የአብክመ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ሠራተኞች ታላቁን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ጐበኙ

የሀገራችን የኢኮኖሚ ምሰሶና የአንድነት መገለጫ የሆነውን ታላቁ የህዳሴ ግድብ ታህሳስ 13/2006 ዓ.ም በአካል ተገኝቶ መጐብኘት ትልቅ ሀሴት እንደፈጠረባቸው ጎብኝዎች ገልፀዋል።

6,000 ሜጋ ዋት የሚያመነጨው፤ በእኛው ባለሙያ እና በእኛው ፋይናንስ የተጀመረው ይህ ግድብ አሁን ከ30 በመቶ በላይ የግንባታው ደረጃ መድረሱ ከፍተኛ ተስፋን ጭሯል። በተለይም ይህንን ታላቅ ሰናይ ተግባር የጽ/ቤቱ ሠራተኞች በሞራል እና በፋይናንስ እየደገፋ መሆናቸው ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።

የግድቡ መሠረት ከተጣለበት ጊዜ አንስቶም ሁለት ጊዜ የወር ደመወዝ በማዋጣት አጋርነታቸውን አረጋግጠው እየቀጠሉ ይገኛሉ። በጉብኝቱ ወቅትም ይህም ድጋፍ የግድቡ ግንባታ ተጠናቆ ፍሬ እስክናይ ድረስ ይቀጥላል ሲሉ አክለው ገልፀዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ ይህ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ሃይል ግንባታ የአፋሪካ እና የአለም ሀገራትን ያስደመመ እና ምናልባትም ኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በኋላ ቀርነት ታሪክ የምትገለገልበት ትልቅ በር ነው ሲሉ የተለያዩ አካሎች ሲገልፁ ይሰማሉ።

ጐብኝዎች በከፊል

ይህ ታላቅ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ኃይል ግንባታ ኢትዮጵያ ያላገኘችውን የወደብ እና የነዳጅ ሀብት ማካካሻ ሆኖ ያገለግላል። በዚህም በረካታ ዜጐችን ከሥራ አጥነት ጐራ የሚወጡበት ከዚህም አልፎ ጐረቤት ሃገራት በኤሌክትሪክ ሃይል ተጠቃሚ የሚሆኑበት በመሆኑ ኘሮጀክቱን ልዩ ያደርገዋል።

በመጨረሻም በዚህ ኘሮጀክት አሁን ያለው ትውልድ ተሣታፊ መሆኑ ከታሪክ አውሪነት ወደ ታሪክ ሰሪነት ያሽጋገረ ታላቅ ሰናይ ተግባር በመሆኑ ለሁላችንም ከፍ ያለ ኩራት ይሰማናል።

LatestNews

Who is online

We have 305 guests and 8 members online