የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ለተለያዩ የዞን የከተማና የወረዳ አመራሮችና ባለሙያዎች የስራ ስልጠና መሰጠቱ ተገለጸ፤

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ለ153 ለተለያዩ የዞን የከተማና የወረዳ የህዝብ ቅሬታ ሰሚ አመራሮችና ባለሙያዎች ከየካቲት 29/2010 ዓ.ም እስከ መጋቢት 2/2010 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ከተማ ስልጠና መስጠቱን አስታወቀ፡፡

የስልጠናው ዓላማ በአዲሱ አመዳደብ የተነሳ ሰልጣኙ በብዛት በአዲስ ምደባ የመጣ ስለሆነ የህዝብን ቅሬታ በአግባቡ አጣርቶ ለደንበኞቻችን ተገቢና ግልጽ የሆነ አሰራር ተከትሎ በአጭር ጊዜ ውስጥ ርዕቱና ተገቢ የሆነ ውሳኔ እንዲሰጥ ታስቦ ነው፡፡

በስልጠናው የቀረቡት ጽንሰ ሀሳቦች ስምንቱ የመልካም አስተዳደር መርሆዎች በደንብ ቁጥር 130/2007 በተካተቱት የምርመራ ማጣራት ስርዓቶችና በማህበራዊ ተጠያቂነት አሀዝ ካርድ አሰራር ዙሪያ አስመልክቶ ዘርዘር ያለ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

የክልሉ የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሰይድ እሸቴ እንዳሉት በዚህ ተከታታይ ሶስት ቀን ውስጥ የተሰጣችሁን የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ወደየስራ ቦታችሁ ተመልሳችሁ ወደ ስራ ስትገቡ በርካታ የህዝብ ቅሬታ በየወረዳዎች ስላሉ ደንበኞቻችንን ባግባቡ በመቀበል በግልጽነት፣ በተጠያቂነት፣ በቅልጥፍናና ፍትሀዊ በሆነ አሰራር ማስተናገድ አለባችሁ በሚል አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል፡፡

በስልጠናው ወቅት አስተያየት ከሰጡት ተሳታፊዎች መካከልም አቶ አማኑኤል ይትባረክ ከጎንደር ከተማ የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ኃላፊ ወ/ሮ የሽእመቤት ይላቅ ከምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ከተማ የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ኃላፊ የሆኑት እንደተናገሩት የተሰጠን ስልጠና አቅም የፈጠረልንና የማናውቃቸውን ህጎችና ደንቦች እንዲሁም መመሪያዎችን በሚገባ ስለጨበጥን ወደየ አካባቢያችን ተመልሰን ህዝባችንን ለማገልገል ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡

መጋቢት 03/2010 ዓ.ም

የዳያስፖራና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት

LatestNews

Who is online

We have 184 guests and 1 member online