የጎሽሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ደንብ መውጣት ተገለጸ፡፡
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት 5ኛ ዙር ሁለተኛ ዓመት የስራ ዘመን ታህሳስ 14 ቀን 2009 ዓ.ም ባካሄደው 7ኛ መደበኛ ስብሰባ የጎሽሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅትን ለማቋቋም የወጣውን ረቂቅ ደንብ መጽደቁን ገለጸ፡፡
በኤጀንሲው ላይ ውይይት ሲካሄድ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ድጋፍና ክትትል ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በአስረጂነት ተገኝተው ጉዳዩን አብራርተዋል፡፡ የጎሽሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት በደሴ ከተማ በአዲስ የሚቋቋም ድርጅት መሆኑ ከአሁን በፊት ይህን ማምረቻ ድርጅት ከግል ባለሃብቶች ጋር በጋራ ለማቋቋም ተሞክሮ ስላልተሳካ አሁን ሙሉበሙሉ በመንግስት የልማት ድርጅቶች ተሸፍኖ እንዲደራጅ የተደረገ መሆኑንና ዓላማውም ባህር ዳር ከተማ ካለው የቧንቧ ፍብሪካ ጋር ተመሳሳይ በሆነ መንገድ የተለያዩ የቧንቧና ፕላስቲክ ውጤቶች በማምረት በኩል በክልሉ ምስራቃዊ አካባቢ ያለውን ሰፊ የገበያ ፍላጎት ለሟሟላት እንዲችል ተደርጎ የተጠና መሆኑን በዝርዝር አስረድተዋል፡፡
የስራ ኃላፊው አያይዘውም ድርጅቱ ከአሁን በፊት በጆይንት ቬንቸር ለመስራት ታስቦ በቦርድ የተቋቋመ ቢሆንም በቅርቡ አደረጃጀቱ በቦርድ ብቻ ሳይሆን በስራ አስኪያጅና የተወሰነ የሰው ኃይል በማቋቋም ስራው የተጀመረበት ሁኔታ እንዳለና የቴክኖሎጂ መረጣም ተካሂዶ ግዥ ለመፈጸም በጨረታ ሂደት ላይ ስለሚገኝ ድርጅቱ በደንብ እንዲቋቋምና ደንቡ ፈጥኖ ውሳኔ ማግኘት ስላለበት መስተዳድር ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ መክሮ ውሳኔ እንዲሰጥበት ጠይቀዋል፡፡
መስተዳድር ምክር ቤቱም በቀረበው ሃሳብ ላይ የተለያዩ አስተያየቶችን በማንሳት ሰፊ ውይይት ካካሄደ በኋላ የቧንቧና የተለያዩ የፕላስቲክ ውጤቶችን አምርቶ በማከፋፈል አገልግሎት ላይ መሰማራት ለክልሉ ሁለንተናዊ እድገት ጉልህ አስተዋፅዖ አለው፡፡ ከምርቱ ውስንነቶች ጋር በተያያዘ ምርቱን የዝናብ እጥረት ባለባቸው የክልሉ አካባቢዎች ብቻ እንዲሰራጭ የነበረውን አቅርቦቱን በማሳደግ ምርታማ በሆኑ አካባቢዎችም ለማረስ የሚያስችል በመሆኑ በቀረበው ሃሳብ ላይ በመስማማት የጎሽሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅትን ለማቋቋም የመጣውን ደንብ መስተዳድር ምክር ቤቱ የመስተዳድር ምክር ቤቱ ደንብ ሆኖ እንዲወጣ ወስኗል፡፡
የተከዜ ተፋሰስን በዘላቂነት ለማልማት አውደ ጥናት ተካሄደ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የክልሉ ፕላን ኮሚሽን ያዘጋጀውን የተከዜ ተፋሰስን በዘላቂነት ለማልማት የተዘጋጀ የፖሊሲ አስመልካች ሠነድ ቀርቦ አውደ ጥናት መካሄዱ ተገለጸ፡፡ ተሰብሳቢ አባላት የክልሉ ካቢኒዎች እና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በ17 ቁጥር አዳራሽ አውደ ጥናቱ ማካሄዱ ጥናቱን ያቀረቡት የክልሉ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ በድሉ ስለጥናቱ ጠ ቀሜታውና በውስጡ ያካተታቸውን ዋና ዋና ነጥቦች አስረድተው(አስተዋውቀው) ሲያበቁ በዋናነት ጥናቱን የተከታተለው ባለሙያ የተጠናውን ጥናት ዘርዘር አድርገው አቅርበዋል፡፡
የዓለም ባንክ ባቀረበው ጥናት መሰረት በሀገራችን ድርቅ 8%ቱን እንደምትይዝና ከሳህራ በታች ካአሉት ሃገራት ሃገራችን በድርቅ በ1ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ ይህንን ድርቅ ስንመለከተው ባለፉት አመታት ህዝቦችን ከድህነት ወለል በታች የነበሩት 42% ሲሆኑ መንግስታችን ባደረገው ተከታታይ የ15 ዓመታት ባመጣው እድገት ከድህነት ወለል በታች የሚገኙት በ2007 ዓ.ም ወደ 22.9% ዝቅ ለማድረግ በተለያዩ የልማት መስኮች ሰፊ ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል፡፡ የአውደ ጥናቱ ዋና ዓላማ ድህነትን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችሉ አማራጮችን ማመልከት ከአፈጻጸማችን የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን የተወሰዱ ትምህርቶችን እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮችን በተጨባች ጥናት ላይ ተመስርቶ ለመለየትና ቀጠናውን በዘላቂነት መቀየር የሚያስችሉ ፕሮግራሞችንና ፕሮጄክቶችን በመቅረጽ የአመለካከትና ረዥም ጊዜ እቅዶችን በመቅረጽ ቀጠናውን በዘላቂነት ለማልማት ወይም ለመቀየር ወሳኝ የሆኑ ልማት ሃብቶችንና አማራጮችን በመረጃ ላይ ተመስርቶ ማመልከት መሆኑን በሰፊው አብራርተዋል፡፡
የጥናቱ ሠነድ በፕሮጀክተር በተደገፈ በዝርዝር ከቀረበ በኋላ ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ስብሰባውን የመሩ ሲሆን ጥናቱ በተከዜ ተፋሰስ ላይ ያተኮረ ቢሆንም በቀጣይ በአባይና በአዋሽ ተፋሰሶችም እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ የካቤኔ አባላቱም ጥናቱ እንደመነሻ ጥሩ ነው ችግሮቹንም በግልጽ የዳሰሰ መፍትሄወችንም ያስቀመጠና የብዙ አገሮችን ተሞክሮም ያካተተ ስለሆነ ጥሩ ነው፡፡ በተጨማሪም ከዚህ ቀደም በስራ ላይ በአሉት የአገር ውስጥ ድርጅቶች ለምሳሌ እንደ አመልድ የመሳሰሉትን ተሞክሮዎች ቢካተቱ እና ባለድርሻ አካላት የሆኑ ቢሮዎችንም የየድርሻቸውን አቅደው ቢንቀሳቀሱ ውጤታማ ያደርገዋል ብለዋል፡፡ የቆበ ጊራና ሸለቆ ልማት ፕሮጀክት ተጎበኘ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር በቆቦ ወረዳ የሚገኘው ቆቦ ጊራና ሸለቆ ልማት ፕሮጀክት ቆቦ ዙሪያ 01 ቀበሌ እና አዩ 03 ቀበሌ ያለውን የሽንኩርት ልማት በጠቅላይ ሚኒስተሩ በክቡር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ጥር 5 ቀን 2009 ዓ.ም ሌሎች ሚኒስተሮችና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸውና የቢሮ ኃላፊወች በተገኙበት መጎብኘቱ ተገለጸ፡፡
የቆቦ ጊራና ሸለቆ ልማት ሁለት ቀበሌዎች የሚያለሙት አርሶአደሮች ተጠቃሚነታቸውን ሲያብራሩ ይህ ልማት ከመጀመሩ በፊት እንኳን ለመስኖ ለመጠጥ ውሃም ከጎረቤት ቀበሌዎች ቀኑን ተጉዘን ሂደን ነበር ከብቶቻችንን የምናጠጣው፡፡ በየጊዜው የሚከሰተው ድርቅም የምንበላው እያጣን በርዳታ ላይ ነበር የኖርነው፤ ዛሬ ልማታዊ መንግስታችን የከርሰ ምድር ውሃ አውጥቶ ከለማ ወዲህ ግን ወደ ልማት ገብተን ሌት ተቀን በመስራት ዛሬ በእየዓመቱ እያንዳንዱ አርሶአደር ከ50,000(ሃምሳ ሺህ) እስከ 100,000(መቶ ሺህ) ብር ድረስ እንደሚያገኙ ገልጸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ፡- 1. >የመብራት ኃይል እጥረት እንዲቀረፍላቸው > 2. >ምርቶቻቸውን በአግባቡ ለመሰብሰብ መንገድ እንዲሰራላቸው > 3. >የባቡር ሃዲድ ዝርጋታ በወረዳችን ስለሚያልፍ ምርታችንን በዘመናዊ ደረጃ እንድናቀርብ ባቡሩ የሚቆምበት ቀላል ጣቢያ እንዲሰራልንና ወደ ውጭ ከቀረጽ ነጻ የሆነ ምርት አቅርበን እንድንሸጥ የሚሉ ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡>
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄዎቹን ካዳመጡ በኋላ ሲያብራሩ በከርሰ ምድር ውሃ የበለጸገ ስለሆነ ልማቱ እየሰፋ እድል ያላገኙ አርሶአደሮችንም በማካተት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የመብራት ችግር አገር አቀፍ ቢሆንም በተቻለ መጠን ያነሳችሁትን ችግር ይፈታል፡፡ ስለባቡር ጣቢያ የተነሳው ችግር መጀመሪያ ሲታቀድ የታለፈ በመሆኑ አሁን እቅዱ እየተከለሰ ስለሆነ እናንተ በውጭ ምንዛሬ ከአገር ተርፎ ማምረት ከቻላችሁ ጣቢያው እንዲስተካከል ይሆናል፡፡ ሌሎችንም ጥራት ያለው ምርት አምርቱ በርቱ እኛም ከጎናችሁ ነን እንደግፋችኋለን እንኮራባችኋለን በማለት አበረታተዋቸዋል፡፡ |
የወልዲያ ዘመናዊ ስታዲዮም ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ተገንብቶ መመረቁ ተገለጸ በአማራ ብሄራዊ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር ወልዲያ ከተማ ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ ስታዲዮም ጠቅላይ ሚኒስተር ክቡር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በተገኙበት ጥር 06/05/2009 ዓ.ም መመረቁን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
በበዓሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ክቡር አቶ ደመቀ መኮነንና ሌሎች ሚኒስተሮች እንዲሁም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድሩና ቢሮ ኃላፊዎች፣ ከአዲስ አበባ፣ከባህር ዳር ከተማ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግስት ሠራተኞችም ተገኝተዋል፡፡ የአካባቢው ነዋሪ ህዝብም ሰንደቅ አላማውንና ልዩ ልዩ መፎክሮችን በመያዝ ተሰልፎ ወደ ስታዲዮሙ በመግባት ታድሟል፡፡ በዚህ ስታዲም በግምት ከ15,000 በላይ የሚሆን ህዝብ ተገኝቷል፡፡
ሺህ ሙሐመድ አሊ አል-አላሙዲ በወልዲያ ከተማ በሀገራችን ተወዳዳሪ የሌለው ዘመናዊ ስታዲዮም ከግማሽ ቢሊዮን በላይ ወይም 5.67 ሚሊዮን ብር የፈጀ እና ዓለም አቀፋዊ ደረጃን ጠብቆ የተሰራና አስፈላጊ የአገልግሎት መስጫዎችን ያካተተ ስታዲዮም ሲሆን የስታዲዮሙ የስፖርት ማዕከል ጠቅላላ 177,000 ሜትር ካሬ ነው፡፡ ስታዲዮሙ በአንድ ጊዜ 25,155 ተመልካቾችን ማስተናገድ የሚችሉ የፕላስቲክ ወንበሮች(መቀመጫወች) የያዘ ለወልዲያ ከተማ አስተዳደርና ለወልዲያ ህዝብ ሽማግሌዎች ያስረከቡ መሆኑን ሲገልጹ ይህ የመጀመሪያዬ እንጂ የመጨረሻዬ እንዳልሆነ ይህ ለወልዲያ ህዝብ ይገበዋል እንጂ አይበዛበትም ገና ብዙ ነገሮች ሊሰሩ የሚችሉ አሉ በማለት ሲቃ በያዘው አነጋገር በደስታ ገልጸዋል፡፡
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ይህ ዘመናዊ ስታንዳርዱን የጠበቀ ስታዲዮም ገንብተው ለወልዲያ ህዝብ በማስረከባቸው ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል፡፡ መንግስታችን ባስቀመጠው መርህ ምስጉን ባለሀብት መንግስት ሊሸፍናቸው የማይችሉትን ሀገራዊ ባለሀብት ይሸፍናሉ በተባለው መሰረት ሺህ ሙሐመድ አሊ አል-አላሙዲ መስራታቸው ያስቀመጥነው መርህ እውን እየሆነ መምጣቱን ያረጋግጣል ብለዋል፡፡ ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸውም የሰሜን ወሎ ህዝብና የወልዲያ ከተማ ህዝብ አነሳሽነት ስታዲዬሙን ለመገንባት ገንዘብ በማዋጣት ለይ እንዳሉ ሺህ ሙሐመድ አሊ አል-አላሙዲን እኔ ልጃችሁ እሰረዋለሁ ብለው ቃል በገቡት መሰረት ሠርተው በማስረከባቸውና ከምርቃቱም በመገኘታችን ታላቅ ኩራት ይገባናል ብለዋል፡፡
ቀጥለውም የሰሜን ወሎ ህዝብም ባወጣው 30 ሚሊዮን ብርና የክልላችን መንግስትም በለገሰው 50 ሚሊዮን በጠቅላላው በ90 ሚሊዮን ብር ከስታዲዮሙ ውጭ የእንግዳ ማረፊያ(ገስትሀውስ) ሌሎችንም ለስፖርት መጫዎቻ የሚያገለግል ስራዎችን ተሠርቷል ብለዋል፡፡ የሰሜን ወሎ ህዝብና የወልዲያ ከተማ ህዝብ ከመንግስት ጎን ተሰልፈው ብዙ አኩሪ ተግባር እየፈጸሙ በመሆናቸው የክልሉ መንግስትም ከጎናቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በሲቪል ሰርቪስ የለውጥ ሠራዊት ግንባታን አስመልክቶ ስልጠና መሰጡቱ ተገለጸ የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ በ10ሩ ዞኖች ላሉ ባለድርሻ አካላት በሲቪል ሰርቪስ የለውጥ ሠራዊት ግንባታ እና በሌሎች ወቅታዊ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የቪዲዮ ኮንፈረንስ ማካሄዱን ገለጸ፡፡ ኮንፈረንሱን የመሩት የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዷዓለም እና የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ገለታ ስዩም ሲሆኑ በሲቪል ሰርቪስ የለውጥ ሠራዊት ግንባታ ዙሪያ የሁሉም ዞኖች የሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት መምሪያና ጽ/ቤት ኃላፊዎች በተገኙበት ኮንፈረንሱ ሲካሄድ ይህ ኮንፈረንስ ከፌደራል እስከ ቀበሌ ያሉትን የመንግስት ሠራተኞች ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን ኮንፈረንሱ በዋናነት የመንግስት ሰራተኞች አሁን ባሉበት ስራቸው ላይ ተወያይተው ለወደፊት አቅጣጫ ለማስያዝ መሆኑን ክቡር አቶ ብናልፍ አንዷዓለም ገልጸዋል፡፡ የውይይቱ ዋና ዓላማ፡- በሁሉም የክልሉ ዞኖች የሚገኙ የተቋሙ አመራሮች በአዲስ መልክ የተቀላቀሉ በመሆናቸው በአሰራሩ ዙሪያ ግልፅነት እንዲኖራቸው እና የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ተቋም ግንባር ቀደም ሚናውን በመጫዎት በሌሎች የሲቪል ሰርቪስ ተቋማት ላይ መልካም ተፅዕኖ ማሳረፍ እንዲችል ለማድረግ መሆኑን አቶ ገለታ ስዩም ተናግረዋል፡፡ አሁን የሚነሱ የህዝብ ጥያቄዎች በአብዛኛው በሲቪል ሰርቫንቱ የሚመለሱ እንደመሆናቸው መጠን አገልግሎት ሰጭው ሰራተኛ በጥልቅ ተሀድሶው ማለፍ እንዳለበትም አቶ ገለታ ጨምረው ተናግረዋል፡፡
|