በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተደራጀው አብይ ኮሚቴ በTana High Level Forum ስብሰባ ቅድመ ዝግጅት ላይ ለ3ኛ ጊዜ ውይይት አካሔደ፡፡

በባህር ዳር ከተማ ለ7ኛ ጊዜ በሚካሔደው የTana High Level Forum ስብሰባ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ ሁሉም የኮሚቴ አባላት በተገኙበት የተካሔደ ሲሆን ስብሰባውን የመሩትም የፎረሙ አብይ ኮሚቴ ም/ሰብሳቢ የሆኑት የአብክመ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ንጉሱ ጥላሁን ናቸው፡፡

በዚህ ውይይትም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሰላምና ደህንነት ጥናት ተቋም (IPSS) የማኔጅመንት አባላት፣ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር፣ የፀጥታ መዋቅሩና ሌሎች ሴክተር መስሪያ ቤቶች ተሳትፈዋል፡፡ እንግዶችን በአግባቡ ለመቀበል የተደረጉ ቅድመ ዝግጅቶች፣ የከተማዋን ፅዳትና ውበት ለማሻሻል እየተሰሩ ያሉ ስራዎች፣ እንግዶች የሚያርፉባቸው ሆቴሎች ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ስለሚሰጡበት ሁኔታና የከተማዋን አጠቃላይ የቱሪዝም ፍሰት ለማሳደግ በሚሰሩ ስራዎች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡ ከሚያዝያ 13-14/2010 ዓ.ም የሚካሔደውን ስብሰባ ካለፉት አመታት በተሻለ መንገድ ለማካሔድ የክልሉ መንግስትና ህዝብ ተቀናጅተው እንደሚሰሩ የአብይ ኮሚቴው ም/ሰብሳቢ አብራርተዋል፡፡

LatestNews

Who is online

We have 147 guests and 2 members online