የጤና ኮሌጅ ተማሪዎች የኪስ ገንዘብ ክፍያ መሻሻሉ ተገለፀ

E-mail Print PDF

የጤና ኮሌጅ ተማሪዎች የኪስ ገንዘብ ክፍያ መሻሻሉ ተገለፀ

የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት 4ኛ ዙር አምሰተ የሥሪ ዘመን አራተኛ መደበኛ ስብሰባ መስከረም 9 ቀን 2007 ዓ/ም ባካሄደው ስብሰባ የጤና ኮሌጅ ተማሪች የኪስ ገንዘብ ክፍያ 240/ሁለት መቶ አርባ / ወደ ብር 360.00/ሦስት መቶ ስለሳ ብር/ እንዲሻሻል መፍቀዱን አስታወቀ።

ውይይቱ የተጀመረው የጤና ቢሮው ባቀረበው ማብራሪያ ሲሆን በማብራሪያቸውም በክልሉ የሚገኙ ኮሌጆች የሚቀበሏቸው አብዛኞቹ ተማሪዎች በክልሉ ገጠራማ አካባቢ ተመልምለው የሚመጡ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በኮሌጆች የማደሪያ፣ የቀለብና የኪስ ገንዘብ ክፍያው ካለው የኑሮ ውድነት  አንፃር የማይጣጣም በመሆኑ የመማር ማስተማሩ ሂደት እንቅፋት እያጋጠመው በመገኘቱ በተለይም ደግሞ ወደ ግብርና እና መምህራን ትምህርት ኮሌጆች ለስልጠና የሚገቡ ሰልጣኞች ወርሐዊ የኪስ ገንዘብ ብር360.00/ሦስት መቶ ስለሳ ብር/ እያገኙ በመሆኑ ወደ ጤና ኮሌጅ የሚገቡ ሠልጣኞች ለእኛም ይህ የክፍያ መጠን ሊፈቀድልን ይገባል በሚል ቅሬታ ማቅረባቸውን ገልፀው፣ ቅሬታው በቢሮውና በስልጠናው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ በማሳደሩ በተጨማሪም በፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በኩል በልዩ ልዩ ኘሮግራሞች እጥረት ያለባቸውን ሙያዎች ለማሟላት ሲባል በበጀት ተደግፈው የተሻለ የኪስ ገንዘብ ክፍያ እያገኙ የሚማሩ ተማሪዎች በመኖራቸው በአንድ ኮሌጅ ውስጥ እየተማሩ የአከፋፈል ልዩነት መኖሩ ከፍተኛ ቅሬታ እንዲያስነሳ እያደረጋቸው ትልቅ የመልካም አስተዳደርና የትምህርት ጥራት ችግር እየፈጠረ በመሆኑ መስተዳድር ምክር ቤቱ የችግሩን አሳሳቢነት ተገንዝቦ እንደ ግብርና እና መምህራን ትምህርት ኮሌጆች ሠልጣኞች ክፍያ ከ240/ሁለት መቶ አርባ/ ወደ 360.00/ሶስት መቶ ስልሳ ብር/ተሻሽሎ እንዲፈቀድ ጠይቀዋል፡፡

 

መስተዳድር ምክር ቤቱም በጉዳዩ ላይ አጽንኦት ሰጥቶ ከተወያየ በኋላ በክልሉ በጤና ኮሌጆች በውል ግዴታ የሚማሩ ተማሪዎች የኪስ ገንዘብን በተመለከተ ጥያቄው ተገቢ መሆኑን በመስማማት ለትምህርት ቢሮና ግብርና ቢሮ ተማሪዎች የሚከፈለው በወር ብር 360 /ሦስት መቶ ስልሳ ብር/ እንዲከፈላቸው ወስኗል።

 
Content View Hits : 9427730

Comments

  • Hi there, just ƅecame aware of your blog through G...
  • Chatrabate does not work, I invite you to my login...
  • Write mоre, tһats all I have to say. Literally, іt...
  • Hi there, just ƅecame aware of your blog through G...
  • Write mоre, tһats all I have to say. Literally, іt...

Latest News

Who is online

We have 149 guests and 13 members online

Entertainment