የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ለዞንና ወራዳ የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ኃላፊዎችና ትምህርት ስልጠና ሱፐርቪዥን ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱ ተገለጸ፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የህዝብ ቅሬታ ሰሚ 56 ለሚሆኑ ለዞንና ወራዳ ቅሬታ ሰሚ ኃላፊዎችና ትምህርት ስልጠና ሱፐርቪዥን ባለሙያዎች በማህበራዊ ተጠቃሚነት አሃዝ ካርድ አሰራር ተሞክሮ፣ በዳሰሳ ጥናት አሰራርና መረጃ አሰባሰብ ጽንሰ ሃሳብ ዙሪያ ከመጋቢት 16-18/2010 ዓ.ም በደብረ ታቦር ከተማ ስልጠና መስጠቱን አስታወቀ፡፡

የክልሉ ህዝብ ቅሬታ ሰሚ ኃላፊ አቶ ሰይድ እሸቴ እንደተናገሩት የስልጠናው ዋና ዓላማ በማህበራዊ ተጠቃሚነት አሃዝ ካርድ አሰራር ተሞክሮ፣ በዳሰሳ ጥናት አሰራርና መረጃ አሰባሰብ ጽንሰ ሃሳብ ዙሪያ ግልጽ ግንዛቤ ተፈጥሮ በየተቋማቱ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን ያስችላል ብለዋል፡፡፡

በዋናነት በስልጠናው ትኩረት ከተሰጠባቸው ርዕሰ ጉዳዮች መካከል የዳሰሳ ጥናት አሰራርና መረጃ አሰባሰብ ጽንሰ ሃሳብ፣ የጥናት ዓይነቶችና የመረጃ አሠባሰብ ስልቶች፣ አሁን በተግባር እየተሰራ ያለው ጥናትና ውጤቱ በሚሉት ጉዳዮች ላይ ለተሳታፊዎቹ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት የተሰጠ ሲሆን ከባህር ዳር ዩኒቨርስቲ በመጡ ሙህራኖች የመረጃ አጠነቃቀር ስልቶችን "IBM" ወይም ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ማሽን በተባለ ሶፍትዌር ፕሮግራም የተግባር ልምምድ ትምህርት ለሠልጣኞቹ ተሰጥቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በማህበራዊ ተጠያቂነት አሃዝ ካርድ አሠራር የተመረጡ ወረዳዎች ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን፣ በክልሉ በኩል ደግሞ የተዘጋጀ መስክ ምልከታ ግብረ መልስ እና ተሞክሮዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

ከስልጠናው ተሳታፊዎች መካከል ከሰሜን ወሎ ዞን ጉባ ላፍቶ ወረዳ ወ/ሮ ገነት እና ከምዕራብ ጎጃም ዞን ጃቢጠናን ወረዳ አቶ ስንታየሁ ስልጠናውን አስመልክተው አስተያየት ሲሰጡ ከስልጠናው በቂ ትምህርት ማግኘታቸውን ጠቅሰው የተማሩትን ትምህርት ተግባራዊ በማድረግ ለሌሎች ማስተማር እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

መጋቢት 19/2010 ዓ.ም

የዳያስፖራና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት

LatestNews

Who is online

We have 154 guests and 2 members online