ዜና መስተዳድር ም/ቤት

በአማራ ክልል ለሚገኙ የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች የተማሪዎች ወርሃዊ የኪስ ገንዘብ 360 ብር እንዲሆን ተወሰነ።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መሰተዳድር ም/ቤት ሚያዚያ 4/2005 ባካሄደው አራተኛ ዙር ሦስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባ በክልሉ ውስጥ በሚገኙ የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች በመደበኛው መርሃ ግብር በዲኘሎማ ለሚሠለጥኑ እጩ መህራን የሚከፈለው 240 ብር ወደ 360 ብር ከፍ እንዲል በሙሉ ድምጽ ወስኗል።

የም/ቤቱ አባላት ይህንን ማድረግ ያስፈለገው ተማሪዎች ያለምንም ገንዘብ ችግር ትምህርታቸውን በአግባቡ ተከታትለው የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ለማድረግ እና በሙያ ሥነ ምግባራቸው የተሻሉ መምህራንን ለማፍራት ታስቦ ነው ብለዋል። ውሳኔውም ከግንቦት 1/2005 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን ተወስኗል።


በአብክመ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት

በህዝብ ግንኙነት ዋና የሥራ ሂደት የተዘጋጀ

LatestNews

Who is online

We have 290 guests and 8 members online