ህግዳ : 22/11/2012 . የዐማራ ክልል /ቤት በጀትና ሹመቶችን በማፅደቅ መጠናቀቁ ተገለጠ

ለሁለት ቀናት በባህርዳር ከተማ የተካሄደው የም/ቤቱ 5 ዙር 5 ዓመት 16 መደበኛ ጉባዔ የክልሉ 2013 በጀት 62 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር እንዲሆን የቀረበለትን አፅድቋል።

ከፀደቀው በጀት 24 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብሩ ከክልሉ የሚሰበሰብ፣ 38 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብሩ ከማዕከላዊ መንግስት ድጋፍ እና ዜሮ ነጥብ 2 ቢሊዮን ብሩ ደግሞ ከውጭ ዕርዳታ የሚገኝ መሆኑ ታውቋል።

2013 በጀት ካምናው ጋር ሲነጻጸር 15 ነጥብ 3 ቢሊዮን (32.4 ከመቶ) እና የማዕከላዊ መንግስት የሰጠው በጀትም እንዲሁ 23 በመቶ ጭማሪ አለው

ምንም እንኳን በጀቱ ጭማሪ ቢኖረውም የሳንባ ቆልፍ (ኮሮና ቫረስ ወረርሽኝን) ለመቋቋም ከሚያስፈገው አንጻር ሲታይ ግን በቂ አለመሆኑን የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ጥላሁን መሃሪ ለም/ቤቱ ተናግዋል።

ጉባዔው በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የተከበሩ አቶ ተመስገን ጥሩነህ አቅራቢነት ለክልሉ ቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊነት በእጩነት የቀረቡትን የአቶ አረጋ ከበደ ለጋስን ሹመትም በአንድ ድሞፀ -ታቅቦ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።

አቶ አረጋ የመጀመሪያ ድግሪያቸውን በልማት አስተዳደር እና ሁለተኛ ድግሪያቸውን ደግሞ በንግድ ስራ አመራር በከፍተኛ ማዕረግ እንዳጠናቀቁ በቀረበው ግለ- ታሪካቸው ላይ ተመልክቷል።

ምክር ቤቱ ከዚህ በተጨማሪም ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኝነት የቀረቡትን 14 ዳኞች ሹመትም በአንድ ተቃውሞ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል

የአራት ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት የቀረቡትን እና 166 አዲስ የወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመት በሙሉ ድምጽ አፅድቋል

ተሿሚዎችን በም/ ቤቱ ፊት ቃለ- መሃላ እንዲፈፅሙ በማድረግ ምቤቱ የሁለት ቀናት ቆይታውን በሰላም አጠናቋል

LatestNews

Who is online

We have 128 guests and 4 members online