የታላቁ ኢትዮጵያ ኤሌክሪክ ኃይል ማመንጫ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እስኪጠናቀቅ ድረስ ድጋፍ እንደሚያደርጉ የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ሠራተኞች ተናገሩ፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ሠራተኞች የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ የተጣለበትን 7 ዓመት ምክንያት በማድረግ "ታላቁ የህዳሴ ግድባችን የሃገራችን ህብረ-ዜማ፣ የህዳሴያችን ማማ" በሚል መሪ መልዕክት በፖናል ውይይት አክብረዋል፡፡

በርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የዳያሥፖራና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አውላቸው ማስሬ የፓናል መወያያ ሰነዱን ሲያቀርቡ በሀገራችን 1983 . በፊት 370 ሜጋ ዋት የነበረው ኃይል አቅርቦት ወደ 4260 ሜጋ ዋት ኃይል በማመንጨት ሽፋኑን 21 በመቶ ወደ 60 በመቶ ማሳደግ እንደተቻለ ገልጸው የህዳሴው ግድብ ግንባታ ሲጠናቀቅም የኃይል አቅርቦቱን ወደ 90 በመቶ ከፍ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

አቶ አውላቸው አክለውም የክልሉ ህዝብ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ከተጣለበት ጊዜ ጀምሮ በቀጥታ ቦንድ ግዥና ስጦታ እስካሁን ከአንድ ቢሊዮን 130 ሚሊዮን 821 ሺህ 428 ብር በላይ የገንዘብ አስተዋጽኦ ማድረግ መቻሉን ገልጸው በልዩ ልዩ የገቢ ማስገኛ ፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞች 27 ሚሊዮን 550 ሺህ ብር ድጋፍ ማድረጉን አስገንዝበዋል፡፡


የውይይት መድረኩን የመሩት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ያየህ አዲስ በበኩላቸው የጽ/ቤቱ ሰራተኞች በወር ደመወዛቸው ቦንድ በመግዛት ድጋፍ ሲያደርጉ እንደቆዩ ተናግረው የጽ/ቤቱ ሰራተኞች እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ለህዳሴው ግድብ ያላቸውን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል፡፡

ከውይይት ተሳታፊዎች መካከል አቶ ዳኘ ጌታሁን፣አቶ አንዳርጌ ማዓዛና አቶ ዮሐንስ ታመነ ከዚህ በፊት ለግድቡ ግንባታ ከደሞዛቸው ቦንድ በመግዛት ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸው ቀጣይም የግድቡ ግንባታ እስኪጠናቀቅ ድረስ አቅማቸው የፈቀደውን ድጋፍ በማድረግ ለግድቡ ግንባታ የዜግነት ግዴታቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል፡፡

መጋቢት 24/2010 ዓ.ም

የዳያስፖራና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት

LatestNews

Who is online

We have 151 guests and 1 member online