ህግዳ : 23/11/2012 . በዐማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን በአንድ ቢሊዬን 711 ሚሊዮን 358 ሺህ 881 ብር ወጪ ግምባታቸው የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ሲመረቁ በግንባታ ላይ ያሉት ደግም ተጎበኙ፡፡

በዐማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የተከበሩ አቶ ተመስገን ጥሩነህ የተመራው የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን ያከተተው ልዑክ በአንዳቤት ወረዳ 100 ሚሊዬን ብር በሚበልጥ ወጭ የተገነቡ የልማት ተቋማትን ዛሬ መርቋል

ከተመረቁት መካከል የአንዳቤት ከተማን ጨምሮዲዲግመኝ ወፍጫሜ እና ደረባ ቤትአንሳ በተባሉ የገጠር ቀበሌዎች የሚገኙ 19 ሺህ 300 አባዎራዎችን ተጠቃሚ ያደረገው የንፁህ መጠጥ ውኃ ግምባታ ይገኝበታል

የአንዳቤት ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልም የተመረቀ ሲሆን ለአጎራባቹ የሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ህዝብም ሊያገለግል አንደሚችል ተጠቁሟል

በዚሁ ወረዳ በግምባታ ላይ የሚገኘው "የጎኖ " ጤና ጣቢያ ማስፋፊያም ተጎብኝተዋል

የልማት ተቋማቱን የመረቁት አቶ ተመስገን ጥሩነህ ባስተላለፉት መልዕክት ህዝቡ ለሰላሙ ዘብ እንዲቆም እና ለዓባይ ግድብ ቀሪ ስራ ቦንድ በመግዛት የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል

ነዋሪዎቹ የመብራት ፣የባንክና ወረዳውን ከምስራቅ ጎጃም ዞን አገናኝቶ በአቋራጭ ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ የሚያስችለው ዓባይ በረሃን የሚያቋርጠው የአስፖልት መንገድ ስራም እንዲፍጠንላቸው ጠይቀዋል

ጥያቄዎቹን ከፌደራል፣ ከዞን እና ወረዳው ጋር በመነጋገር ምላሽ እንሰጣለን ሲሉ አቶ ተመስገን አስታውቀዋል

ልዑኩ በነዋሪዎቹ የይፍጠንልን ጥያቄ የቀረበበትን ከሞጣ-ጃራገዶ በአንድ ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር እየተገነባ ያለውን የኮንክሪት አስፓልት መንገድም ጎብኝቷል

ግምባታው 58 በመቶ ግንባታው መጠናቀቁና ግንባተውን እያከናወነ ያለው የቻይናው ኢንጅነሪንግ ግሩፕ ተወካይ በሰጡት ማብራሪያ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በመልካም አፈጻጸም ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

መንገዱ በዓባይ ወንዝ ላይ 220 ሜትር ርዝመት ያለው ድልድይ እንደሚገነባለትም ተጠቁሟል፡፡

መንገዱ አካባቢው ትርፍ አምራች በመሆኑ ሲጠናቀቅቆ የተሻለ የንግድ ትስስር ይፈጥራልም ተብሏል

በዚሁ የምረቃና ጉብኝት ፕሮግራም የክልሉ /ቤት አፈ - ጉባዔ ክብርት ወርቅሰሙ ማሞ የከልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ፈንታ ማንደፍሮ የዐማራ ብልፅግና ፖርቲ /ቤት ኃላፊ አቶ አገኘሁ ተሻገርና ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል

ተሳታፊዎቹ ችግኝ በመትከል የአረንጓዴ አሻራቸውንም
እንዳሰረፉ ታውቋል

 

LatestNews

Who is online

We have 205 guests online