አዋጅ ቁጥር ------/2003 ዓ.ም

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአስፈፃሚ አካላት እንደገና ማቋቋሚያና ሥልጣንና ተግባራት መወሰኛ አዋጅ።

በአገር አቀፍ ደረጃ የተቀረፀውን የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በማሣካቱ ረገድ ክልላችን የሚኖረውን ድርሻ በአይነትም ሆነ በመጠን ከፍ ለማድረግና የህዝቡን የላቀ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ በልማታዊና ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ የተቃኘ የመንግሥት አደረጃጀት ፈጥሮ ወደ ሥራ መግባት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

ይህንኑ ታሣቢ በማድረግ ተያያዥነት ያላቸውን የሥራ ሂደቶች እያሠባሠቡ በአንድ አስፈፃሚ አካል ሥር ከማጠቃለል ጐን ለጐን ዓላማ አስፈፃሚ መሥሪያቤቶች ለልማቱ መፋጠን ባላቸው ተጨባጭ ፋይዳ ላይ በመመሥረት አበይት የትኩረት መስኮቻቸውን ከወዲሁ ለይተው ይበልጥ በእነዚሁ ላይ እንዲረባረቡና ለውጤታማ አፈፃፀም እንዲተጉ የሚያችላቸውን ህጋዊ ሁኔታ ማመቻቸት ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ፤

ከነዚሁ ቁልፍ መርሆዎች በመነሣትና ክልሉ እስከ አሁን ድረስ ባካሄደው መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ጥናት ውጤትና ትግበራው ወቅት የተገኙተን በጐ ልምዶችና የታዩትን ፈርጀ ብዙ ዝንባሌዎች ግምት ውስጥ በማስገባት ከየተቋቋሙበት ተልዕኮ ጋር የተገናዘበ የተግባርና ኃላፊነት ሽግሽግም ሆነ የተጠሪነት ለውጥ ሊደረግባቸው የሚገቡትን አስፈፃሚ አካላት በውል ለይቶና ሁኔታው በፈቀደ መጠን አደረጃጀታቸውን ከፌዴራሉ መንግሥት አወቃቀር ጋር አጣጥሞ በግልፅ መደንገግና ባልተጋነነ ወጭ እርስ በርስ የሚደጋገፉበትን የተሣለጠ አሠራር ማሥፈን እንደሚገባ በመታመኑ፤

የአማራ ክልል /ቤት በተሻሻለው የብሔራዊ ክልሉ ህገ-መንግስት አንቀጽ 49 ንዑስ አንቀፅ 3(1) ድንጋጌ ሥር በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን አዋጅ አውጥቷል።

ይቀጥላል

koga deneb

Head of Gevernemt 2003