There are no translations available.

የንግድና ፋይናንስ ጉዳዮች አማካሪ ተግባርና ኃላፊነት

Ø የክልሉ በጀት ለተመደበለት አላማ መዋሉን፣ፍትሀዊ የበጀት ማከፋፈያ ቀመር ተዘጋጅቶ መተግበሩን፣ የመንግስት የፋይናንስ አስተዳደር ስርአት ከብክነት የፀዳ መሆኑን ይከታተላል፡፡ ችግሮች በሚያጋጥሙ ጊዜ የችግር መፍቻ ዘዴዎችን በማዘጋጀት ለርዕሰ መስተዳድሩ ምክረ ሀሳብ ያቀርባል፣

Ø በመንግስት የሚፈፀሙ የአገልግሎት፣ የዕቃ እና የስራ ግዥዎች ህጉን ተከትለው መፈፀማቸውን፣ የመንግስት የግዥ መርሆዎች ሳይሸራረፉ በስራ ላይ መዋላቸውን እና ግዥዎች በተቀመጠው የጨረታ ስታንዳርድ መሰረት እየተፈፀሙ መሆናቸውን በመገምገም በሚስተዋሉ ችግሮች ዙሪያ የማሻሻ ምክረ ሀሳብ ያቀርባል፣

Ø የመንግስት በጀት ለታቀደለት አላማ እንዳይውል የሚያደርጉ አዋጆች፣ ደንቦች መመሪያዎች እና አሰራሮች በሚያጋጥሙበት ጊዜ ተገቢ የሆነ ጥናት በማድረግ ለማሻሻል የሚያስችሉ አዳዲስ የአሰራር ስርአቶችን ለርዕሰ መስተዳድሩ ያቀርባል፣

Ø አዳዲስ የኢንቨስትመንት አማራጮች ወደ ተግባር ለመለወጥ ገች የሆኑ አሰራሮች እና ወደ ስራ የገቡ ኢንቨስሮቶች የምርታማነትና የተወዳዳሪነት ችግር እና መንስኤዎችን በመለየት የማሻሻያ ሀሳብ ያቀርባል፣

Ø የክልሉ የንግድ ስርአት ጤናማ ውድድርን፣ በፍትሀዊነት ሀብት መፍጠርን፣ ከሙስና እና አድለዎ አሰራር የፀዳ ድጋፍን፣ አዳዲስ የግብይት ስርአትን፣ ተወዳዳሪነትን እና እሴት መፍጠርን መሰረት ያደረገ የአሰራር ስርአት እና አተገባበርን የተከተለ መሆኑን ለማረጋገጥ ተገቢ ክትትል ያደርጋል፣

Ø የክልሉን ገቢ ለማሳደግ እንዲቻል የገቢ መሰረቶች በዝርዝር ተጠንተው ከፍተኛ የታክስ አስተዳደር ወጭ የማይጠይቁትን እና ከፍተኛ ገቢ ማመንጨት የሚችሉትን በስራ ላይ እንዲውሉ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታን በጥናት እንዲለይ በማስደረግ ውጤቱን ለርዕሰ መስተዳድሩ ያቀርባል፣

Ø የግብር ከፋዮች ፍልሰትን ለማስቀረት እና ገቢ በተገቢው ሁኔታ እንዲሰበሰብ፣ የግብር አስተዳደር ስርአቱ የተሳለጠ እንዲሆን የገቢዎች ቢሮ ከላይ እስከ ታች ያለው አመራር እና ባለሙያ የሚያደርጉትን ጥረት በመከታተልና በመደገፍ ለችግሮች ሲያጋጥሙ የመፍትሄ ሀሳብ ለርዕሰ መስተዳድሩ ማቅረብ፣

Ø የመንግስት የልማት ድርጅቶች ከተቋቋሙበት ግብ አኳያ ተልዕኳቸውን በአግባቡ እንዳያስፈፅሙ ገች የሆኑ አሰራሮች ልምዶች እና ህጎች በየጊዜው እንዲሻሻሉ ከሚመለከተው አካል ጋር በመቀናጀት ተገቢ ጥናት ያደርጋል የመፍትሄ ሀሳብ ያቀርባል፣

Ø የኦዲት ስርአቱ የሚዘምንበትን ሁኔታ በጥናት በመመስረት ምክረ ሀሳብ ያቀርባል፣የኦዲት ግኝቶች መንስኤና የቀጣይ ስጋቶችን በዝርዝር በማጥናትና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል ስልት እንዲቀየስ የሚያስችል የመፍትሄ ሀሳብ ያቀርባል፣

Ø የክልሉ የኢንዱስትሪ ልማት እንቅስቃሴ በተፋጠነ መንገድ እንዲከናወን በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ያጠናል፣ መፍትሄ ሀሳቦችን በማደራጀት ተግባራዊ በሚሆኑበት ዙሪያ ላይ ምክረ ሀሳብ ያቀርባል፣የኢንዱስትሪ ፓርኮች ውጤታማነትን ይከታተላል፣

Ø የፋይናንስ እና የሀብት አስተዳደር እና አጠቃቀም ስርአቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ የሚሄድበትን ሁኔታ በጥናት በመለየት ከተገቢ የመፍትሄ ሀሳብ ጋር ለርዕሰ መስተዳድሩ ያቀርባል፣

Ø በየአመቱ በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ እየተዘጋጀ ለመስተዳድር ምክርቤቱ ውሳኔ በሚላከው የተጠቃለለ ፈንድ ረቂቅ ላይ ሙያዊ አስተያየቶችን ፣መግለጫዎችን እና የማሻሻያ ሀሳቦችን በማዘጋጀት ውሳኔው በሚተላለፍበት ጊዜ ከቢሮው የተለየ የማብራሪያ ሀሳብ የሚያቀርብ ከሆነ በአስረጅነት በመቅረብ ዝርዝሩን ለካብኔው ያስረዳል፣

Ø የፋይናንስ ህጋዊነትና ተጠያቂነት የኦዲት ግኝቶች ላይ ተገቢውን ትንታኔ በማድረግ ሊወሰዱ የሚገባቸውን እርምጃዎችና ለወደፊት መደረግ የሚገባቸውን የመፍትሄ ሀሳቦች በማካተት ለርዕሰ መስተዳድሩ ምክረ ሀሳብ ያቀርባል፣

Ø በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የፋይናንስ ተቋማት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችል የብድርና ቁጠባ ተግባራትን በማከናወን ላይ ስለመሆናቸው ተገቢ ጥናት በማድረግ ስለሚሻሻሉበት መንገድ ለርዕሰ መስተዳድሩ ምክረ ሀሳብ ያቀርባል፣

Ø ልዩ በጀት እና ድጋፍ ወይም የመቋቋሚያ ፈንድ እንዲደረግላቸው የሚጠይቁ ተቋማት፣ ቡድኖች እና ግለሰቦች በተመለከተ የጥያቄያቸውን ተገቢነትና ምክንያታዊነት በማጣራት የደረሰበትን ድምዳሜ ለርዕሰ መስተዳድሩ ያማክራል፣

Ø የክልሉ መንግስት የብድር ዋስትና እና የዶላር ምንዛሬ ቅድሚያ እንዲሰጣቸው የሚጠይቁ የመንግስት ተቋማት፣የግል ድርጅቶች ፣የመንግስት የልማት ድርጅቶች እና ዩኒየኖች የሚያቀርቡትን መነሻ ምክንያት በዝርዝር በማጥናት እና ተገቢ የሆኑ የህግና የአሰራ መርሆችን በማጣቀስ በተደራጀ መልኩ ለርዕሰ መስተዳድሩ ምክረ ሀሳብ ያቀርባል፣