የክልሉ ህዝብ ቅሬታ ሰሚ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አደረገ

የክልሉ ህዝብ ቅሬታ ሰሚ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አደረገ፤

የአብክመ የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ከክልሉ አጋርና ባለድርሻ አካላት፣ ቢሮ ኃላፊዎችና መምሪያ ኃላፊዎች በተገኙበት በቅሬታ ማስተናገጃ ስርዓቱ ውጤታማነት እና የአፈጻጸም ችግሮች ዙሪያ አስመልክቶ የተፈጸሙ ጠንካራ ጎኖችን በምሳሌ እየገለፁ በአፈጻጸም በኩል ጥሩ ትብብር የሚያደርጉ መስሪያ ቤቶች እንዳሉና በእጥረትም በአፈጻጸም ላይ የታዩትን ዘርዘር አድርገው በማቅረብ ተሳታፊው ይህንን መነሻ በማድረግ በሰፊው እንዲወያዩበት የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ዳይሬክተሩ አቶ ያረጋል አስፋው ገልዋል፡፡

ጽሁፉን መነሻ በማድረግ ከባለድርሻ አካላት፣ አጋር አካላትና ከየቢሮዎች የተገኙ ኃላፊዎች የቅሬታ ማስተናገጃ ስርዓቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ውጤታማ እንዲሆን ሁሉም የየራሱን ድርሻ እንዲወጣ የመልካም አስተዳደር ስርዓቱ እምርታ እንዲያመጣ ሁላችንም የየድርሻችን እንወጣለን ሲሉ ሁሉም ተሳታፊዎች ቃል ገብተው የስብሰባው ማጠቃለያ ሁኗል፡፡

መጋቢት 19/2010 ዓ.ም

የዳያስፖራና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት

 

 

የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ለዞንና ወራዳ የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ኃላፊዎችና ትምህርት ስልጠና ሱፐርቪዥን ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱ ተገለጸ፡፡

የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ለዞንና ወራዳ የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ኃላፊዎችና ትምህርት ስልጠና ሱፐርቪዥን ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱ ተገለጸ፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የህዝብ ቅሬታ ሰሚ 56 ለሚሆኑ ለዞንና ወራዳ ቅሬታ ሰሚ ኃላፊዎችና ትምህርት ስልጠና ሱፐርቪዥን ባለሙያዎች በማህበራዊ ተጠቃሚነት አሃዝ ካርድ አሰራር ተሞክሮ፣ በዳሰሳ ጥናት አሰራርና መረጃ አሰባሰብ ጽንሰ ሃሳብ ዙሪያ ከመጋቢት 16-18/2010 ዓ.ም በደብረ ታቦር ከተማ ስልጠና መስጠቱን አስታወቀ፡፡

የክልሉ ህዝብ ቅሬታ ሰሚ ኃላፊ አቶ ሰይድ እሸቴ እንደተናገሩት የስልጠናው ዋና ዓላማ በማህበራዊ ተጠቃሚነት አሃዝ ካርድ አሰራር ተሞክሮ፣ በዳሰሳ ጥናት አሰራርና መረጃ አሰባሰብ ጽንሰ ሃሳብ ዙሪያ ግልጽ ግንዛቤ ተፈጥሮ በየተቋማቱ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን ያስችላል ብለዋል፡፡፡

በዋናነት በስልጠናው ትኩረት ከተሰጠባቸው ርዕሰ ጉዳዮች መካከል የዳሰሳ ጥናት አሰራርና መረጃ አሰባሰብ ጽንሰ ሃሳብ፣ የጥናት ዓይነቶችና የመረጃ አሠባሰብ ስልቶች፣ አሁን በተግባር እየተሰራ ያለው ጥናትና ውጤቱ በሚሉት ጉዳዮች ላይ ለተሳታፊዎቹ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት የተሰጠ ሲሆን ከባህር ዳር ዩኒቨርስቲ በመጡ ሙህራኖች የመረጃ አጠነቃቀር ስልቶችን "IBM" ወይም ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ማሽን በተባለ ሶፍትዌር ፕሮግራም የተግባር ልምምድ ትምህርት ለሠልጣኞቹ ተሰጥቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በማህበራዊ ተጠያቂነት አሃዝ ካርድ አሠራር የተመረጡ ወረዳዎች ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን፣ በክልሉ በኩል ደግሞ የተዘጋጀ መስክ ምልከታ ግብረ መልስ እና ተሞክሮዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

ከስልጠናው ተሳታፊዎች መካከል ከሰሜን ወሎ ዞን ጉባ ላፍቶ ወረዳ ወ/ሮ ገነት እና ከምዕራብ ጎጃም ዞን ጃቢጠናን ወረዳ አቶ ስንታየሁ ስልጠናውን አስመልክተው አስተያየት ሲሰጡ ከስልጠናው በቂ ትምህርት ማግኘታቸውን ጠቅሰው የተማሩትን ትምህርት ተግባራዊ በማድረግ ለሌሎች ማስተማር እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

መጋቢት 19/2010 ዓ.ም

የዳያስፖራና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተደራጀው አብይ ኮሚቴ በTana High Level Forum ስብሰባ ቅድመ ዝግጅት ላይ ለ3ኛ ጊዜ ውይይት አካሔደ፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተደራጀው አብይ ኮሚቴ በTana High Level Forum ስብሰባ ቅድመ ዝግጅት ላይ ለ3ኛ ጊዜ ውይይት አካሔደ፡፡

በባህር ዳር ከተማ ለ7ኛ ጊዜ በሚካሔደው የTana High Level Forum ስብሰባ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ ሁሉም የኮሚቴ አባላት በተገኙበት የተካሔደ ሲሆን ስብሰባውን የመሩትም የፎረሙ አብይ ኮሚቴ ም/ሰብሳቢ የሆኑት የአብክመ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ንጉሱ ጥላሁን ናቸው፡፡

በዚህ ውይይትም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሰላምና ደህንነት ጥናት ተቋም (IPSS) የማኔጅመንት አባላት፣ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር፣ የፀጥታ መዋቅሩና ሌሎች ሴክተር መስሪያ ቤቶች ተሳትፈዋል፡፡ እንግዶችን በአግባቡ ለመቀበል የተደረጉ ቅድመ ዝግጅቶች፣ የከተማዋን ፅዳትና ውበት ለማሻሻል እየተሰሩ ያሉ ስራዎች፣ እንግዶች የሚያርፉባቸው ሆቴሎች ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ስለሚሰጡበት ሁኔታና የከተማዋን አጠቃላይ የቱሪዝም ፍሰት ለማሳደግ በሚሰሩ ስራዎች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡ ከሚያዝያ 13-14/2010 ዓ.ም የሚካሔደውን ስብሰባ ካለፉት አመታት በተሻለ መንገድ ለማካሔድ የክልሉ መንግስትና ህዝብ ተቀናጅተው እንደሚሰሩ የአብይ ኮሚቴው ም/ሰብሳቢ አብራርተዋል፡፡

 

የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት እና የዞን አስተዳደር ጽ/ቤቶች የ2010 በጀት አመት የመጀመሪያው የ6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተጀመረ፡፡

የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት እና የዞን አስተዳደር ጽ/ቤቶች የ2010 በጀት አመት የመጀመሪያው የ6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተጀመረ፡፡

የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ከዞን አስተዳደርና ከንቲባ ጽ/ቤቶች ጋር በባህር ዳር ከተማ የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ ውይይት የሚደረግባቸው ርዕሰ ጉዳዮች፡-

- የፕላን ኮሚሽን አደረጃጀትና የአስተዳደር ጽ/ቤቶች ቅንጅታዊ አሠራር

- የዞንና የከንቲባ አስተዳደር ጽ/ቤቶች የሠው ኃይል አደረጃጀት ስምሪትና የጥያቄ አቀራረብ

- የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አስፈላጊነትና ክልላዊ ሁኔታዎች

- የህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እና ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች መንስኤና ውጤት ክልላዊ ገጽታ

- የገጠር ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ለየደረጃው አስተዳደር ጽ/ቤቶች ስራ መቃናት ያለው ፍይዳ፤ አስተዳደርና አጠቃቀም

- የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የ6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት

- የዞንና የከንቲባ ጽ/ቤቶች ሪፖርት

- የቀጣይ ወራት ትኩረት አቅጣጫዎች ሲሆኑ፤

የምክክር መድረኩ ከመጋቢት 12-14/2010 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ይሆናል፡፡

መጋቢት 12/2010 ዓ.ም

የዳያስፖራና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት

 

በአማራ ብሔራዊ ክልል ከስደት ተመላሾችን በILO ፕሮጀክት ለማቋቋም የተከናወኑ ተግባራትና ያጋጠሙ ችግሮችን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደረገ፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልል ከስደት ተመላሾችን በILO ፕሮጀክት ለማቋቋም የተከናወኑ ተግባራትና ያጋጠሙ ችግሮችን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደረገ፡፡

ከስደት ተመላሾች በክልላቸው ሰርተው መኖር የሚያስችላቸውን አቅም ለመፍጠር፣ የስልጠናና ሌሎች ድጋፎችን ለማድረግ በተዘጋጀው ፕሮጀክት አፈጻጸም ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተደረገውን ውይይት የመሩት የአብክመ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ያየህ አዲስ ሲሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ያከናወኑትን ተግባራትና ያጋጠሙትን ችግሮች በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

እስካሁን ድረስ 3,397 ለሚሆኑ ተመላሾች የኢንተርፕሪነር ስልጠና መውሰዳቸውንና 1582 ለሚሆኑ ተመላሾችም የሙያ ስልጠና መሰጠቱን የአብክመ ሙያ፣ ቴክኒክና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ አሳውቋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ለ796 ተመላሾች 19,779,260 ብር ከአብቁተ ብድር መውሰዳቸውን በውይይቱ ተገልጿል፡፡

የባለድርሻ አካላት ተቀናጅቶ አለመስራትና የተለያዩ ስልጠናዎችን ከወሰዱት ተመላሾች ውስጥ የደረሱበትን ደረጃ በመከታተል ውስንነት መኖሩንም ተገምግሟል፡፡ በቀጣይም ፕሮጀክቱ ተግባራዊ በሚደረግባቸው ዞኖችና ወረዳዎች አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አብራርተዋል፡፡

መጋቢት 07/2010 ዓ.ም

የዳያስፖራና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት

 

 
 • «
 •  Start 
 •  Prev 
 •  1 
 •  2 
 •  3 
 •  4 
 •  5 
 •  6 
 •  7 
 •  8 
 •  9 
 •  10 
 •  Next 
 •  End 
 • »


Page 1 of 17
Content View Hits : 9427862

Comments

 • It's a shame yyou dоn't have a donate button! I'd ...
 • Ꮤow that ѡas unusual. I just wrߋte an very long co...
 • I do truѕt all the ideas you've introduced on your...
 • Ꮤow that ѡas unusual. I just wrߋte an very long co...
 • Ꮤow that ѡas unusual. I just wrߋte an very long co...

Latest News

Who is online

We have 128 guests and 15 members online

Entertainment