Tana high level forum of security on Africa በሚል ስያሜ በባህር ዳር ከተማ የሚካሄደው አለም አቀፍዊ ኮንፈረንስ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ሁሉም አካል ርብርብ ሊያደርግ እንደሚገባ የክልሉ መስተዳድር ም/ቤት አሳሰበ።

 

የክልሉ መስተዳድር ም/ቤት የካቲት 20/2004 ዓ.ም 4ኛዙር 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ዘጠነኛ አስቸኳይ ስብሰባውን  ባካሄደበት ወቅት እንደተገለፀው ከሚያዚያ 6-7/2004 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ Tana high level forum on security in Africa በሚል ርዕሰ አንድ አለም አቀፋዊ ኮንፈረንስ ይካሄዳል። ኮንፈረንሱ የአፍሪካ መሪዎች ችግሮቻቸውን በራሳቸው እንዲፈቱ ለማድረግ፣ በአለም ላይ ያላቸውን ተደማጭነት የበለጠ ለማሳደግና በአፍሪካ አሁን እታየ ያለውን መልካም ነገር አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችሉ ሐሳቦችና ውይይቶች የሚካሄዱበት እንደሆነም ተብራርቷል።

በኮንፈረንሱ የሀገር መሪዎች፣የግል ድርጅቶች ፣ ምሁራን ሲቪል ሶሳይትና ታዋቂ ሰዎች እንዲሁም የብራዚል፣ ህንድና ቻይና የፖለቲካ መሪዎች የሚሣተፉበት እንደሆንና ኮንፈረንሱን የቀድሞው የናይጀሪያ መሪ የነበሩት አሊሴን ጐን አባሳንጆ እንደሚመሩት የመስተዳድር ም/ቤቱ አባላት በተወያዩበት ወቅት ተገልጿል።

 

የአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ በዋናነት የሚያስተባብረውና 80 ያህል ተሳታፊዎች የሚካፈሉበት ይህ ኮንፈረንስ 10 የአሜሪካ፣15 የአለም አቀፍ የሬድዮ፣ የቴሌቪዥንና የህትመት ሚዲያዎች ተገኝተው እንደሚካፈሉበትም ታውቋል። የባህር ዳር ከተማ ህዝብ እንግዳ ተቀባይ በመሆኑ ከተማዋ በማደግ ላይ ያለች በተፈጥሮ የታደለችና በርካታ መዝናኛዎች የሚገኙባት በመሆኑና ወደፊት ከተማዋን 2ኛ የኢትዮጵያ የኮንአረንስ ማዕከል ለማድረግ በመታሠቡ ኮንፈረንሱን ለባህር ዳር ከተማ ለማካሄድ እንዳስፈለገ ተጠቁሟል።

 

በመጨረሻ መስተዳድር ም/ቤቱ በጉዳዩ ላይ ሠፊ ውይይት አካሄዶ አሁን የተፈጠረውን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ክልሉንና ባህር ዳር ከተማን መልካም ገጽታ ማስተዋወቅ እንደሚገባ፣ ለኮንፈረንሱ ዝግጅት መሳካትም መላው የከተማው ነዋሪና የመንግስት መዋቅር እጅ ለእጅ ተያይዞ ሊረባረብ እንደሚገባው አስምሮበታል።

LatestNews

Who is online

We have 309 guests and 7 members online