In View of the Revival of National Unity
By:
Merhatsidk Mekonnen Abayneh
Bahir Dar, January 21 2018
1. >Introduction>
In a country which is, by far, not short of national, regional and international conferences, another glorious symposium of its kind was hosted on the 16 and 17 of January 2018 in the town of Bishoftu, not far from Addis. According to the concept note circulating to the table at the time, the main pre-occupation of this one was to discuss nation-building as a buzz concept first and gradually develop a model that would perhaps suit Ethiopia on an inflated impression that it currently needs to reconfigure itself as an emerging federation on the soil of discord. Setting the stage of the discussion were quite a good number of enlightening presentations from such eminent scholars as Prof. Christopher clapham, from the Center of African Studies, Cambridge University, (U.K), Prof. Fantu Cheru from the University of lieden (the Netherlands), Prof. Zeresenay Alemseged from the University of Chicago (U.S.A Prof. Adebayo Olukoshi from the Institute of Democracy and Electoral Assistance, (IDEA), Prof. Richard Joseph from the Brooking Institution (U.S.A, Prof. Mohamed Salih, from ISS Erasmus University, (the Netherlands) and Dr. Gunter Schroeder, an independent analyst from Germany.
With That tremendous intellectual resource, it was originally anticipated that this high-level conference would conceptualize nation-building in the contemporary era, critically scrutinize into its essential ingredients and subsequently come up with a meaningful instrumentality capable of lifting the country out of its abysmal state of affairs feared to accelerate or hasten its political collapse. Nevertheless, it seems to me that it has ended up without even producing an agreeable formula of what the terms ‘nation’ and ‘nation-building’ themselves constitute from the standpoint of our current domestic predicament.
With the presence of a few senior government officials noticeable, invitees to the symposium were largely drawn from the spectrum of the society such as the academia, opposition political parties, civic and religious groupings, the media and foreign embassies based in Addis as well as the EPRDF war veterans and other prominent personalities far and wide. Definitely, the academic community from the Addis Ababa University appears to have dominated the attendance and spearheaded the discussion in the symposium.
2. >The Issues on the Table>
Following our exposure to a series of presentations, participants of the symposium had, at the initial stage, to desperately grapple with a plethora of crude and complex issues engulfing the entire deliberation, so to speak.
What constitutes a nation as a concept?
3. >What does nation-building mean in the context of state formation?>
Any significant difference between the ideas of nation-building and state-building having due regard to comparative experiences brought about from various regions the world over?
Is nation-building relevant to Ethiopia today? and if so, why?
For the purpose of the symposium, a nation was roughly defined as a collective aspiration of people having ethnic, linguistic, religious and cultural diversities towards the formation of a common state on behalf of all in a single political community to which they belong territorially and psychologically while still preserving their respective identities in tact. Hence, the term is believed to represent an idea or allegiance of an organized community to a preferred authority with a genuine sense of belonging and a shared vision more than a territorial space occupied and controlled by a government of the day imposed in whatever manner.
That said, however, none of the distinguished scholars were able to cite for us a single instance in history in which a viable nation-state was purportedly born out of this kind of smooth and democratic process. More over, almost all of them agreed that nation-building is an evolving and an unfinished business by its very nature, as far as they are concerned.
Regardless of slight variations, both nation-building and state-building were used by the participants almost interchangeably throughout the deliberation. Although comparative experiences vary from one region to another, the Swiss and Scandinivian models sounded high in the discussion. An element of compulsion is always inevitable at the initial stage of state formation conducted anywhere in the world. success in nation-building does, however, lie in the negotiation and conclusion of a social contract aimed at including or holding a multitude of diverse communities desiring to live together and thereby develop a collective ideology with a unifying state apparatus in a continuous interaction for ages.
The process of nation-building historically recorded to have been undergone in the African Continent is inextricably linked with the colonial occupation of its vast territories and the merciless subjugation of its different peoples by sheer force. In the majority of instances, nation-states in present-day Africa are simply the mechanical creations of European colonialism and do suffer real legitimacy when it comes to their territorial incorporation and citizenship identity.
3. 2nd Thought on the Value of the Symposium
Unlike the entire Africa, no doubt that Ethiopia is a nation-state with an age-old political independence that had never been colonized by any foreign power from antiquity. Thus, there were few elements from among the gathering who had a 2nd thought on the substantial value of the symposium from this perspective. Some even remarked behind the podium that Ethiopia is neither South Sudan or Somalia in need of being built afresh as a nation long after it has established political system way back 3,000 years ago.
Towards the conclusion of the symposium, Prof. Ephraim Isaac, a distinguished scholar in Near Eastern Languages and the pioneering Founder of the Afro-American Studies at the Harvard University, (U.S.A), went deep into the history of ancient Ethiopia and called upon the congregation that our longstanding traditional and religious values and norms be seriously taken on board in the reinvigorated consideration and accomplishment of its overall renaissance. Prof. Beyene Petros, Deputy Chair of the Ethiopian Federal Democratic Forum, (Medrek), on his part, earlier reiterated that the pressing need of the country today is for the widening of democratic space as well as submitting for national truce and reconciliation instead of nation-building as proposed on the part of the initiators of the latest symposium
4. >Closing Remarks>
The F.D.R.E’s Constitution of 1995 envisions present-day Ethiopia as a grand political community to be founded on the ‘rule of law’, ‘capable of ensuring lasting peace’, ‘guaranteeing democratic order’ as well as ‘promoting the rapid socio-economic development’ of its inhabitants. Admittedly, there is no such thing as nation-building word by word in the entire text of the constitution. Yet, one is here reminded at best to critically examine such vital phrases in the very preamble of the constitution as ‘mutual interest’, ‘emergence of common outlook’ and ‘common destiny’ which might be well taken to carve out the essential building blocks of the concept in view.
Ironically, the country resembles to be less a nation than those which formally make it up in a rather crude-looking construction from the very start. In other words, it is the So-called ‘nations, nationalities and peoples’ which are declared to have formally constituted Ethiopia as a mother nation of the whole conglomeration. That does not, however, reduce the status of the country to the extent of disqualifying it from continuing to act as a sovereign nation-state duly recognized under international law, as the isolated segment of few participants were trying to suggest in an apparently extreme scenario.
My first-hand impression is that one cannot and should not totally dismiss the value of the proposed nation-building project for Ethiopia provided that it be implemented in an inclusive and democratic process. After all, we have unanimously conceded to the preposition that nation-building is a continuous and an unfinished business in any given political landscape roughly explored by the successive presentations. Nevertheless, the theoretical discourse on the nation-building project ought to be accompanied or complemented with the guiding principles of ‘national reconciliation’ which the country badly needs to also go through in the wake of its pressing challenges at the moment.
5. > >
በስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው መግለጫ ላይ አንዳንድ ነጥቦች (ካለፈው ሳምንት የቀጠለ) ከመርሃጽድቅ መኮንን አባይነህ ባህርዳር፣ ጥር 5 ቀን 2010 ዓ.ም
በዚህ መጣጥፍ የመጀመሪያ ክፍል የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከአታካች ግምገማ በኋላ በግንባሩ አባል ድርጅቶች መካከል ተፈጥሮ ነበር ያለውን የርስበርስ ጥርጣሬና አለመተማመን አስወግዶ ከፍተኛ መግባባትና የሃሳብ አንድነት ላይ እንደደረሰ ድምጹን ከፍ አድርጎ በማሰማት በቅርቡ ያወጣውን የአቋም መግለጫ ተንተርሼ አንዳንድ ነጥቦችን ማንሳቴ ይታወሳል፡፡ በዚያ ክፍል ግንባሩ ግምገማውን ያካሄደበትን አመክንዮ፣ የመግለጫውን አወቃቀርና አንዳንድ ወገኖች በድጋፍም ሆነ በነቀፌታ መልክ የሚያሰሙትን አስተያየት በማጣቀስ ለጊዜው በመረጥኳቸው ጉዳዮች ላይ አተኩሬ የራሴን ትንታኔ ካቀረብኩ በኋላ በማጠቃለያው ላይ በልዩ ትኩረት ተይዘው በኮሚቴው ውሳኔ ተላልፎባቸዋል የተባሉትን 8 (ስምንት) ዋና ዋና ነጥቦች በይደር አቆይቻቸው ነበር፡፡ እነሆ በቃሌ መሰረት እንካችሁ ለማለት ዛሬ ተመልሻለሁ፡፡ 1. >ህግና ስርአትን ስለማስከበርና የህዝብን ደህንነት ስለማስጠበቅ> እንደሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው እምነት የልማትና የዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ እንቅስቃሴዎችን በማጠናከር የህዝቡን የላቀ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከሁሉ አስቀድሞ በሀገሪቱ ውስጥ አስተማማኝ ሰላም ማስፈን ተገቢ ነው፡፡ ግንባሩ ይህንን ያሰመረበት ከሰላም ውጭ የሚካሄድ ልማትም ሆነ የሚዘመር ዴሞክራሲ አለመኖሩን ለማጠየቅ ይመስላል፡፡ ስለሆነም ከፍተኛ አጽንኦት ሰጥቶ ውሳኔ ያሳለፈበት የመጀመሪያው ጉዳይ እርሱ የሚመራው መንግሥት ሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት ያጋጠማትን ሰው-ሰራሽ አደጋ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲቀለብስና ሕዝቡን ወደተረጋጋ ኑሮው እንዲመልስ የሚለው ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ የሕብረተ-ሰቡን ሰላማዊ ኑሮ ክፉኛ የሚያውኩ ማናቸውንም አይነት ህገወጥ እንቅስቃሴዎች መንግስት ከህዝቡ ጋር ሆኖ የመቆጣጠር ሃላፊነት አለበት ሲል ነግሮናል፡፡ በመሰረቱ የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ጉዳይ ላፍታም ቢሆን ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ነገር አይደለም፡፡ በዚህ ረገድ የሚታዩትን የህግ ጥሰቶች መንግሥቱ ተግቶ እንዲቆጣጠርና ሰላምና ደህንነትን በአስተማማኝ ሁኔታ ማስፈን እንደሚገባው ተጠናክሮ መገለጹ ጅብ ከሄደ ውሻጮኸከሚባል በስተቀር የሚነቀፍበት ምክንያት የለውም፡፡ በኔ በኩል ይህ ውሳኔ ራሱን በራሱ የሚገልጽና ፈረንጆቹ (ሰልፍ-ኤክስፕላናቶሪ) የሚሉት አይነት ይመስለኛል፡፡ ለመሆኑ በአንድ ማህበረ-ሰብ ውስጥ በመንግሥት ስም የተደራጀ ተቋም ይህንን ካላከናወነ የማንን ጎፈሬ ሊያበጥር ኖሯል ከዚህ አንጻር ግንባሩ እንደሚለው በያካባቢው የህዝብ መገልገያዎች በሆኑ ተቋማት ላይ የተነጣጠረ ሁከትና ግርግር የሚፈጥሩ ወገኖችን ለይቶ በመከታተልና በመቆጣጠር የህብረተ-ሰቡ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ሳይስተጓጎል መቀጠሉን ለማረጋገጥ ያመች ዘንድ አውራና መጋቢ መንገዶችን በመዝጋት የዜጎችን ከስፍራ ስፍራ የመዘዋወር መብት አለአግባብ የሚያግዱ ህገወጥ የተናጠልና የቡድን እንቅስቃሴዎች መገታት እንዳለባቸው ለመግባባት አያዳግትም፡፡ ሆኖም ይህ በወጉ ሊፈጸም የሚችለው በመንግሥት ብርቱ ፍላጎት ብቻ እንዳልሆነ ከወዲሁ መታወቅ አለበት፡፡ ቀድሞ ነገር በሁከት ፈጣሪነት የሚከሰሱት ግለሰቦችና ቡድኖች ያልተገባ መደበቂያ ዋሻ የሚያደርጉት ሰፊውን ህዝብ ስለሆነ እርምጃው ቢወሰድ ፍሬ የሚኖረው የሰላሙ ተጠቃሚ የሆነውን ምልአተ-ህዝብ ከጎን ማሰለፍ የተቻለ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ ውሳኔው ከዚህ ላቅ ባለ ድምጸት በአንዳንድ አጎራባች ክልሎች ውስጥ በወሰን-ይገባኛልም ሆነ በሌሎች ምክንያቶች ተደጋግሞ እያጋጠመ ያለው የንጹሃን ዜጎች ሞትና የህዝብ መፈናቀል በአስቸኳይ መቆም እንዳለበት ያሳስባል፡፡ ይልቁንም በቅርቡ በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች መካከል ባሉ አዋሳኝ አካባቢዎች ባጋጠሙ ደም አፋሳሽ የርስበርስ ግጭቶች ሳቢያ የተፈጠረው የሰላማዊ ወገኖች ሞትና እንግልት እንዲሁም የመቶ ሺዎች መፈናቀል እልባት አግኝቶ በግጭቱ ሳቢያ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በጊዜያዊ መጠለያ የሚገኙት ዜጎች እንደገና የሚቋቋሙበትና መደበኛ ህይወታቸውን በተረጋጋ መንገድ የሚመሩበት ሁኔታ ባስቸኳይ እንዲመቻችላቸው ያዝዛል፡፡ ወደቀድሞው ቤት-ንብረታቸው ሊመለሱ ይችሉ እንደሆነ ግን ውሳኔው አንዳች ፍንጭ አይሰጥም፡፡ በመጨረሻም እነዚሁ ክልሎች ለገቡበት የርስበርስ ግጭት መንስኤዎች ናቸው የተባሉት ሕገወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎች ሳይቀር በአስቸኳይ ቆመው አርሶና አርብቶ-አደሮች የተሰማሩበት የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለበለጠ አደጋ እንዳይጋለጥ አስፈላጊው ጥበቃና ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ቃል ተገብቷል፡፡ ይሁን እንጂ የኮንትሮባንድ ንግዱ ከአባባሽነት አልፎ የደም አፋሳሽ ግጭቱ አይነተኛ መንስኤ ነው ለማለት በበኩሌ አልደፍርም፡፡ ዜጎች በብሄራዊ ማንነታቸውና በሚናገሩት የአፍ መፍቻ ቋንቋ እየተለዩ በጠራራ ጸሃይ መጠቃታቸው፣ መሳደዳቸውና በሀይል መፈናቀላቸው እየታየ የዚህ መንስኤ የኮንትሮባንድ ንግድ ነው ብሎ ማስተሀቀሩ አጥብቀን የምንመኘውን መፍትሄ በብዙ ማይሎች የራቀና የተወሳሰበ እንዳያደርገው እሰጋለሁ፡፡ 2. >የውስጠ-ድርጅት ዴሞክራሲ> የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውሳኔ ያሳለፈበት ሁለተኛው ነጥብ የአባል ድርጅቶቹን ውስጣዊ ዴሞክራሲ ይመለከታል፡፡ በዚህ ነጥብ ላይ የተላለፈው ውሳኔ ባጭሩ በግንባር ደረጃ ሲካሄድ የቆየውን መሰረታዊ ግምገማ መነሻ በማድረግና የሀገሪቱን የትራንስፎርሜሽን አጀንዳ በውጤታማነት ለማስፈፀም ይቻል ዘንድ እያንዳንዱ ብሔራዊ ድርጅት በከፍተኛ አመራር ደረጃ የሚታይበትን ድክመት በጥልቀት ከመረመረ በኋላ በግልጽነትና በተጠያቂነት ላይ የተመሰረተ የእርምትና የማስተካከያ እርምጃ በሚወስድበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ድግግሞሽ ቢታይበትም እስካሁን ከምናውቀውና ከተለመደው የድርጅቱ ባህል እምብዛም የተለየ አሰራር ባለመሆኑ በዚህ ላይ አቃቂር ለማውጣት አልፈለግሁም፡፡ 3. >የልማት አቅርቦት ሚዛናዊነት> በክልሎች መካከል ከጊዜ ወደጊዜ የልማት ደረጃ ልዩነት እየተፈጠረ መጥቷል የሚለውን ስሞታ እኔም አልፏልፎ እሰማለሁ፡፡ የግንባሩ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በሶስተኛ ውሳኔው የተመለከተው ይህንኑ ነጥብ መሆኑ ታዲያ ስሞታው ስነ-ልቡናዊ ብቻ እንዳልሆነ አረጋግጦልኛል፡፡ በሀገሪቱ የተተከለው ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በህዝቦች መካከል እኩልነትንና ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ መሠረታዊ ጥያቄዎችን አስቀድሞ እንደመለሰ ግንባሩ ያምናል፡፡ ያም ሆኖ ታዲያ እርሱ እንደሚገልጸው ከአፈፃፀም ድክመት ጋር በተያያዘ ከቦታ ቦታ የሚታዩ የልማት አቅርቦት ውጣ-ውረዶች እንደሚታዩ ባካሄደው ግምገማ ሳይቀር አረጋግጦ መውጣቱን ይፋ አድርጓል፡፡ በቅድሚያ እንደቆዳ ስፋታቸው ሁሉ ክልሎቻችን በተፈጥሮ ጸጋቸውም ሆነ በሰው ሀይል ሀብታቸው አንደኛው ከሌላው ጋር ሊለያዩ የመቻላቸውን እውነታ አምኖ መቀበል ተገቢ ነው፡፡ ከዚህ አልፎ በፖሊሲ ደረጃ የተደገፈ እስኪመስል ድረስ አንደኛው ክልል በጥሬ የእርሻ ምርት አቅራቢነት ተወስኖ ሲንከላወስ ሌላኛው ክልል በዘመናዊ ኢንዱስትሪ ውጤቶች አቀነባባሪነት እንዲሰለጥን ሲደረግ በሚታይበት ጊዜ ግን ፉክክሩ የተዛባና ፍትሃዊነት የጎደለው ይሆናል፡፡ የአቋም መግለጫው እንደሚለው በስርዓቱ ውስጥ ያለው ወሳኝ የልማት አቅም በራሳቸው በክልሎች ውስጥ የሚገኘው ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት ክልሎችን የሚያስተዳድሩ ብሄራዊ ድርጅቶች ይህንኑ የየክልሎቻቸውን የልማት አቅም አሟጠው የሚጠቀሙበትን ስልት መቀየስ እንደሚገባቸው ኮሚቴው አስምሮበታል፡፡ በርግጥ በዚህ ብቻ አልተወሰነም፤ በፌደራል መንግሥቱ ደረጃም ቢሆን ይህንን አይነቱን የልማት ደረጃ ልዩነት ቀስ በቀስ የማጥበብና ሃገራዊ አንድነትን ይበልጥ የማጠናከር ፋይዳ ያላቸው ዘርፈ-ብዙ ፕሮጀክቶች በተጨማሪ እየታቀዱ መከናወን እንደሚገባቸው ተገቢውን አቅጣጫ እንደሰጠ አስተውያለሁ፡፡ እንግዲህ ገቢራዊነቱን በቅርብ እየተከታተሉ ወደፊት መወቃቀስ ሳይሻል አይቀርም፡፡ 4. >የማሻሻያ ፕሮግራሞች ክለሳና አተገባበር> በኔ አስተያየት ኢህአዴግ ነጋ-ጠባ የሚወተውተውን ያህል ተሳክቶለት የማያውቀው የመንግሥታዊ ብቃትና ውጤታማነት ጉዳይ ነው ብል የተሳሳትኩ አይመስለኝም፡፡ ሰፊውን ጊዜ የሚያባክነውና መላ ጉልበቱን የሚያፈሰው በማሻሻያ ፕሮግራሞች ቀረጻና ክለሳ ስም ገደብ-የለሽና አንዳንዴም አስቀድመው ያልታቀዱ አታካች ስብሰባዎችን በማካሄድ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ሌላው ቀርቶ የፖለቲካ ድርጅቱ ስብሰባዎች እንኳ የሚካሄዱት በመንግሥት የስራ ሰአት እንደሆነ እንታዘባለን፡፡ ከዚህ አንጻር ይህ ደካማና ከአገልግሎት ሰጪነት ይልቅ በስብሰባ አዳኝነት ተጠምዶ የምናየው መንግሥታዊ ቢሮክራሲ ለህዝብ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ የመስጠት አቅምና ቁመና እንዲኖረው ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው; የተጀመሩትን የሪፎርም ፕሮግራሞች ውጤታማ ለማድረግና መስተካከል ያለባቸው አቅጣጫዎች ቢኖሩ ከህዝቡና ከፈፃሚ አካላት ጋር በመተባበር እንደገና ተከልሰው ወደሙሉ ትግበራ እንዲገቡ ይደረጋል መባሉስ በተጨባጭ ምን ይጨምርልን ይሆን; በዚህ አጋጣሚ በፌደራልም ሆነ በክልል ደረጃ ተዋቅሮ የምናገኘው ሲቪል ሰርቪስ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ የአገልጋይነት መንፈስ ተላብሶ የሕዝቡን አንገብጋቢ ጥያቄዎች በወቅቱ ለመመለስ ተግቶ እንዲረባረብ በመግለጫው አማካኝነት ጥሪ ቀርቦለታል፡፡ 5. >የህዝብን አመኔታ መልሶ ማግኘትና ቅሬታዎቹ የሚደመጡበትን እድል ማስፋት> ኢህአዴግ በዚህኛው ውሳኔው እመራዋለሁ ከሚለው ህዝብ ጋር የተካረረ ግጭት ውስጥ እንደገባና ታማኝነቱ ክፉኛ እየተሸረሸረ እንደመጣ የተቀበለው ይመስላል፡፡ እንዲያውም ከአሁን በኋላ ህዝቡ ለሚያነሳቸው አንገብጋቢ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት መጣር እንደሚገባው መረዳቱን በአደባባይ ሲያውጅ ተሰምቷል፡፡ ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ ይመስላል፣ ሕዝብ በየደረጃው የሚደመጥበትንና ወሳኝነቱ በሚገባ የሚረጋገጥበትን እድል ይበልጥ ለማስፋትና በተለይም የያካባቢው ወጣቶች አዘውትረው የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች ለመመለስና በልማትም ሆነ በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ረገድ ሊኖራቸው የሚገባውን ንቁ ተሣትፎ በተሟላ ሁኔታ ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት እንዲከናወኑ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡ በርግጥ በአንድ ወቅት የታጣን የህዝብ አመኔታ ቀድሞ በነበረበት ሁኔታ መልሶ መቀዳጀቱ የተመኙትን ያህል ቀላል ላይሆን ይችላል፡፡ ያም ሆኖ የፈሰሰ ውሃን ከማፈስ እንደማይከብድ አውቀው መግለጫው በተሰማበት ሰሞን በመጠኑም ቢሆን ልባቸውን ከፍተው ያዳመጡትና ቃል ኪዳኑን ከተስፋ ጋር የተቀበሉት ወገኖች አልታጡም፡፡ ስለሆነም ግንባሩ ሳል ይዞ ስርቆት ቂም ይዞ ጸሎት እንዳይሆንበት ውሳኔውን እውን ለማድረግ እንደወትሮው የምልአተ-ህዝቡን ልብ ለመማረክ ከፈለገ በየጊዜው ሱባኤ መግባቱን ቀነስ አድርጎ በጸጸቱ ልክ ተጨባጭና ተከታታይ እርምጃዎችን መውሰድ ይኖርበታል፡፡ ከቃላት በላይ የሚናገረው ተግባር ነውና፡፡ 6. >የመድበለ-ፓርቲ ስርአት ግንባታ> የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ-መንግሥት ለፖለቲካ ብዝሃነትና ለመድበለ-ፓርቲ ስርአት ተገቢውን እውቅና ይሰጣል፡፡ ይሁን እንጂ ህገ-መንግሥቱ ከታወጀበት ጊዜ አንስቶ በዚህ ዘርፍ ያለው እንቅስቃሴ በግርድፉ ሲዳሰስ ያን ያህል አበረታች አልነበረም፣ አይደለምም፡፡ አሉ የሚባሉት ተቀናቃኝ የፖለቲካ ድርጅቶች አማራጭ ፕሮግራሞቻቸውን ለህዝብ እያቀረቡ እንዲያው ለወጉ ያህል በምርጫ የመሳተፍና ለመመረጥ የመወዳደር መብት ባይነፈጋቸውም እስከዛሬ ድረስ ለአምስት ተከታታይ ዙሮች በተካሄዱት ሀገር-አቀፍ ምርጫዎች በሰፊ ርቀት እያሸነፈ መንግስታዊ ስልጣኑን በብቸኝነት ተቆጣጥሮ ከቆየው ግንባር ጋር ያላቸው ግንኙነት ፍጹም የሻከረና ሰላማዊ ድባብ የማይታይበት ነው፡፡ ስለሆነም ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ከረዥም ጊዜ በኋላ ይህንኑ ሀቅ አምኖ በመቀበል ከሁሉም ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችና ከህዝቡ ጋር ተባብሮ በመድበለ-ፓርቲ ስርአት ግንባታው ውስጥ የሚታዩትን ህጸጾች ለማረም መወሰኑ አበጀህና ግፋበት የሚያሰኘው ነው እላለሁ፡፡ ከዚህ አልፎ ምሁራንና የሲቪክ ማህበረ-ሰቡ አባላት የዴሞክራሲውን ምህዳር ለማስፋት በሚደረገው ጥረት ተገቢ ሚናቸውን ለመጫወት የሚችሉበት ምቹ ሁኔታ ይፈጠር ዘንድ ተግቶ ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት እስከመግለጽ ደርሷል፡፡ ይህ ማለት እንግዲህ የፖለቲካ ሜዳውን ለፖለቲካ ስልጣን ተወዳዳሪዎች ብቻ ሳይሆን በሀገራችን ጉዳይ እኛንም ያገባናል ለሚሉ ወገኖች ሁሉ ሳይሰስቱ ክፍትና ተደራሽ በማድረግ የተለያዩ አስተያየቶችን ያለአድልዎ ማስተናገድ መሆኑ ነው፡፡ የሀቀኛ ዴሞክራሲ ትሩፋቱም ከዚህ ውጭ የሚታሰብ አይሆንም፡፡ 7. >የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ከበሬታ> የዜጎችና የህዝቦች መሰረታዊ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችና ነጻነቶች ተፈጥሯዊነትና አይገሰሴነት በህገ-መንግሥቱ አንቀጽ 10 ስር ተረጋግጧል፡፡ ዝርዝራቸው በምእራፍ ሶስት (3) ስር የሰፈረው እነዚህ መሰረታዊ መብቶችና ነጻነቶች ለህዝብ ጥቅምና ለሀገራዊ ደህንነት ሲባል ራሱ ህገ-መንግሥቱ አስቀድሞ ከሚደነግገውና ይህንኑ ገቢራዊ ለማድረግ የወጣ ወይም ወደፊት የሚወጣ ህግ በግልጽ ከሚፈቅደው ስነ-ስርአት ውጭ በሆነ ማናቸውም አይነት እርምጃ ሊገደቡ አይችሉም፡፡ የግንባሩ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያወጣው የአቋም መግለጫ በዚህ ጉዳይ ላይ ሠጠሁት የሚለው ውሳኔ ግልጽነት የጎደለውና አሻሚነት የሚታይበት ነው፡፡ ለመሆኑ በሀገሪቱ ውስጥ በሰብአዊ መብቶች ጥሰት ረገድ የሚታዩትን አዝማሚያዎችና ተግባራት እመክታለሁ ወይም እከላከላለሁ ማለት በተጨባጭ ምን ማለት ነው; በርግጥ የህዝቡን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በአስተማማኝ ደረጃ ለማስከበር ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው ተጨማሪ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ በውሳኔው ላይ ተጠቅሷል፡፡ ለኔ ግን ይህ ሁሉ ከቃላት ጨዋታ የዘለለ አይደለም፤ ልባዊ ቁርጠኝነትንም ያመለክታል ብዬ አላምንም፡፡ እንዲያውም ኮሚቴው ያለው ሊባል ከሚገባው በጅጉ ያነሰ መስሎ ይሰማኛል፡፡ ለወደፊቱ የሚያጋጥሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ግንባሩ እንደሚለው አጥብቆ መመከት ወይም መከላከል ተገቢነቱ አያጠያይቅም፡፡ ይበልጥ የሚታመነው ግን በአሁኑ ወቅት በተጨባጭ ይታያሉ ያላቸው ጥሰቶች በወጉ እንዲመረመሩና ተጠያቂዎች ሆነው የተገኙት ወገኖች ለፍርድ እንዲቀርቡ ቢያደርግ እንደሆነ ለመምከር እወዳለሁ፡፡ 8. >የመገናኛ-ብዙሃን ሚና> ይህኛውን የውሳኔ ነጥብ አስመልክቶ በክፍል አንድ (1) ላይ ብዙ ሳላወራ የቀረሁ አይመስለኝምና በዚህ ክፍል ላይ ትንሽእቆጠባለሁ፡፡ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የመጨረሻ ባደረገው በዚህ ነጥብ ሁለንተናዊ ልማትን በማበረታታትና ሃገራዊ አንድነትን በማጠናከር ዙሪያ ተግተው መስራት ሲገባቸው ሕዝብን ከህዝብ ጋር በሚያራርቅ አሉታዊ ተግባር ተጠምደው ይታያሉ ያላቸው አንዳንድ የግልና የመንግሥት ሚዲያ ተቋማት ይህንኑ የተሳሳተ ቅኝታቸውን የሚያስተካክሉበትን ሁኔታ ለመፍጠር እንደሚንቀሳቀስ አስታውቋል፡፡ ኮሚቴው በአንክሮ እንደገለጸው ከሆነ በፌደራልም ይሁን በክልሎች ደረጃ በህዝብ መገናኛ-ብዙሃን አማካኝነት ከሕጋዊ አሠራር ባፈነገጠ አካሄድ የሁከትና የግርግር መልእክቶች ይሰራጫሉ፣ ይሰበካሉ፡፡ ስለሆነም ይህንን አፍራሽ እንቅስቃሴ ለመቀልበስ የሚያስችሉና የተቀናጁ እርምጃዎች በመንግሥት እንደሚወሰዱ ከወዲሁ አስጠንቅቋል፡፡ በግልም ይተዳደሩ በመንግሥት የመገናኛ-ብዙሃን ተልእኮና የስምሪት መስክ ቀድሞ ነገር የሚወሰነው በየተቋቋሙበት ቻርተርና በየተቀረጸላቸው ዝርዝር የኤዲቶሪያል ፖሊሲ አማካኝነት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከዚህ በተለየ ድርጅታዊ መግለጫ አማካኝነት ከፍላጎታቸው ውጭ የስምሪት መስካቸውን እንዲያስተካክሉ ማስገደዱ እምብዛም አያዋጣም፡፡
ከመካከላቸው የሚዲያ ህግ በግልጽ የሚከለክለውን የፈጸሙ መኖራቸው ከተረጋገጠ ደግሞ ጉዳዩን በተናጠል አጣርቶ ተገቢውን የእርምት እርምጃ መውሰድ የአባት ነው፡፡ ከዚህ አልፎ በዘገባችሁ ውስጥ ያኛውን ትታችሁ በዚህኛው ላይ አተኩሩ እያሉ አጠቃላይነት ባለው አነጋገር ገና ብቅ ብቅ በማለት ላይ የሚገኙትን ለጋ ተቋማት እስከማስፈራራት መዝለቁ ግን የሀገሪቱ ህገ-መንግሥት በአንቀጽ 29 ንኡስ አንቀጽ (3) ሀ. ስር በበር የከለከለውን ቅድመ-ምርመራ በጓሮ መመለስ እንዳይመስል ብርቱ ጥንቃቄ የሚያሻው ጉዳይ ነው፡፡ በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው መግለጫ ላይ አንዳንድ ነጥቦች ከመርሐፅድቅ መኮንን አባይነህ ባህርዳር፣ ጥር 1 ቀን 2010 ዓ.ም
1. >መግቢያ > አራቱን ብሄራዊ ድርጅቶች በማጣመር የተዋቀረው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ድፍን 17 ቀናትን እንደፈጀ በተነገረለት ታሪካዊ ስብሰባው ማግስት ዘርፈ-ብዙ ጉዳዮችን የዳሰሰ አንድ ሰሞናዊ መግለጫ አውጥቷል መግለጫው ትኩስና በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች አማካኝነት በቅብብሎሽ ላይ ያለ በመሆኑ ለብዙ አንባቢያን አዲስ እንደማይሆንባቸው ከወዲሁ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ይልቁንም ከመታወቅ አልፎ ሀገራችን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ለገባችባቸው አደገኛና ውስብስብ ችግሮች ዓይነተኛ መፍትሄዎችን አንግቦ መጥቷል ከሚሉት የዋሃን አንስቶ ከወትሮው የተለየ አንዳች ቁምነገር አለያዘምና በከንቱ አትድከሙ እያሉ እስከሚያሟርቱት የፍፁም ቀቢጸ-ተስፋ ሰለባዎች ድረስ ከቀደምት የግንባሩ መግለጫዎች በተሻለ ሁኔታ የብዙዎችን ትኩረት እንደሳበ ተረድቻለሁ፡፡ 2. >በአስተያየቶች ላይ የኔ አስተያየት > ግንባሩ ከሰማይ በታች ያሉ ጉዳዮችን ሁሉ ያለገደብ እንዳነሳና ከመቸውም ጊዜ ይልቅ በግልጽነት ሲከራከርባቸው እንደሰነበተ ሊቀ-መንበሩ ራሳቸው በቴሌቪዥን ሲናገሩ ሰምቻለሁ፡፡ ያም ሆኖ የትኛውም ድርጅታዊ መግለጫ የአንድን ታላቅ ሀገርና ህዝብ መላ ችግሮች ጨርሶ እንደሚፈታ መመኘት ይቅርና ከመነሻው ማሰቡ ራሱ አመክኒዮ የጎደለው አስተያየት ከመሆን ከቶ ሊዘል አይችልም፡፡ በመሰረቱ ሀገራችንን ክፉኛ እየተፈታተነ ያለው ፖለቲካዊ ቀውስ በስልጣን ላይ ያለም ቢሆን ከአንድ የፖለቲካ ድርጅት የአቋም መግለጫ አቅም ያለፈ መሆኑን በተገቢው መንገድ ማጤን ይገባል፡፡ መላው ህዝባችን መግለጫውን ሊረዳውና ሊገመግመው የሚገባው የሁሉንም ባለድርሻዎች ገደብ የለሽ ተሳትፎ በሚጠይቀው ዘርፈ-ብዙ ጥረት ማእቀፍና አውድ ውስጥ ሆኖና በችግሩ አፈታት ረገድም የራሱን ቀና ተባባሪነት ጭምር ግምት ውስጥ አስገብቶ መሆን ይኖርበታል፡፡ በርግጥ ኢህአዴግ ለጊዜውም ቢሆን በመንግስት ስልጣን ላይ ያለ አንድ ወሳኝ ሀይል መሆኑን አስምሮ መነሳት አስፈላጊ ነው፡፡ ነገር ግን የሀገራችን ችግሮች ሁሉ አልፋና ኦሜጋ ሊሆን አይችልም መግለጫውም ያንን ታሳቢ አድርጎ የተቀረፀና የወጣ ነው ብዬ አላምንም፡፡ ቢያንስ ጥሪውን በቀጥታ ያስተላለፈው ለራሱ ለድርጅቱ አባላትና ለህዝቡ እንደሆነ ከአንዳንድ የመግለጫው መንደርደሪያ ወይም መዝጊያ አረፍተ-ነገሮች ለመገንዘብ ችያለሁ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ መግለጫው ለጥቅስ የሚበቃ አንዳች ቁምነገር የሌለበት ባዶ ቱሪናፋ ብቻ ነው የሚሉት ጽንፈኞች ተቃራኒውን ማየት ይበጃቸዋል እላለሁ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ እግዜርን የሚያካክሉ 36 (ሰላሳ ስድስት) ወንድና ሴት መሪዎች (በርግጥ አብዛኞቹ ወንዶች ናቸው)፣ ለአስራ ሰባት ቀናት ያህል በአት ዘግተውና ሱባኤ ተቀምጠው ለያውም ድምፅ የመስጠት መብት በሌላቸው ነባርና አንጋፋ የግንባሩ አበው ታጋዮቻቸው ምክር ጭምር እየታገዙ እልህ አስጨራሽ ውይይትና የጦፈ ክርክር ሲያካሂዱ ከሰነበቱ በኋላ በመካከላችን ይታዩ ነበር ያሏቸውን የርስበርስ ጥርጣሬዎች አስወግደን መተማመንና የሃሳብ አንድነት ላይ ደርሰናል በማለት ያረቀቁትና ለህዝባቸው ይፋ ያደረጉት ይህ የአቋም መግለጫና ውሳኔ አንዳች አይነት በጎ ነገር የሌለውና በእንቶ-ፈንቶ ጉዳዮች የታጨቀ ማዘናጊያ ብቻ ነው ብሎ መደምደሙ ጤናማነት አይመስለኝም፡፡ ይነስም ይብዛም መግለጫው በዝርዝር ሲታይ ከቀዳሚ የግንባሩ መግለጫዎች ሁሉ በተሻለ አንዳንድ ቁምነገሮችን እናገኝበታለን፡፡ እርግጥ ነው፣ እነዚህ ውስን ቁምነገሮች ከነጻ መሬት ጉባኤዎች ወዲህ ታይቶ በማይታወቅ የተራዘመ ስብሰባ ምክንያት ከባከነው ጊዜ አንፃር የባለዋጋነታቸው ደረጃ ሊያነጋግር እንደሚችል እኔም አምናለሁ፡፡
3. >የመግለጫው አወቃቀር> በዚህ የአቋም መግለጫው ኢህአዴግ እንደአንድ መሪ የለውጥ ሀይል መንግስታዊ ስልጣን ከጨበጠበት ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ ከምልአተ-ህዝቡ ጋር ባካሄደው ርብርብ ሀገሪቱን በኢኮኖሚ ረገድ ከነበረችበት የማሽቆልቆል ጉዞዋ በመግታት ወደሚያስጎመጅ የእድገት ደረጃ ለማሸጋገር እንደቻለ አጠንክሮ በማወጅ ተንደርድሯል ይህ መቸም ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ ነውና ያልተለመደ ነገር መስሎ ጎራ በመለየት እንዳዲስ ባያጨቃጭቀን እመርጣለሁ፡፡ በርግጥ የቋንቋ አጠቃቀም ነገሮችን ሊያኮስስ ወይም ሊያወፍር ይችላል፡፡ የትኛውም ወገን ቢሆን ማስተባበል የማይችለው ግን በተለይ በመሰረተ-ልማት ዝርጋታና በማህበራዊ አገልግሎት ዘርፎች ረገድ እንደተባለው ላለፉት አመታት በሀገሪቱ ውስጥ ቀላል የማይባሉ እመርታዎች መመዝገባቸውን ነው፡፡ በሁሉም ማእዘናት አውራና መጋቢ መንገዶች ተዘርግተዋል፤ ትምህርት ቤቶች ተከፍተዋል፤ የጤና አገልግሎት መስጫ ድርጅቶች ተስፋፍተዋል…፡፡ በኔ አስተያየት ለዚህ እውነታ የአለም ባንክና የአለማቀፍ ገንዘብ ድርጅትን የመሳሰሉት የውጭ ተቋማት ምስክርነት እምብዛም አያስፈልገንም፡፡ ይሁን እንጂ ግንባሩ እንደሌላው ጊዜ ከፍ ብሎ የተጠቀሰውን የዘልማድ መወድስ ተቀኝቶ ብቻ ከመድረኩ አልወረደም፡፡ በአቋም መግለጫው አነጋገር ከፍተኛ አመራሩ በፈጸማቸው ስህተቶችና እድገቱ በፈጠራቸው አዳዲስ ፍላጎቶች ሳቢያ ጊዜያዊና በቀላሉ ሊታለፉ የሚችሉ ናቸው ብሎ ሊያሳንሳቸው ቢዳዳውም ሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት ከባድ ፈተናዎች እንደተደቀኑባት ያለማወላወል በአደባባይ አምኗል፡፡ መግለጫው ከዚህ በኋላ አከታትሎ ያሰፈራቸው ቅድመ-ውሳኔ ሃተታዎች በ23 ረዣዥም ፓራግራፎች ተከፋፍለው መቀነባበራቸውን ተመልክቻለሁ፡፡ በሁሉም ላይ የሚሰማኝን አስፋፍቼ ብጽፍ ምንኛ በወደድኩ ነበር፡፡ ሆኖም ይህንን ላድርግ ብል የናንተን ብቻ ሳይሆን የኔንም ወርቃማ ጊዜ ክፉኛ ይሻማብኛል ብዬ ፈራሁና ለአሁኑ በጥቂት የተመረጡ ነጥቦች ላይ ብቻ ማተኮርን ፈለግሁ፡፡ ከዚህ የተነሳ በአባል ድርጅቶች መካከል መርህ-አልባ ግንኙነትና ያልተገባ ነው በተባለው ቡድናዊ ትስስር፣ በመድበለ-ፓርቲ ስርዓት ግንባታና በፖለቲካ ብዝሀነት፣ በብሄራዊ ማንነትና በሀገራዊ አንድነት ሚዛን አጠባበቅ እንዲሁም በሚዲያ ተቋማት ክትትልና ቁጥጥር ላይ መግለጫው በተለይ አተኩሮ ያካሄዳቸውን ግምገማዎችና ደረስኩባቸው ያላቸውን ማጠቃለያዎች ለመመርመር እሞክራለሁ፡፡ ለዛሬው ባይደርስልኝም ግንባሩ ድህረ-ግምገማ ያሳለፋቸውን ባለስምንት ነጥብ ውሳኔዎች በመጨረሻ እተችባቸዋለሁ፡፡ 3.1 መርሕ-አልባ ግንኙነት ግንባሩ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአንዳንድ ብሄራዊ ድርጅቶች መካከል በመርህ ላይ ያልተመሰረቱ ናቸው ያላቸውን ግንኙነቶችና ቡድናዊ ትስስሮች እንዳሸተተ ያቋም መግለጫው በስምንተኛው ፓራግራፍ ላይ በዝርዝር አውስቷል፡፡ በበኩሌ ይህ ግምገማ ሰፊ ማብራሪያን የሚጠይቅና ለትርጉም ተጋላጭ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ ይህንን ያልተገራ አባባል አንዳንዶች በቅርቡ ሲካሄዱ በነበሩት የፓርቲ-ለፓርቲ ብቻ ሳይሆን የህዝብ-ለህዝብ ግንኙነቶች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ነው ሲሉ በጀሮየ ሰምቻለሁ፡፡ ለምሳሌ በ2008ና 2009 ዓ.ም ተከስቶ የነበረውን ህዝባዊ ሁከትና አለመረጋጋት ተከትሎ መጀመሪያ መቀሌ ለዳግመኛ ጊዜ ደግሞ ጎንደር ላይ በትግራይና በአማራ ክልል መንግስታት አመራሮችና በተመረጡ ጉባኤተኞች መካከል የርስበርስ ግንኙነቶችና ምክክሮች ተካሂደው ነበር፡፡ በመቀጠል ደግሞ ከዚያ ሰፋ ባለ ዝግጅትና አደረጃጀት የአማራና የኦሮሞ ህዝቦች ባህርዳር ከተማ ላይ ደማቅና የተዋጣለት ነው የተባለለትን የጋራ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ ማካሄዳቸው እውነት ሲሆን በተመሳሳይ መንገድ የቤኒሻንጉል-ጉምዝ ተወካዮችና የኦሮሚያ አቻዎቻቸው አዳማ ከተማ ላይ ተገናኝተው በጋራ ጉዳዮቻቸው ላይ መምከራቸውና መዝከራቸው ይታወሳል፡፡ በኔ በኩል የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እንዲህ ያሉትን የህዝብ-ለህዝብ የምክክር መድረኮች መርሕ-አልባ ግንኙነቶች ነበሩ ሲል የፈረጀ ስለመሆኑ ከመግለጫው ውስጥ ፈልቅቄ ለማውጣትና ለመረዳት ፈፅሞ አልተቻለኝም፡፡ አያደርገውም እንጂ እንዲያ ብሎ ሊፈርጅ ከሞከረም ፍፁም ስህተት ይሆንበታል፡፡ ኢህአዴግ እነዚህንና እነዚህን የመሳሰሉትን ሰፋፊ የምክክር መድረኮች ሊያበረታታ እንጂ ሊነቅፍ የሚችልበት አንዳች ምክንያት ይኖረዋል ብዬ ለመገመት አልደፍርም፡፡ እንዲያውም በአንድ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ሳይቀሩ ከፍ ብሎ የተጠቀሱት የህዝብ-ለህዝብ ግንኙነቶች እኛ አስቀድመን ሳናውቃቸው የተከናወኑ አልነበሩም ብለው ሲናገሩ ማድመጤን አስታውሳለሁ፡፡ መሰል ግንኙነቶች ለወደፊቱ እንደሚቀጥሉም ፍንጭ ሰጥተው እንደነበር ትዝ ይለኛል፡፡ ከዚህ ይልቅ ግንባሩ መርህ-አልባ ግንኙነት የሚለው ምናልባት የአንዱ ተጣማሪ ድርጅት ክፋይ ሀይል ከሌላኛው ድርጅት አንጃ ጋር በምስጢር የሚያደርጋቸውና በጠባብ ፍላጎቶችና ጥቅሞች ላይ ይበልጥ አተኩረው ግንባሩ የሚመራበትን ጥብቅ የማዕከላዊነት አሰራር ሳይከተሉ በሹልክታ የሚካሄዱትን ግንኙነቶች ሊሆን እንደሚችል እጠረጥራለሁ፡፡ ከዚህ ውጭ በጠራ አደባባይ የሚካሄደውን፣ ፀሀይ የሞቀውንና ሃገር ያወቀውን የህዝብ-ለህዝብ ግንኙነት አበጃችሁ፣ ደግ አደረጋችሁ፣ ይልመድባችሁ፣ ከማለት በስተቀር በተባለው ደረጃ ሊኮንን የሚችልበት ምክንያት ፈፅሞ አይታየኝም፡፡ ሁላችንም በዚህ መልክ እንድናስብ አበረታታለሁ፡፡ 3.2. የመድበለ-ፓርቲ ስርዓት ግንባታና የፖለቲካ ብዝሃነት የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሀገሪቱ ህገ- መንግሥት በሚፈቅደው ልክ የመድበለ-ፓርቲ ስርዓት ግንባታውን ለማጠናከር እስካሁን ከልቡ ተግቶ እንዳልሰራ ያለማወላወል ማመኑ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ በዚህ ረገድ ተቀናቃኝ ወይም ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለችግሩ የየራሳቸውን ድርሻ መውሰድ እንዳለባቸው ቢታመንም ላለፉት 26 ዓመታት ሀገራዊ፣ ክልላዊና የአካባቢ ምርጫዎች በተካሄዱ ቁጥር በአውራ ፓርቲነት የሚታይ አንድ ጥምር ግንባር ብቻ ከ99 እስከ100 ፐርሰንት የየምክር ቤቶችን መላ መቀመጫዎች እየተቆጣጠረ መቆየቱ አስተዛዛቢ ነው፡፡ ስለሆነም ህገ-መንግሥታዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት በሰፈነበት በየትኛውም ማህበረ-ሰብ ዘንድ ቅቡልነት የሌለውን ይህንን ዓይነቱን የተዛባ አሰራር ቀስ በቀስ ለማሻሻልና ለማረም ደፍሮ ቃል መግባቱ ራሱ ከፍተኛ ሞገስ ሊቸረው ይገባል እላለሁ፡፡ ሁሉም ነገር ራስን ከማወቅና እውነታውን በቅንነት ከመረዳት ይጀምራል፡፡ ስለሆነም የፖለቲካ ድባቡ ለተቃዋሚ ወገኖች ክፍት እንደሚደረግና በህዝብ ምርጫ ለሚደረገው የመንግሥት ስልጣን አያያዝ እስከዛሬ ድረስ ከሚታየው የተሻለ የመጫወቻ ሜዳ በእውነት ሊፈጠር እንደሚችል የተሰጠው የተስፋ ቃል ወደገቢር እንዲለወጥ ተጨማሪ ሰላማዊ ትግል ከማካሄድ ታቅቦ ባዶ ፕሮፓጋንዳ ብቻ እንደሆነ ዘወትር ማዜሙ የለውጥ ፍላጎታችንንም ቢሆን አንድ ስንዝር እንኳ ወደፊት ፈቀቅ አያደርገውም፡፡ 3.3 ብሄራዊ ማንነትና ሀገራዊ አንድነት የኢህአዴግ የፖለቲካ ፍልስፍና የሚጀምረው ኢትዮጵያ የብዙ ብሄሮች፣ ብሄረ-ሰቦችና ህዝቦች መኖሪያ የሆነች ሀገር ናትና በቅድሚያ የነዚህን ብሄሮች፣ ብሄረ-ሰቦችና ህዝቦች ማንነት ከማወቅና በየሰፈሩባቸው አካባቢዎች የውስጥ አስተዳደር ከመትከል ባለፈ አስፈላጊ ሆኖ ቢያገኙት ከህብረቱ ተነጥለው በመውጣት የየራሳቸውን ሉአላዊ መንግሥታት የመመስረት መብት ያላቸው መሆኑን አጽንኦት ሰጥቶ ከማረጋገጥ ነው፡፡ ይልቁንም በኢህአዴግ እምነት እነዚህ ወገኖች ማንነታቸው በቅድሚያ ካልታወቀና ነፃ ህልውናቸው ወይም ሉአላዊነታቸው ካልተረጋገጠ በስተቀር ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር የለችም፣ አትኖርምም፡፡ ይህ የግንባሩ ፍልስፍና የማይዋጥላቸው ወገኖች በበኩላቸው ኢትዮጵያ በዋነኝነት የዜጎቿ እንጂ የብሄር-ብሄረ-ሰቦቿ ሀገር ናት ብለው አያምኑም በመሰረቱ ብሄር-ብሄረ-ሰቦችና ህዝቦች የሚለው ሀረግ የራሳቸው የዜጎች ስብስብ የሆነ ቡድናዊ መገለጫ እንጂ ያን ያህል አምርረን ልንጠላው የሚገባ አንዳች ጉድፍ አይደለም፡፡ ዋናው ችግር ያለው ከብሄራዊ ማንነትና ከኢትዮጵያዊ ዜግነት የትኛው ይበልጣል በሚል ማለቂያ የሌለው ፍትጊያ የሚካሄደው ሳብ-ገትር ወይም የገመድ ጉተታ ላይ ይመስለኛል፡፡ በመሰረቱ ኢትዮጵያ የሁለቱም ሀገር ናት፡፡ ብሄር-ብሄረ-ሰቦቿ ሲመነዘሩ ግለሰብ ዜጎቿ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያውያን በሁለቱም ደረጃ እኩል ህጋዊ ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል፡፡ እንደብሄር ብቻ ሳይሆን እንደዜጋም ጭምር እኩል የመታየትና ያለአድልዎ የመጠበቅ የማይሸራረፍ መብት አላቸው፡፡ ግንባሩ ታዲያ በዚህኛው የአቋም መግለጫው ላይ ብሄራዊ ማንነትን ከሀገራዊ አንድነት ጋር በንቃት አጣጥሞ ሲሰራ እንዳልቆየ በአደባባይ መናዘዙን እኔ በበኩሌ ለማድነቅ እፈልጋለሁ፡፡ ዛሬም ቢሆን እንዳልመሸ አያይዤ ለመምከር እወዳለሁ፡፡ እንደእውነቱ ከሆነ ኢትዮጵያ የብሄር ብሄረ-ሰቦች ሀገር መሆኗ አይካድም፡፡ ሆኖም እነዚህ ወገኖች ከሚለያዩባቸው ይልቅ የሚመሳሰሉባቸውና አልፏልፎም የአንደኛውን ብሄር ተወላጅ ከሌላኛው ለመለየት እስኪያቅት ድረስ ጭራሹን ተዋህደው የሚገኙባቸው ኩነቶች አመዝነው ይታያሉ፡፡ ስለሆነም በተፈጥሮ የተገኙ ልዩነቶችን በአግባቡ የማስተናገዱ እርምጃ ያለው ተገቢነት ሳይዘነጋ ከሁሉም በላይ ለዜግነት ቅድሚያውን ሰጥቶ መስራቱ አጥብቆ ይመከራል፡፡ ከዚህ አንጻር እስካሁን የተጓዝንበትን ርቀት በውል ፈትሸን የወደፊቱን ለማቃናት ቃል መግባቱ ሊበረታታ እንጂ ያን ያህል ሊጣጣል ወይም ሊስተሀቀር አይገባውም፡፡ 3.4. የሚዲያ ተቋማት ክትትልና ቁጥጥር ኢትዮጵያ ውስጥ ሃሳብን የመግለፅ ነፃነት በህገ-መንግሥት ደረጃ ተረጋግጧል፡፡ ይህንን መብት በተሟላ ሁኔታ ገቢራዊ ለማድረግ ደግሞ አይነተኛው መሳሪያ ሚዲያ ለመሆኑ አንድና ሁለት የለውም፡፡ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በዚህኛው የአቋም መግለጫው ታዲያ የግልም ሆነ የመንግስት መገናኛ-ብዙሀንን የስምሪት መስክ ለመወሰን የፈለገ መስሎ እንደተሰማኝ ለመደበቅ አልፈልግም፡፡ እንደግንባሩ አነጋገር ከሆነ የመገናኛ-ብዙሀን ተቋማት አተኩረው መስራት ያለባቸው በልማትና በዴሞክራታይዜሽን ወይም ህዝቦችን በማቀራረብ ላይ መሆን ይኖርበታል፡፡ አመለካከቱ በርግጥ በጎ ቢሆንም ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ይህንን ብሎ ብቻ መግለጫውን አልቋጨም፡፡ የግልና የመንግሥት መገናኛ-ብዙሃን ተቋማት ያአንድ ወገን ትርክት አፍራሽ መልዕክት ወይም ስብከት ማስተላለፊያዎች ሆነው ማገልገል እንደሌለባቸውና ከዚህ መስመር ወጥተው ቢገኙ ደግሞ ተገቢው እርምጃ እንደሚወሰድባቸው አፅንኦት ሰጥቶ እስከማስጠንቀቅ ዘልቋል፡፡ እዚህ ላይ የግሎችን ለጊዜው እናቆያቸውና ተግባራቸውን በመንግሥት ወጪ የሚያካሂዱ የመገናኛ-ብዙሀን ተቋማት የተለያዩ አስተያየቶችን የማስተናገድ ግዴታ እንዳለባቸው የሀገሪቱ ህገ-መንግሥት በአንቀፅ 29 ንዑስ አንቀፅ (5) ስር በግልፅ ደንግጎ እናገኘዋለን፡፡ ይህንን ግዴታ በመግለጫው መቀነስ ወይም ማሻሻል የማይቻል ጉዳይ መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል፡፡ ከዚህ አልፈው በግንባሩ እንደተፈራው ህዝብን ከህዝብ ጋር የሚያቃቅሩ፣ የጦርነት ቅስቀሳዎችን የሚያካሂዱ ወይም ሀገራዊ ሰላምንና ደህንነትን የማናጋት ውጤት ያላቸውን መልዕክቶች በዘፈቀደ ሲያሰራጩ የሚገኙ ተቋማት ቢኖሩ ለድርጊቶቻቸው የራሳቸውን ሃላፊነት ይወስዳሉ፣ በህግም ይጠየቃሉ፡፡ ስለሆነም ለጉዳዩ ዝርዝር የአሰራር ስነ-ስርዓት ዘርግቶ አፈፃፀሙን መከታተል የመንግሥት ሃላፊነት ነው፡፡ በዚህ ረገድ የሚወሰደው ማናቸውም እርምጃ ግን የምልአተ-ህዝቡን መረጃ የማግኘት መብት ከአጠቃላዩ የደህንነት ፍላጎት ጋር ባገናዘበ ሁኔታ በብርቱ የሃላፊነት ስሜት መፈጸም ይኖርበታል፡፡ 4. >ስምንቱ የውሳኔ ነጥቦች> የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከግምገማው በኋላ ውሳኔ የሰጠባቸው አበይት ነጥቦች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው፡- 1. >ሁከት ፈጣሪዎችን በመቆጣጠር ህግና ስርአትን ማስከበርና የህብረተ-ሰቡ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ሳይስተጓጎል መቀጠሉን ማረጋገጥ፤> 2. >ብሄራዊ ድርጅቶች በከፍተኛ አመራር ደረጃ የየራሳቸውን ጥልቅ ግምገማ እንዲያካሂዱና የእርምትና የማስተካከያ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ማድረግ፤> 3. >በክልሎች መካከል የሚታዩ የልማት አቅርቦት ልዩነቶችን ማጥበብና ሀገራዊ አንድነትን ማጠናከር፤> 4. >የሪፎርም ፕሮግራሞችን መከለስና አተገባበራቸውን ከወቅቱ የህዝብ ጥያቄዎች ጋር ማጣጣም፤> 5. >የህዝብን አመኔታ መልሶ ለማግኘትና ለአንገብጋቢ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ ተከታታይ እርምጃዎችን መውሰድ፣ ብሎም ህዝብ የሚደመጥበትንና ወሳኝነቱ የሚረጋገጥበትን እድል ማስፋት፤> 6. >ከሁሉም ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችና ከህዝቡ ጋር በመተባበር በመድበለ-ፓርቲ ስርአት ግንባታ ውስጥ የሚታዩትን ጉድለቶች ለመቅረፍ መንቀሳቀስ፤> 7. >በህገ-መንግሥቱ የተከበሩ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን የመጣስ አዝማሚያዎችንና ተግባራትን አጥብቆ መመከትና መከላከል፤> 8. >ህዝብን ከህዝብ ጋር በሚያራርቅ አፍራሽ ተግባር ላይ የተሰማሩ የግልና የመንግሥት መገናኛ-ብዙሃን ተቋማት አካሄዳቸውን እንዲያስተካክሉ ማድረግ፡፡>
ማሳሰቢያ አልፏልፎ የነካካኋቸው ቢሆንም እነዚህን የውሳኔ ነጥቦች በሚመለከት ከማዘጋጀው አጭር ትንታኔ ጋር ሳምንት እመለሳለሁ፡፡
ብቻ የዚያ ሰው ይበለን፡፡ |
Breaking the taboo By: Merhatsidk Mekonnen Abayneh Bahir Dar, January 17 2018 The right to freedom of expression in the form of art or any other medium of transmission on one’s own choice is so fundamental that it has been duly guaranteed under Art. 29 Sub-Art. (2) of the F.D.R.E’s Constitution of 1995. Nobody can easily revoke or restrain its exercise and enjoyment in an arbitrary and irresponsible manner as it so happens on a number of instances these days. Artist Tewodros Kasahun, best known for ‘Teddy Afro’, is warming up for a music concert ever to be held in Bahir Dar very shortly following his repeated rejections in the Capital, Addis Ababa. In fact, it is quite troubling to recollect that such an iconic and beloved Star of his generation has been turned down to show up with similar concerts on several occasions before, simply for lack of prior permission from the relevant authorities approached, in the first place. ‘Ethiopia’, the latest album of Teddy Afro, has been hitting a record high in the country’s music history and is being tuned to by the people of all ages almost like a national anthem. Admittedly The lion-share of his contemporary songs are, often times, reflective of His strong passion for love and peace in favor of national unity and reconcilliation, to say the least. On the contrary, though, there are certain elements in the mainstream society who would like to brand the iconic figure as the champion of the old order desperately preserving and even advancing the defunct ideology of the unitary state. This ill-considered branding might, in my view, have been attributable to some of his moving lerics which tend to amply honor and dignify the pioneering Ethiopian monarchs like Emperors Teodros, Menilik ii and Haile-Sillassie I along with their respective contributions viz-a-viz the country’s nation-building process. Yet, he did not, at times, hesitate or shy away to equally reflect on the corresponding weaknesses of , especially the dictatorial Dereg regime, along with its succeeding system of state administration to this date for what he also considers them to be unfit for the highest public office in their consecutive ages and styles of governance. ‘Yasteserrial’, one of his popular and remarkable hits released in 2005, would perhaps suffice to depict the singer’s uncompromising distaste for any form of authoritarian tendency and action, whoever is the perpetrator. To my compelling belief, Teddy Afro keeps on promoting mutual love and compassion in his songs under the banner of Ethiopian unity and peaceful co-existence between and among its all citizens and communities without discrimination. Thus, one cannot confidently resonate that he is in favor of the unitary system of state governance and administration simply for his consistent and unrelenting outcry for the national concordance and collaboration of his compatriots in the wake of a looming threat to our outstanding and age-old values jealously defended and preserved by our outgoing forefathers. In my view, Tewodros is more a social engineer determined to preach and promote lasting peace and love than a politician poised to challenge an existing political superstructure having consciously rallied behind an organized and ideologically solidified system of views and institutions. At any rate, we will be able to witness his magic performance out in the open and try to capture his ideal instrumentality for the furtherance of intergroup tolerance and social cohesion, not later than Sunday, January 21, 2018. Thanks to the Bahir Dar City Administration which has finally managed to break the taboo and allowed the beloved Star to organize and show the upcoming concert in a dramatic move against the backdrop of misguided prohibitions and last-minute cancellations of pre-arranged events he had to pass through at the national level with little or no justifications at all.
የኳራንታይን አገልገሎት ክፍያ ተመን መጽደቁ ተገለጸ፡፡ የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት 5ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን ህዳር 15 ቀን 2010 ዓ.ም ባደረገው 10ኛ መደበኛ ስብሰባ የኳራንታይን አገልገሎት ክፍያ ተመን ማጽደቁን ገለጸ፡፡ የአማራ ክልል የእፅዋት፣ ዘርና ሌሎች የግብርና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥርና ኳራንታይን ባለስልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሙሉጌታ ደባሱ እንደገለጹት የዕፅዋት፣ ዘርና ሌሎች የግብርና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥርና ኳራንታይን ባለስልጣን በመስክ የዘር ጥራት ቁጥጥር፣ ላብራቶሪ ፍተሻ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የአገልግሎት ክፍያ እንዲያስፈጽም በዘር ደንብ ቁጥር 661/2008 እና በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዕቃና የአገልግልት ክፍያ መመሪያ ቁጥር 7/2004 የተፈቀደ ቢሆንም በመደበኛነት የማይከናወንና ለእቃውና ለአገልገሎቱ የሚጠይቀው የተናጠል ዋጋ ከብር 50 በላይ በሚሆንበት ጊዜ በመመሪያው አንቀጽ 6(3) (ሐ) በተደነገገው መሰረት የመንግስት መስሪያ ቤቶች ማንኛውም የእቃ እና የአገልግሎት ክፍያ ማስከፈል የሚቻለው ለገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የውሳኔ ሃሳብ ቀርቦ መስተዳድር ምክር ቤቱ ሲፈቅድ ብቻ በመሆኑ መስተዳድር ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ መክሮ እንዲፈቅድ የቀረበ ጥያቄ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ዋና ሥራ አስኪያጁ አክለውም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያቀረበው የእፅዋት ዘር የብቃት ማረጋገጫና ተያያዥ አገልግሎቶች የክፍያ ተመን በፌዴራል ፀድቆ በደቡብና በኦሮሚያ ክለሎችም እየተሰራበት ያለና ተግባሩም ተመሳሳይ መሆኑን አብረርተዋል፡፡ መስተዳድር ምክር ቤቱም በቀረበው ሃሳብ ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን በማንሳት በጉዳዩ ላይ በስፋት ተወያይቶ፣ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ በመስክ የዘር ጥራት ቁጥጥር፣ ላቦራቶሪ ፍተሻና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የአገልግሎት ክፍያ ማስፈፀም በመሆኑ ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የአገልግሎት ክፍያ ማስፈፀም እንዳለበት በመስማማት፣ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ጥያቄና በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በኩል ተደግፎ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ መሰረት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀድቆ በወጣው የዕፅዋት ዘር የብቃት ማረጋገጫና የተያያዥ አገልግሎቶች የክፍያ ተመን ደንብ ላይ የተቀመጠው የአገልግሎት ክፍያ ተመን በክልሉም ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ ታህሳስ 25/2010 ዓ.ም የዳያስፖራና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት |