There are no translations available.

የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ ተግባርና ኃላፊነት

Ø የክልሉን የፋይናንስ የሀብት አስተዳደርና አጠቃቀም በተመለተ እየተከታተለ ለርዕሰ-መስተዳድሩ ምክረ ሃሣብ ያቀርባል፤

Ø የክልሉን የምግብ ዋስትና ኘሮግራም ውጤታማነት ይከታተላል፣ ይገመግማል በላቀ ሁኔታ ተፈፃሚ የሚሆንበትን ምክረ ሃሣብ ይለግሳል፡፡

Ø በክልሉ ውስጥ የሚካሄደውን የአረንጓዴ ልማት ኢኮኖሚ ስትራቴጅ አተገባበር ይከታተላል፣ ይገመግማል፡፡

Ø በክልሉ ህብረተሰብ የሚከናወነውን የተፈጥሮ ሀብት ልማት ሥራ ዘላቂና ውጤታማ እንዲሆን ይከታተላል፣ ይገመግማል፤

Ø የክልሉ ወጣቶችና ሴቶች በኢኮኖሚው ተሣታፊና ተጠቃሚ የሚሆኑበት ጉዳይ ላይ በየጊዜው አማራጮችን በማጥናት የምክረ ሀሳብ ያቀርባል፡፡

Ø ክልሉ በእንሰሳት ሀብት ልማት ማግኘት የሚገባወን የላቀ ጥቅም እንዲያገኝ በትኩረት ይሰራል፡፡

Ø የክልሉ ከተሞች ልማት ዕድገት የተፋጠነ እንዲሆን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተገናኘ ይገመግማል፣ አዳዲስ ሃሳቦችንና ሥልቶችን በመቀየስ ተግባራዊ በሚሆኑበት አግባብ ላይ የምክር ሀሳብ ያቀርባል፡፡

Ø የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት እንቅስቃሴ በተፋጠነ መንግድ እንዲከናወን በየጊዜው በዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ያጠናል፣ የመፍትሔ ሃሳቦችን በማደራጀት ተግባሪዊ በሚሆኑበት ዙሪያ ላይ የምክር ሃሳብ ያቀርባል፡፡

Ø የክልሉ ግብይት ስርዓት ጤናማና ውጤታማ እንዲሆን ተገቢውን ክትትል ያደርጋል፣ የህብረት ስራ ማህበራት እድገትን የሚያቀጭጩ ጉዳዮችን በመለየት ተገቢውን ትግል እንዲደረግባቸው ያደርጋል፡፡

Ø የክልሉ ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋና ለዚህ እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮችን እየለዩ ተገቢው አመራር እንዲሰጥባቸው ይደግፋል፡፡

Ø የክልሉ ገቢ እንዲያድግና በዘርፉ የሚስተዋለው ኪራይ ሰብሳቢነት ትግል የሚደረግበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣ በዚህ ዙሪያ ወደ ርዕሰ-መስተዳድሩ የሚመጡ ባለጉዳዮችን ተቀብሎ በማነጋገር መፍትሔ ያሰጣል፡፡

Ø ወደ ክልሉ መንግስት የተለያዩ ቢሮዎች የሚላከውን የፌዴራል መንግስትና የረጅ ድርጅቶች ፋይናንስ አፈፃፀም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ አስፈላጊው የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ የተደራጀ የውሣኔ ሃሣብ ለርዕሰ-መስተደድሩ ያቀርባል፡፡

Ø ልዩ የበጀት ድጋፍ፣ የፋይናንስ ድጐማ ወይም የማቋቋማያ ፈንድ እንዲደረግላቸው የሚጠየቁ ተቋማት፣ ቡድኖች ወይም ግለሰቦች ጉዳይ ሲመራለት የጥያቄውን ተገቢነት በማጣራት በመረጃ ላይ የተደገፉ የውሳኔ አስተያየቱን ለርዕሰ-መስተደድሩ ያቀርባል፡፡

Ø የክልሉ ዋና ኦዲተር /ቤት በሚያካሂዳቸው የሂሳብና የክዋኔ ኦዲት ምርመራዎች ዙሪያ የተስተዋሉ ጉድለቶችንና ግኝቶችን ተቀብሎ በኦዲት ሪፖርቱ አስተያየት መሰረት አግባባነት ያለው እርምጃ እንዲወሰዱ ለርዕሰ-መስተዳድሩ የውሣኔ ሃሣብ አደራጅቶ ያቀርባል አፈፃፀሙንም ይከታተላል፡፡

Ø በርዕሰ-መስተዳድሩ የሚሰጡ ተዛማጅ ሥራዎችን ያከናውናል፡፡

Ø ተጠሪነቱም ለርዕሰ-መስተዳድሩ ሆኖ በየጊዜው የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀርባል፡፡