File Name Size # of Hits Action
news 0.00 KB 201 Download

newsዜና መስተዳድር ምክር ቤት


የአማራ ክልል መስተዳድር ም/ቤት በክልሉ ለበርካታ ዓመታት የቆየው የጤና አገልግሎት ክፍያ መሻሻል እንደሚገባው አመለከተ።

የክልሉ መስተዳድር ም/ቤት ነሐሴ 11 ቀን 2004 ዓ.ም አራተኛ ዙር ሦስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሦስተኛ መደበኛ ስብሰባውን በካሄደበት ወቅት እንደገለፀው ላለፉት 21 ዓመታት የክልሉ የጤና አገልግሎት ክፍያ ምንም ዓይነት ማሻሻያ ሳይደረግበት ቆጥቷል። በዚህም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የጤና አገልግሎት ሽፋንና የባለሙያ ፍላጐት በቆየው የአገልግሎት ክፍያና በመግስት በጀት ብቻ መሸፈን እያደረገ መጥቷል።

ስለሆነም የጤና አገልግሎት ክፍያውን በተጠናና ተመጣጣኝ በሆነ መንገድ ማሻሻል እንደሚገባ ታምኖበታል።

በጉዳዩ  ላይ በሙያው የተሰማሩ የህክምና ባለሙያዎችና ተጠቃሚው ህብረተሠብ ሐሳብ እንዲሰጥበት የተደረገ ሲሆን በዚህም የህብረተሰቡን አቅም ግምት ውስጥ ያስገባ የጤና አገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ እንደሚያስፈልግ መተማመን ላይ መደረሱን መስተደድር ም/ቤቱ ገልጿል። የጤና አገልግሎት ክፍያው ሲሻሻል በመከላከል ላይ ያተከረውን የጤና መርህ እንደሚያጠናክርና የጤናውን አገልግሎት ተደራሽነት እንደሚያረጋግጥ ተሰምሮበታል።

ሆኖም ማሻሻያው በነፃ መታከም በሚገባቸው አካላት ላይ ተጽዕኖ እንዳይኖረው ተገቢው ጥንቃቄ እንዲደረግና ቅድሚያ ትኩረት ለሚሰጣቸው እንደ ወባ፣ ኤች. አይ.ቪ/ኤድስና የሳንባ ነቀርሳ ለመሳሰሉት በሽታዎች ክፍያ እንደማያስፈልጋቸው በመስተዳድር ም/ቤቱ በአጽንኦት ተገልጿል።

የአማራ ክልል መስተዳድር ም/ቤት ከክልሉ እስከ ወረዳ ባሉ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚገኙ አሮጌ ተሽከርካራዎችና ቁርጥራጭ ብረቶች በየአካባቢው በጨረታ ተሽጠው እንዲወገዱ ወሰነ።

የአማራ ክልል መስተዳድር ም/ቤት ነሐሴ 11 ቀን 2004 ዓ.ም ባካሄደው አራተኛ ዙር ሦስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሦስተኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ እንደተገለፀው ጉዳዩን አስመልክቶ መረጃ ከላኩ ወረዳዎች፣ ዞኖችና የክልል መ/ቤቶች ሪፖርት መረዳት እደተቻለው በአጠቃላይ በክልሉ የሚገኙት አሮጌ ተሽከርካሪዎችና ቁርጥራጭ ብረቶች በጨረታ ቢሸጡ ክልሉ ከ56 ሚሊዮን 166 ሽህ ብር በላይ ገቢ ማግኘት ይችላል።

መስተዳድር ም/ቤቱ ይህንን ውሳኔ የወሰነው እነዚህ አሮጌ ተሽከርካሪዎችና ቁርጥራጭ ብረቶች እንዲሁ ባለበት ቢቀመጡ ለአካባቢ ንፅህና ጠንቅ ከመሆናቸውም ባሻገር ለሌላ አገልግሎት መዋል ሲችሉ በቆይታ ብዛት ለበለጠ ብልሽት ስለሚዳረጉ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት እንደሆነ ተገልጿል።

ስለሆነም በየወረዳው ዞኖችና የክልል መ/ቤቶች የሚገኙ እነዚህ አሮጌ ተሽከርካሪዎችና ቁርጥራጭ ብረቶች አካባቢን ማዕከል ባደረገ ሁኔታ በጨረታ እንዲወገዱ መስተዳድር ም/ቤቱ ወስኗል። ከሚወገዱት ተሽከርካሪዎች መካከል የተሻለ አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ ካሉ አስፈላጊው ማጣራት ተደርጐ ለተለያዩ ማህበራትና ተቋማት የሚሠጡት መንገድ እንዲመቻችም ም/ቤቱ በውሳኔው ገልጿል።

የአማራ ክልል መስተዳድር ም/ቤት በክልሉ ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ የጦር መሳሪያዎች እንዲወገዱ ወሰነ።

የአማራ ክልል መስተዳድር ም/ቤት ሐምሌ 11 ቀን 2004 ዓ.ም ባካሄደው አራተኛ ዙር ሦስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛው ስብሰባው በክልሉ ምንም አይነት አገልግሎት የማይሠጡና ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ ተከማችተው የሚገኙ የጦር መሳሪያዎች በጥንቃቄ እንዲወገዱ ወስኗል።

በም/ቤቱ ስብሰባ ወቅት እንደተገለፀው  የጦር መሳሪያዎቹ ለበርካታ ዓመታት በእየአካባቢው የተከማቹ ሲሆን በየመጋዝኖች እንዲሁ መቀመጣቸው በተለያዩ ምክንያቶች ከቁጥጥር ውጭ በሆነ ምክንያት በህ/ሰቡ ላይ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ የሚል ጥርጣሬ በመኖሩና ጉዳዩም አለም አቀፋዊ ተቀባይነት ያለው በመሆኑ ውሳኔው ተወስኗል ነው።

ም/ቤቱ በውሳኔው ለአገልግሎት የሚውሉ የጦር መሳሪያዎች ካሉ ተጣርቶ ፀጥታን ሊያስከብሩ ለሚችሉ አካላት የሚተላለፉበት መንገድ እንዲመቻች እንዲሁም ከጦር መሳሪያዎች መካከል በቅርስነት የሚያገለግሉ ካሉ በክልሉ ባህል ቱሪዝምና ፖርኮች ልማት ቢሮ አማካኝነት በሙዚየም ውስጥ እንዲቀመጡ እንዲደረግ አካቷል።

የአማራ ክልል የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽንና ቴክኖሎጅ ልማት ኤጀንሲ ማቋቋሚያ ደንብ ማሻሻያ ደንብ ፀደቀ።

የአማራ ክልል ም/ቤት ነሐሴ 1 ቀን 2004 ዓ.ም ባካሄደው አራተኛ ዙር ሦስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባው ወቅት እንደተገለፀው ከዚህ ቀደም ኤጀንሲው በአስራር ላይ ይገጥሙት የነበሩትን አንዳንድ እንቅፋቶች ለማስተካከል እንዲቻል የኤጀንሲውን ማቋቋሚያ ደንብ ማሻሻል አስፈልጓል።የአማራ ክልል መስተዳድር ም/ቤት በክልሉ ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ የጦር መሳሪያዎች እንዲወገዱ ወሰነ።

የአማራ ክልል መስተዳድር ም/ቤት ሐምሌ 11 ቀን 2004 ዓ.ም ባካሄደው አራተኛ ዙር ሦስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛው ስብሰባው በክልሉ ምንም አይነት አገልግሎት የማይሠጡና ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ ተከማችተው የሚገኙ የጦር መሳሪያዎች በጥንቃቄ እንዲወረዱ ወስኗል።

በም/ቤቱ ስብሰባ ወቅት እንደተገለፀው ውሳኔው የተወሰነው የጦር መሳሪያዎቹ ለበርካታ ዓመታት በእየአካባቢው የተከማቹ ሊሆን በየመጋዝኖች እንዲሁ መቀመጣቸው በተለያዩ ምክንያቶች ከቁጥጥር ውጭ በሆነ ምክንያት በህ/ሰቡ ላይ ጉዳት ሊያደርሱ ይታላሉ የሚል ጥርጣሬ በመኖሩና ጉዳዩም አለም አቀፋዊ ተቀባይነት ያለው በመሆኑ ነው።

ም/ቤቱ በውሳኔው ለአገልግሎት የሚውሉ የጦር መሳሪያዎች ካሉ ተጣርቶ ፀጥታን ሊያስከብሩ ለሚችሉ አካላት የሚተላለፍበት መንገድ እንዲመቻች እንዲሁም ከጦር መሳሪያዎች መካከል በቅርብነት የሚያገለግሉ ካሉ በክልሉ ባህል ቱሪዝምና ፖርኮች ልማት ቢሮ አማካኝነት በሙዚየም ውስጥ እንዲቀመጡ እንዲደረግ አካቷል።

በማሻሻያ ደንቡ መሠረት ኤጀንሲው ተጠሪነቱ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሆኖ ኤጀንሲው በስሩ የክልሉን ቢዝነስ ኢንኩቤሽን ማዕከል የሚያስተዳድር ይሆናል። በተጨማሪም ለማዕከሉ መንግስት በጀት የሚመደብ ሲሆን ማዕከሉ በተለያዩ መንገዶች የሚያገኘውን ገቢ ለመንግስት ፈሰስ ያደረጋል ወይም ለማዕከሉ ማጠናከሪያነት ያውላል።

የማሻሻያ ደንቡ እንደሚያስረዳው ማዕከሉ የተለያዩ ካምፓኒዎች እንዲፈጠሩ የመመልመልና የመደገፍ ስራዎችን ይሠራል፣ ወጣቶች በስራ ፈጠራ እንዲሠማሩ የሚያስችል ስልጠና ይሠጣል ራሳቸውን በቻሉ ጊዜም ማዕከሉን ለቀው እንዲወጡ ሁኔታዎችን ያመቻቻል።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት  መስተዳድር ም/ቤት ከመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ወደ ሁለተኛ ደረጃ የሚሸጋገሩ ተማሪዎችን ዝቅተኛ የማለፊያ ነጥብ ወሠነ።

መስተዳድር ም/ቤቱ ባካሄደው አራተኛ ዙር ሶስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሁለተኛ አስቸኳይ ስብሰባው ከመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ወደ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የሚሸጋገሩ ተማሪዎችን ዝቅተኛ የማለፊያ ነጥብ የወሠነ ሲሆን በዘንድሮው ዓመት የተመዘገበው ውጤት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀርም የ8.61 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተገልጿል።

ምክር ቤቱ በክልሉ ትምህርት ቢሮ አማካኝነት በቀረበው በዚህ አጀንዳ ላይ ሠፊ ውይይት ካካሄደ በኋላ በ2004 ዓ.ም ከመጀመሪያው ደረጃ

ት/ቤት ወደ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት እርከን ለመግባት የሚያስችለው ዝቅተኛ የማለፊያ ነጥብ ለወንዶች አማካይ ውጤት 40 እና በላይ፣ ለሴቶችና ለአካል ጉዳተኞች ደግሞ አማካይ ውጤት 38 እና በላይ እንዲሆን በሙሉ ድምጽ ወስኗል።

ምክር ቤቱ የወሠነው ዝቅተኛ የማለፊያ ነጥብ በቀጣይ ጊዜ ወደ 10ኛ እና 12ኛ ክፍል የሚደርሱ ተማሪዎችን ቁጥር የሚጨምር 80 በመቶ ተፈታኝ ተማሪዎችን የሚያሳልፍ እና የተማሪ ጥምርታን 1:69 በማድረግ የተሻለ እንደሆነ ተገልጿል። ምክር ቤቱ ወደፊት ተማሪዎች የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንዲችሉ የተጀማመሩ ፈርጀ ብዙ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸውም አስምሮበታል።


< Back to previous page

LatestNews

Who is online

We have 191 guests and 2 members online