There are no translations available.

የግብርና ጉዳዮች አማካሪ ተግባር እና ኃላፊነቶቹ

Ø የስነምህዳር ቀጠናዎችን ማዕከል ያደረገ የተቀናጀ የግብርና ኮሞዲቲ ክላስተር ልማት አተገባበርን በመከታተል እና በመገምገም የአ/አደሩ ገቢና የኑሮ ደረጃ እንዲሻሻል ተገቢውን ምክረ-ኃሳብ ያቀርባል፡፡

Ø የተፈጥሮ ኃብት ልማት፣ ጥበቃ እና አጠቃቀም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይከታተላል ይገመግማል እንዲሁም የግብርና ስርዓታችን ከተፈጥሮ ኃብት ጋር ያለውን የመጠፋፋት ችግር እንዲስተካከል በማድረግ የአካባቢ መራቆትን ለመቀነስ የሚያስችሉ አማራጭ ኃሳቦችን ያቀርባል፣

Ø በክልሉ ውስጥ የሚከናወኑ የመስኖ አውታር ግንባታ ስራዎችን ውጤታማነት በመከታተል እና በመገምገም የዘርፉ ምርታማነት እንዲያድግ ምክረ-ኃሳቦችን ያቀርባል፣

Ø በክልሉ ውስጥ ያሉትን የእንስሳት ሃብት ምርትና ምርታማነት እንዲያሳድግ የሚረዱ አማራጮች እንዲቀርቡለት እና ተጠቃሚነቱ እንዲሻሻል ይከታተላል ይገመግማል አስፈላጊውን ምክረ-ኃሳብም ይለግሳል፣

Ø የአ/አደሩ ሁለገብ ህብረት ስራ ማህበራትን እና ዩኒየኖችን በመከታተልና በማጠናከር ተቋማቱ ግብርናችንን ለማዘመን በሚደረገው ጥረት የጎላ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ተገቢ ድጋፍ እና ክትትል ያካሂዳል፣

Ø የስነ-ምህዳር ቀጠናዎችን ማዕከል ያደረገ የግብርና ምርምር ስርዓት እንዲኖር ይከታተላል ፣ይገመግማል አስፈላጊውን ድጋፍም ይሰጣል፣

Ø ከግብርና ተቋም ጋር የሚሰሩ መንግስታዊ የሆኑና ያልሆኑ ድርጅቶች ፕሮጀክቶቻቸውን በማናበብ ድግግሞሽን ለማስቀረት እና ከደሴታዊ አሰራር ወጥተው ለዋናው የግብርና ስርዓት የሚወራረስ እሴት እንዲኖራቸው ለማስቻል አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ለበላይ አመራሩ ምክረ-ኃሳቦችን ይሰጣል፣

Ø ግብርናችንን ሰፊ የስራ ዕድል መፍጠሪያ ማዕከል ለማድረግ በውጤታማነት እና እሴት ጭመራ ላይ ያተኮሩ ስራዎች እንዲሰሩ ይከታተላል ይገመግማል፣

Ø በግብርና ማሳዎች ላይ የሚስተዋለውን የመሬት ሽሚያ መልክ ለማስያዝ የስርዓተ-ግብርና የአካባቢ ዲዛይን እንዲተገበር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ ይሰራል፣

Ø የግብርና አሰራራችን ከግብዓት ማቃመስ ችግር እና ከተበጣጠሱ ማሳዎች አሰራር ደረጃ በደረጃ እየተላቀቀ ጎን በጎን የኮሜርሻል አሰራርን አጣምሮ እንዲሄድ አስፈላጊውን ግምገማ እና ክትትል ያደርጋል፣

Ø በርዕሰ መስተዳድሩ የሚሰጡትን ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፣

Ø ስራዎቹን ማዕከል አድርጎ ሪፖርት በየጊዜው አዘጋጅቶ ለርዕሰ-መስተዳድሩ ያቀርባል፣