ህግዳ : 26/11/2012 . በዐማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን 257 ሚሊዬን ብር በሚበልጥ ወጭ የተገነቡ የልማት ተቋማትን የመመምረቅና የጉብኝት ስራ መካሄዱ ተገለጠ

ከተመረቁት ተቋማት መካከል የመተማ ከተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ማስፋፊያ ግንባታ እና የደም ባንክ ማዕከል ይገኙበታል

ተቋማቱን የመረቁት የዐማራ ክልል ርዕሰ መሰተዳድር የተከበሩ አቶ ተመስገን ጥሩነህ በርሳቸው የተመራው ከፍተኛ የክልሉ አመራሮችን ያካተተው ልዑክ እና በልዩ ሁኔታ ተጋባዥ የሆኑ በገዳማት የማኖሩ የኃይማኖት አባቶች በተገኙበት ነው

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አደባባይ ሙሉጌታ አንደገለጡት 257 ሚሊዬን ብር በሚበልጥ ወጭ የተገነቡ የቋራና አብርሃ ጅራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎችም ተጠናቀዋል

ሁለት 2 ደረጃ እና አራት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ሌሎች የልማት ተቋማትም መጠናቀ ቃቸውን አቶ አደባባይ ተናግረዋል

ከተጠቀሱት በተጨማሪ በመንግስት ከአንድ ነጥብ ስድስት ቢሊዬን ብር በሚበልጥ ወጭ በመገምባት ላይ የሚገኘው የቋራ ገለጎ አብርሃ ጅራ ገንዳ ውኃ የአስፓልት መንገድ እንዲፋጠንም አስተዳዳሪው አሳስበዋል

የክልሉ /ቤት አፈ -ጉበዔ / ወርቅሰሙ ማሞ ፣ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ ዶክተር ፈንታ ማንደፍሮ የክልሉ ብልፅግና ፖርቲ /ቤት ኃላፊ አቶ አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና በክልሉ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የተወጣጡ ሙሁራን በምረቃው ላይ ታድመዋል

ታዳሚዎቹ በአካባቢው በጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል አማካኝነት የአኩሪ አተር ሰብልን በአዲስ ለማላመድና የሰሊጥን ምርታማነት በሄክታር የሚገኘውን 3 ኩንታል ምርትን ወደ 10 ኩንታል ለማሳደግ 100 ሄክታር በሚበልጥ መሬት ላይ የሚካሄደውን የዘር ብዜት እንቅስቃሴም ጎብኝተዋል

ይህ ጥረት አበረታች ቢሆንም ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ለበለጠ ስኬት ማዕከሉ መስራት እንዳለበት ምክረ - ሀሳብ ተሰጥቶታል

አቶ ተመስገን ባስተላለፉት መልዕክት ለሁሉ ነገር መሰረት ለሆነው ለጋራ ሰላም እና የህግ የበላይነትን የማስከበር ስራ ትኩረት መስጠት ይገባል

በአካባቢው ተፈጥሮ የነበረውን የእርስ በእርስ ግጭት ለማርገብ ልዩ አስተዋፆ ለበረከቱት የማህበረ ስላሴ እና የጣራ ገዳም አባቶች እንዲሁም ለእንግዶች የዕውቅና መታሰቢያ ስጦታ ተበረክቷል

LatestNews

Who is online

We have 202 guests and 1 member online