በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ሠራተኞች በጤና መድህን ዙሪያ ሠፊ ውይይት አካሄዱ።

ህዳር 26/2006 ዓ.ም የጽ/ቤቱ ሠራተኞች የጤና መድህንን ምንነትና ጠቀሜታ እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር 690/2002 እና በደንብ ቁጥር 691/2003 ላይ ከግማሽ ቀን ያላነሰ ውይይት ተካሂዷል።

በዋናነት ሠራተኛው መንግስት ያወጣውን አዋጅና ደንብ ተገንዝቦ ያለብንን የጤና ችግር በመደጋገፍ ጤናማ ህብረተሰብ መፍጠር ያስችለናል ያሉት የውይይቱን የመነሻ ጽሑፉ ያቀረቡት አቶ መኮነን ፈጠነ እና ወ/ሮ ንግስት አስፋው ናቸው።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በከፊል

የጤና መድን መርህ የእርስ በርስ መደጋገፍን፣ ፍትሃዊ የአገልግሎት ተጠቃሚነትን እና የመድህኑን አሠራር በባለቤትነት መንፈስ መከታተልና መምራት የሚቻልበት በመሆኑ ተወዳዳሪ የሆኑ የግልም ሆነ የመንግስት የጤና ተቋማት ተሣታፊ ያደርጋል፤ በዚህም በህክምና ተቋማት አሁን ያሉ የአቅም፣ የቀናነትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን ሊፈታ እንደሚችል አክለው ገልፀዋል። በመጨረሻም የዜጐችን ጤንነት በራሣችን አቅም ተባብረን በመስራት ጤናማ ህብረተሰብን በመፍጠር ምርታማነትን መጨመር ይቻላል ብለዋል።

ሠራተኞች በበኩላቸው ይህ የጤና መድህን አዋጅና ደንብ መዘጋጀቱ ጥሩ መሆኑን ገልፀው ነገር ግን ይህን አዋጅና ደንብ ተፈፃሚ ለማድረግ መንግስት ከህዝቡ ጋር በመሆን የጤና ተቋማትን አቅም ማሳደግ፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት እና የፀረ-ሙስና ተግባራት ላይ መስራት ይገባል ሲሉ አበክረው ተናግረዋል።

በመጨረሻም ሠራተኛው መንግስት ያወጣውን አዋጅና ደንብ በመገንዘብ የኘሮግራሙ ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያስችል የመነሻ ጽሁፍ መቅረቡ እንዲሁም ሠራተኛው ጉዳዩን በባለቤትነት በመያዝ በአፈፃፀም ላይ ሊከሠቱ የሚችሉ ክፍተቶችን ከመንግስት ጋር በመሆን ለመፍታት ያስችላል ፤፤ በዚህም መንግስት የዜጐችን ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መንገድ እንዲሰራ ያስቸለዋል ያሉት የኘሮግራሙን ማጠቃለያ ሀሳብ የሰጡት የጽ/ቤቱ ም/ኃላፊ አቶ ተሠማ ደምሴ ናቸው፥

LatestNews

Who is online

We have 277 guests and 5 members online