ግዴታቸውን በወቅቱና በታማኝነት የሚወጡትን ማበረታታት፣ በሕገ-ወጦችና ግብርን በሚያጭበረብሩና በሚሰውሩ ላይ ያለማመንታትና ለሌሎች አስተማሪ በሆነ መልኩ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ፣

ሠ. በቡድን መሥራት፣

በተቋም፣ በሥራ ሂደት፣ በስራ ቡድን፣ በቡድን እንዲሁም ከአጋር አካላትና ከህብረተሰቡ ጋር ለተቋሙ ዓላማ መሳካት በህብረት፣ በትብብር፣ በመግባባትና በትጋት መሥራት።

ረ. የሴቶችንና የወጣቶችን ተሳትፎ ማረጋገጥ፣

በተቋም ደረጃ የሴቶችንና የወጣቶችን ተሳትፎን ማረጋገጥ፣ የሴቶችና የወጣቶች ጉዳይ ተቋሙ በሚያከናውናቸው ተግባራት ውስጥ ተካተው እንዲፈጸሙ ማስቻል ፣ ብቃታቸውን ማጎልበትና የአመራርና የተጠቃሚነት ደረጃቸውን ማሳደግ፡፡

Our location



Scroll to Top