ህግዳ : 15/12/2012 . በቡሬ ከተማ 991 ነጥብ 2 ሚሊዬን ብር በሚበልጥ ወጭ የተገነባ ግዙፍ የዘይት ፍብሪካ የሙከራ ምርት በመጀመሩ መደሰታቸውን አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለጡ

የዐማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር የተከበሩት አቶ ተመስገን ጥሩነህ በግል ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ትላንት እንደገለጡት በቡሬ ከተማ የተገነባ ግዙፍ የዘይት ፍብሪካ የሙከራ ምርት በመጀመሩ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በማስተላለፍ መደሰታቸውን ገልጠዋል

በቡሬ ኢንዱስትሪ ፖርክ 991 ሚሊዬን 242 ሺህ ብር "ሪችላንድ" በሚል ስያሜ ከተገነቡ ሶስቱ ግዙፍ ዘይት ፋብሪካዎች አንዱ የሙከራ ምርት ጀምሯል ሲሉ አቶ ተመስገን አብስረዋል

ፍብሪካው በዓመት አንድ ሚሊዬን አምስት መቶ ሺህ ኩንታል አኩሪ አተር ስለሚያስፈልገው ጥምር ጠቀሜታ እንዳለው ርዕሰ መስተዳደሩ ገልጠዋል

ከአገር ውስጥ አልፎ ምርቱን ለውጭ አገር ገበያ በማቅረብም ቀዓመት 61 ሚሊዬን 680 ሺህ ዶላር የውጭ ምንዛሬ እንደሚያስገኝ ጠቁመዋል

ፍብሪካው 22 ሚሊዬን 500 ሺህ ሊትር ዘይት ለአገር ውስጥ ፍጆታ እንደሚያቀርብ አስታውቀዋል

የፍብሪካውን ባለቤት አቶ ሙላቱን ባለ ብዙ ራዕዩ ባለኃብት ሲሉ የገለጡት አቶ ተመስገን ለባለኃብቱ እና መላው የፋብሪካው ሰራተኞች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል ::

ይህን ፍብሪካ በአቶ ተመስገን የተመራ ከፍተኛ ልዑካን ቡድን በቅርቡ ጎብኝቶት እንደነበር ይታወሳል

LatestNews

Who is online

We have 156 guests and 1 member online