በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ሰራተኞች የጥልቅ ተሀድሶ መጀመራቸው ተገለጸ
የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ሰራተኞች "ብቁና ውጤታማ ሲቪል ሰርቪስ ለአገራዊ ህዳሴ!" በሚል መሪ ቃል ለተከታታይ ለ5 ቀን የሚቆይ የጥልቅ ተሃድሶ መድረክ ጀመሩ፡፡ ለተሃድሶው የተዘጋጀው ጽሁፍ ዋና ዓላማው በጥልቅ ተሃድሶው አልፎ ህዝቡን እንዲያገለግል ያለመ ነው፡፡
ሲቪል ሰርቫንቱ የመንግስትን ስትራቴጂ በአግባቡ በመፈጸም ለህብረተሰቡ ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ ሆኖ እንዲፈጽም ተሃድሶው አስፈላጊ መሆኑን ተወያይቶ በመስማማት ውይይቱም በተጠናከረ ሁኔታ በከፍተኛ አመራሮች አወያይነት እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በ2009 በጀት ዓመት በምደባ ለተጠቃሚዎች የሚተላለፍ የከተማ መሬት አቅርቦት በእቅድ መያዙ ተገለጸ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት መስተዳድር ምክር ቤት አምስተኛ ዙር ሁለተኛ አመት የሥራ ዘመን ህዳር 23 ቀን 2009 ዓ.ም ባደረገው 6ኛ መደበኛ ስብሰባ በ2009 በጀት ዓመት በምደባ ለተጠቃሚዎች የሚተላለፍ የከተማ መሬት አቅርቦት እቅድ ማፅደቁን ገለጸ፡፡ ውይይቱ የተጀመረው የከተማ ልማት፣ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ም/ኃላፊ በተሰጠ ማብራሪያ ሲሆን በክልሉ የሊዝ ደንብ ቁጥር 104/2004 አንቀጽ 22 ንዑስ አንቀጽ አንድ መሠረት በምደባ የሚቀርብ የመሬት ዕቅድ በቢሮው በኩል ቀርቦ በመስተዳድር ምክር ቤቱ ከፀደቀ በኃላ አተገባበሩ በከተሞች በኩል እንዲፈጸም ከተሞች መረጃውን በማሰባሰብ በቢሮው በኩል ተዘጋጁቶ መቅረቡን ገልጸው፣ በዚህም በክልሉ በሚገኙ ከተሞች መሬትን በዕቅድና በቁጠባ ፍትሃዊነትና ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ማቅረብ እንዲቻል በበጀት ዓመቱ ተለይቶ በሁሉም የክልሉ ከተሞች በምደባ ለተጠቃሚዎች የሚተላለፈውን የቦታ መጠን በአገልግሎት አይነት በዝርዝር በማቅረብ ምክር ቤቱ ተደራጅቶ የቀረበውን ዕቅድ እንዲያፀድቅላቸው ጠይቀዋል፡፡
በዚህም መሰረት ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ በጥልቀት ተወያይቶ በክልሉ ውስጥ በሚገኙት ከተሞች መሬትን በእቅድና በቁጠባ ፍትሃዊና ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ማቅረብ እንዲቻል በበጀት ዓመቱ ውስጥ በሁሉም የክልሉ ከተሞች በምደባ ለተጠቃሚዎች የሚተላለፈው የቦታ መጠን በአገልግሎት አይነት ተለይቶ በዝርዝር ተዘጋጅቶ የቀረበው እቅድ መረጃው ከሁሉም ከተሞች ተሰባስቦ በቢሮው በኩል ተደራጅቶ እንዲፀድቅ መቅረቡ ተገቢ መሆኑ ላይ በማስማማት ተዘጋጅቶ የቀረበውን እቅድ በቀረበበት አግባብ ምክር ቤቱ ወስኗል፡፡ ለሁለት ሽሀ ዘጠኝ በጀት ዓመት ለስፖርት ምከር ቤት ሥራ ማስኬጃ የሚሆን በጀት ተመደበ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት መስተዳድር ም/ቤት አምስተኛ ዙር ሁለተኛ ዓመት የሥራ ዘመን ህዳር 16 ቀን 2009 ዓ.ም ባደረገው አምስተኛ መደበኛ ስብሰባ ለ2009 በጀት አመት ለስፖርት ምክር ቤትና ለወልዲያ ስታዲየም ምርቃት የሚሆን 20.3 ሚሊዮን ብር መመደቡን፣ምክር ቤቱ ገልጻል፡፡ ውይይቱ የተጀመረው በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በኩል በታየበት ወቅት የተደረሰበትን የውሣኔ ሃሳብ የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በዝርዝር በማቅረብ ሲሆን በዚህም መነሻ የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ ለ2009 በጀት ዓመት በስፖርት ምክር ቤት የብር 61.2 ሚሊዩን በላይ ድጋፍ እንዲደረግለት እንዲሁም በወልዲያ ከተማ የተገነባውን ዘመናዊ ስታዲየም የሚመረቅበት ወቅት ታሪካዊ ሥራ ለሠሩት አካላት እውቅና ለመስጠትና ለከተማ አስተዳደሩ የመስተንግዶ ወጭ ለመደገፍ ብር ሦስት መቶ ሰባ ሺህ እንዲደገፍ ባቀረበው ጥያቄ ላይ የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ክልሉ ካለው በጀት አንፃር ተገቢነቱን መርምሮ የቀረበውን የውሣኔ ሃሣብ መስተዳድር ምክር ቤት ውሣኔ እንዲሰጥበት ጠይቀዋል፡፡ በዚህም መሠረት መስተዳድር ምክር ቤቱ በቀረበው ሃሣብ ላይ በጥልቀት ከተወያየ በኃላ በቢሮው በኩል በቀረበው የውሣኔ ሃሣብ በመስማማት፣ 1ኛ. ለስፖርት ምክር ቤት 20 ሚሊዮን ብር
2ኛ. ለወልደያ ከተማ ስታዲየም ምርቃት የሚውል ብር ሦስት መቶ ሺህ እንዲሁም ለግለሰቦች እውቅና ለመስጠት በአይነት ለሚሰጥ ሽልማት ብር 30,950= በድምሩ 20,300,950/ሃያ ሚሊዮን ሦስት መቶ ሰላሣ ሺህ ዘጠኝ መቶ አምሣ ብር ድጋፍ እንዲደረግ መስተዳድር ም/ቤቱ ወስኗል፡፡ |
የአማራ ክልል የአፈር ለምነት ዳሰሣ ጥናት እና የማዳበሪያ አጠቃቀም ምክረሃሣብ መጽሐፍት ካርታ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የማስረከብ ስነ-ሰርዓት ተከናወነ፡፡ የአፈር ለምነተና የማዳበሪያ አጠቃቀም ምክረሃሣብ መጽሐፍ ካርታ ርክክብ ስነ-ስርዓት መካሄዱን ተገለፀ መጽሃፋ ካርታው ኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ እና ግብርና የተፈጥሮ ሃብት ሚኒስቴር የጋራ ጥረት የሆነው የኢትዮጵያ የአፈር ሃብት መረጃ ሥርዓት ኘሮጀክት ውጤት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ይህ ፈር ቀዳጅ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ስለ አፈር ለምነት ዘመናዊ የሆነ መረጃ ለማግኘት ያለውን ችግር በመቅረፋ አርሶአደሮች በበቂ ሁኔታ ተገቢውን ማዳበሪ እንዲጠቀሙ ለማድረግ ታልሞ በ2004 ዓ.ም መጀመሩን ገልፀዋል፡፡ መፅሀፍ ካርታው በግብርናው ዘርፍ ወሣኝ ሚና ካላቸው አንዱ የሆነውን የአፈርን ጤንነትና ለምነት ይመለከታል፡፡ በዚህ መሠረት ለአፈር ለምነት ችግር ሣይንሣዊ ምላሽ በመስጠት ድህነትን ለማጥፋት እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን የአብክመ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ገልፀዋል፡፡ በመጽሀፍ ካርታው በአማራ ክልል የሚገኙ 134 ወረዳዎችና ቀበሌዎች የአፈር ለምነት ሁኔታዎች አንድ በአንድ ማዳበሪያ አጠቃቀም ምክረሃሣባቸው የተዘረዘሩ ሲሆን የነዚህን ወረዳዎች የአፈር ለምነት ዳሰሣ ውጤት ለመግለጽ ሃያ ሁለት የአፈር ለምነት መገምገሚያ ባህሪ ጥቅም ላይ መዋሉን ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም የመድረክ መሪው እንደገለፅት ይህ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያን የአፈር ለምነት ሁኔታ እና የመሬት ገፅታ በካርታ የማስቀመጥ ሥራ በአይነትና በመጠን በአፍሪካ የመጀመሪያው እንደሆነ ጠቁመው የክልሉ መንግስት ይህን ካርታ መሬት ላይ በማሣረፋ የክልሉን ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር የሚመለከታቸውን ባለሙያዎች በማሠማራት ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ የአርሶአደሩን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ተገቢ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ በክልል ደረጃ የሚገኘውን የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲን አደረጃጀት ሥራ ለማስጀመር በጀት መመደቡ ተገለጸ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት መስተዳድር ም/ቤት አምስተኛ ዙር ሁለተኛ ዓመት የሥራ ዘመን ህዳር 16 ቀን 2009 ዓ.ም ባካሄደው አምስተኛ መደበኛ ስብሰባ በክልል ደረጃ ለሚገኘው የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲን አደረጃጀት ሥራ ለማስጀመር ለደመወዝና ለሥራ ማስኬጃ የሚሆን ከ6.6 ሚሊዮን ብር በላይ መመደቡን መስተዳድር ም/ቤቱ ገለጸ፡፡ ውይይቱ የተጀመረው የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ኃላፊ እና በክልል ደረጃ የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ እንዲሁ በስድስት ከተሞች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እንዲኖር በተወሰነው መሠረት ኤጀንሲው ለ2009 በጀት ዓመት ለደመወዝና ስራ ማስኬጃ ብር 16,575,687.00 በጀት እንዲፈቀድለት ያቀረበው ጥያቄ በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በኩል ታይቶ የቀረበውን የውሣኔ ሃሣብ መነሻ በማድረግ ነው፡፡
መስተዳድር ምክር ቤቱም በቀረበው ሃሣብ ላይ በጥልቀት ተወያይቶ ቢሮው የጉዳዩን አግባብነት መርምሮ በቀረበው የውሣኔ ሃሣብ ላይ በመስማማት፣ኤጀንሲው በተወሰነ ደረጃ ሥራ ለማስጀመር ይቻል ዘንድ ለሥራ ማስኬጃና ለደመወዝ የሚሆን ብር 6,656,570/ስድስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሃምሣ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ሰባ ብር እንዲፈቀድ በስምምነት መስተዳድር ም/ቤቱ ወስኗል፡፡ |
- የአብክመ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በፍኖተ ሰላም ከተማ የምክክር መድረክ ማካሄዱን ጽ/ቤቱ አስታወቀ
- The Emergence and Evolution of Intergovernmental Relations in Ethiopia: Processes, Institutional Arrangements and Structures in the Making
- የፈለገ ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል ማስፋፊያ ሥራ መፈቀዱ ተገለጸ
- ከ200 በላይ ለሚሆኑ የቅሬታ መርማሪና አጣሪ ባለሙያዎች በእንጅባራ ከተማ ስልጠና መሠጠቱ ተገለፀ፡፡