የደሴ ቲሹ ካልቸር ማዕከል ማቋቋሚያ ደንብ መውጣቱ ተገለጸ፡፡
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት 5ኛ ዙር 2ኛ አመት የስራ ዘመን ግንቦት 25 ቀን 2009 ዓ/ም ባደረገው አስራ ዘጠነኛ መደበኛ ስብሰባ የደሴ ቲሹ ካልቸር ማዕከል ማቋቋሚያ ደንብ ማውጣቱን አስታውቋል፡፡
ውይይቱ የተጀመረው ሰብሳቢው ባቀረቡት ማብራሪያ ሲሆን አማራ ክልል በተፈጥሮ ሁሉም አይነት ምርት የሚመረትበት አካባቢ ቢሆንም ከፍራፍሬ ልማት አኳያ ትልቁ ችግር የዕውቀት ማነስ፣ የአቅርቦት ችግር ንፅህናው የተረጋገጠ ችግኞችን አዘጋጅቶ ለአርሶ አደሩ ማቅረብ አለመቻሉ ሲሆን ይህንን ችግር ለመፍታት ቲሹ ካልቸር በማቋቋም ምርጥ የሆኑትን ዝርያዎች በላብራቶሪ በማባዛት ንፅህናው የተጠበቀና በአንድ ጊዜ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞችን እያባዙ ለአርሶ አደሩ ዘር የሚሸጥና ከዚህ በተጨማሪም ለዩኒቨርስቲዎች መማሪያ የሚሆን ትልቅና ራሱን የቻለ የደሴ ቲሹ ካልቸር ማዕከል ማቋቋም እንዳለበት ገልፀው የተዘጋጀው ረቂቅ ደንብም ከህግ አኳያ ተገቢውን የህግ ቅርፅ እንዲይዝ ከማድግ አንፃር በህግ አማካሪያችን ታይቶ የቀረበ ነው ብለዋል፡፡
የግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ በበኩላቸው ቲሹ ካልቸሩ በአመት ከ20 ሚሊየን በላይ ችግኝ ያባዛል ተብሎ በዕቅድ የተያዘ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ አያይዘውም ችግኝ እያባዙ መሸጥ በጣም ትልቅ ሀብት የሚገኝበት የስራ መስክ እየሆነ በመምጣቱ በፍጥነት ባለቤት ኑሮት ወደ ተግባር መግባት አለበት የሚል አቅርበዋል፡፡
ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በአሁኑ ሰዓት 82 በመቶ የሚሆነው ስራ የተጠናቀቀ ሲሆን ለሁለትና ሶስት ወራት በኋላ ወደ ስራ መግባት የሚቻልበትን ሁኔታ ለመፍጠር ቀሪ ስራዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ እየተደረገ መሆኑን ገልፀው ስራውን ለማጠናቀቅ ትልቅ ችግር የሆነው ባለቤት የሌለውና በተደራቢ ስራነት የተያዘ በመሆኑ በቀጣይ ይህ ትልቅ ፕሮጀክት ራሱን የቻለ የሚከታተለው አካል ኖሮት በበጀት አመቱ መጨረሻ አብዛኛው ስራ ተጠናቆ ስራ እንዲጀምር በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
መስተዳድር ምክር ቤቱም በቀረበው ጉዳይ ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን በማንሳት ሰፊ ውይይት ካካሔደ በኃላ የደሴ ቲሹ ካልቸር ማዕከል በተለይ አትክልትና ሆርቲ ካልቸርን በማስፋፋት ግብርና ቢሮና አካባቢ ደንና ዱር እንስሳ ጥበቃና ልማት መስሪያቤቶች ሊሰሯቸው የሚችሉትን ስራዎች በማሳካት በኩል ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ፣ ለሀገር የሚጠቅምና ክልሉን ወደተሻለ ደረጃ ሊያሸጋግር የሚችል ከፍተኛ ሀብት ማፍራት የሚችል ትልቅ ቲሹ ካልቸር በመሆኑ ራሱን የቻለ ማዕከል ሆኖ እንዲቋቋም በቀረበው ሀሳብ ላይ በመስማማት፤
ተጠሪነቱ ለግብርና ቢሮ እንዲሆንና የገቢ ምንጩን በተመለከተ በራሱ ገቢ የሚተዳደር ራሱን የቻለ ማዕከል ሆኖ ከመንግስት ድጋፍ የሚደረግለትና ከሌሎች ፍላጎት ካላቸው ወገኖች ጋር በስምምነት አብሮ እንደሚሰራ ፤
በአጠቃላይ የደሴ ቲሹ ካልቸር ማዕከል ከማንም ጥገኛ ያልሆነ ራሱን የቻለ ማዕከል ሆኖ እንዲቋቋም የመስተዳድር ምክር ቤቱ ደንብ ሆኖ እንዲወጣ ወስኗል፡፡
የጥበብ ጉዞው ለአማራ ክልል የኪነ-ጥበብ እድገት ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ፡፡ የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት 5ኛ ዙር ሁለተኛ አመት የስራ ዘመን ሚያዝያ 9 ቀን 2009 ዓ/ም ባደረገው 8ኛ አስተኳይ ስብሰባ ህያው የጥበብ ጉዞ ወደ አባይና ጣና ምድር የጉዞ መነሻ ሀሳብ ኪነ-ጥበብ ለአማራ ክልል እድገት ስለሚጠቅም ለደራሲያን ማህበር ማበረታቻ የሚሆን ከ600 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ገለጸ፡፡ መስተዳድር ምክር ቤቱም በቀረበው ሀሳብ ላይ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን በማንሳት ሠፊ ውይይት ካካሄደ በኋላ የጥበብ ጉዞው ለአማራ ክልል የኪነጥበብ እድገት ወሳኝ የሆኑ የተለያዩ የኪነ-ጥበብ ዝግጅቶችን ለማቅረብ ምቹ ሁኔታዎችን የሚፈጥርና በአጠቃላይ ለክልሉ የገጽታ ግንባታ ወሳኝ ሚና የሚጫወት በመሆኑ ለዚህ ስራ መሳካት የደራሲያን ማህበርን ማበረታታትና መደገፍ ተገቢ መሆኑን አምኖበታል፡፡ በመሆኑም ይህንን ጉዞ ለማሳካት በክልሉ መንግስት በኩል የተጠየቀው አጠቃላይ ብር 674,000 (ስድስት መቶ ሰባ አራት ሽ ብር) ድጋፍ እንዲደረግ ውሳኔውን አስተላልፏል፡፡
የዳያስፖራና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በስመ-ንብረት ዝውውር ክፍያ አፈጻጸም ባጋጠሙ ችግሮችላይ የመፍትሄ ሀሳብ መሰጠቱ ተገለጸ፡፡ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት 5ኛ ዙር ሁለተኛ አመት የስራ ዘመን ጥር 19 ቀን 2009 ዓ/ም ባካሄደው 10ኛ መደበኛ ስብሰባ በስመ-ንብረት ዝውውር ክፍያ አፈጻጸም ባጋጠሙ ችግሮች ዙሪያ ቢሮው ባቀረበው ማሻሻያ ውሳኔ መሰጠቱን አስታወቀ፡፡ ውይይቱ የተጀመረው በህግና አስተዳድር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የፍትህ ቢሮ ሀላፊ ሲሆኑ በክልሉ ቴምብር ቀረጥ አዋጅ ቁጥር 31/1991 አንቀጽ 3/12 ስር በልዩ ሁኔታ በጋብቻ በጋራ በተፈሩ ሀብትና ንብረቶች ስመ-ንብረት ዝውውር ላይ የባል/ሚስት ድርሻን የቴምብር ቀረጥ ክፍያን የማይመለከት መሆኑን የሚጠቅስ አንድ ንዑስ አንቀጽ ቢቀመጥ፣ ቋሚ ኮሚቴው አክሎም በከተማ ልማት ፣ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ የተሻረው መመሪያ ህጋዊ አሰራሩን ተከትሎ በመመሪያ ቢሻርና ከዚሁ ጋር ተያይዞም ስመ-ንብረት ዝውውር ሲፈጸም ሚስት/ባል ከራሱ ወይም ከራሱ ድርሻ ውጭሊኖር የሚችልን የንብረት ስመ-ንብረት ማጠቃለያን አጋጣሚ መንግስት ገቢ ማግኘት ስለአለበት ከድርሻውጭ ያለው ንብረት የሚከፈልበት መሆኑን በአዋጁም ሆነ በመመሪያው ተብራርቶ ቢቀመጥ የሚል የውሳኔ ሀሳብ ኮሚቴው ማቅረቡን ገልጸዋል፡፡ በዚህ መሰረት ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ ባልና ሚስት ሆነው በጋብቻ በጋራ ሀብትና ንብረት አፍርተው ቆይተው በተለያዩ ምክንያቶች የባልን ወይም የሚስትን ንብረት ድርሻ በስም ለማድረግ በስመ-ንብረት ዝውውር ወቅት የሚከፈሉ የታክስና የአገልግሎት ክፍያዎች ዝውውር ተጨማሪ ጥቅም በማያገኙበት የሃብትና ንብረት ባለቤት ሆነው በቆዩ የትዳር አጋሮች በአንዳቸው ስም ተመዝግቦ በመቆየቱ ብቻ 2% የቴምብር ቀረጥ ታክስ እና 3%ደግሞ የአገልግሎት ገቢ ከንብረቱ ጠቅላላ ዋጋ ታስቦ መከፈሉ አድሏዊና ኢ-ፍትሀዊ መሆኑና ጉዳዩም በዋናነት ጫና እየፈጠረ ያለው በሴቶች የንብረት ባለቤትነት ላይ መሆኑን ጉዳዮን የፍትህ ቢሮና ህግና አስተዳድር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ካቀረበው የውሳኔ ሀሳብ የተረዳ መሆኑን ምክር ቤቱ ማስተካከያ መደረግ እንዳለበት ተስማምቷል፡፡ በመሆኑም የሀብትና ንብረት ባለቤት ሆነው በቆዩ የትዳር አጋሮች በአንዳቸው ስም ተመዝግቦ በመቆየቱ 2% የቴምብርና ቀረጥ ታክስ እና 3%የአገልግሎት ክፍያ ከንብረቱ ጠቅላላ ዋጋ ታስቦ እንዲከፍሉ ማድረግ ፍትሃዊ ባለመሆኑ በፍችና በሞት የሚደረግ የስመ-ንብረት ዝውውር ከቀረጽ ነፃ እንዲሆን፣ከዚህ ጋር በተያያዘም፣በከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ያወጣው መመሪያ ቁጥር 4/2006 ዓ/ም አንቀጽ 14/4 በባል ወይም በሚስት ስም የተመዘገበ ንብረት ክፍፍል ሲደረግ አንደኛው ወገን የሚያጠቃልለው ሲሆን የሚከፈለው 3% የአገልግሎት ክፍያ እንዲሻር መስተዳድር ም/ቤቱ ወስኗል፡፡
የዳያስፖራና ህዝብ ግንኙነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት |
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ የተጣለበት 6ኛ ዓመት በዓል
|