There are no translations available.

 

ተግባር እና ኃላፊነቶቹ

ü አስተዳደራዊ ፍትህ ፈልገው ወደ ጽህፈት ቤቱ የሚመጡትን ባለጉዳዮች ተቀብሎ ያስተናግዳል፣ ጉዳያቸውን በማጣራት ወቅታዊና አፋጣኝ ምላሽ ይሰጣል፣ ወይም በክፍሉ ደረጃ ሊፈታ የማይችል ሆኖ ሲያገኘው ተገቢው ምላሽ ይሰጥበት ዘንድ አስተያየቱን በጽሁፍ አደራጅቶ ቅሬታው ለቀረበበት አካል ወይም አግባብ ላለው የክልሉ መንግሥት መስሪያ ቤት የበላይ ኃላፊ ያስተላልፋል፤

ü የክልሉ መንግሥት ተቋማት ከሚሰጧቸው አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ ከዜጎች የሚቀርቡ ቅሬታዎችንና አቤቱታዎችን ተቀብሎ በሚመረምርበትና በሚያጣራበት ጊዜ ለሥራው አስፈላጊ የሆኑትን ኦፊሴላዊ ሰነዶችና ሌሎች ማስረጃዎች አስቀርቦ ይመለከታል፣ ያጠናል፤

ü ደረጃውን የጠበቀና ሁሉንም ያለአድልዎ ለማስተናገድ የሚያስችል የህዝብ ቅሬታዎች አቀራረብና አቀባበል ስርዓት ቀርጾ በስራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፣ ይህንኑ በተለያዩ አመቺ ዘዴዎች ለተጠቃሚው ህብረተ-ሰብ ያስተዋውቃል፤

ü ከህዝብ የሚቀርቡ የአስተዳደራዊ ፍትህ መጠየቂያ አቤቱታዎችን ዓይነት፣ ብዛትና መንስኤ በየጊዜው እያጠና የሕዝብ አቤቱታዎች በየደረጃው ባሉ የክልሉ መንግሥት አስተዳደር አካላት መፍትሄ የሚያገኙበትን መንገድ በመጠቆም ለውሳኔ ሰጪ አካላት ያቀርባል፡፡