ከአባይ ድልድይ እስከ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ድረስ ያለውን አስፍልት መንገድ በአዲስ መልክ ለማሠራት ተወሰነ

ከአባይ ድልድይ እስከ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ድረስ ያለውን አስፍልት መንገድ በአዲስ መልክ ለማሠራት ተወሰነ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተደድር ምክር ቤት አራተኛ ዙር አምስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ባካሄደው ውይይት ለአስፋልት መንገዱ መሠሪያ ከሃምሣ ሚሊዮን ብር በላይ መወሰኑን ገለፀ።

ውይይት የተጀመረው የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ባቀረቡት ማብራሪያ ሲሆን፣ በማብራሪያቸውም የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከአባይ ድልድይ እስከ ገብረኤል ቤተክርስቲያን ያለውን ሁለት ኪሎ ሜትር መንገድ ጠባብ ከመሆኑ የተነሳ በየቀኑ ግጭት እየተፈጠረ ሰው እየሞተ በመሆኑ መንገዱን ለማሠራት ብር ሃምሣ ስምንት ሚሊዮን መመደቡን ገልጸዋል።

ኃላፊው አያይዘውም ከተማ አስተዳደሩ በዋናነት መንገዱ እያደረሰ ካለው አደጋ አንፃር ጊዜ የማይሰጠው ስለሆነ እንዲፈቀድላቸው ባቀረቡት መሠረት ጉዳዩ አንገብጋቢና አሣማኝ መሆኑን ለም/ቤቱ አብራርተዋል።

በዚህም መሠረት አስተዳደር ምክር ቤቱ ባቀረበው ሐሣብ ላይ በሰፊው ተወያይቶ የመንገዱ መሠራት የትንፊክ መጨናነቅ እንዳይኖር የሚያደርግና አደጋውን የሚቀንስ በመሆኑ ለሚመለከተው አካል ደብዳቤ ተጽፎል። እርምቱ እንደ ወጣ ሥራው እንዲጀምር ወስኗል።

 

የዳያስፖራና ህዝብ ግንኙነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

 

የአማራ ክልል በ2007 ዓ.ም 5.5 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን ገለፀ።

 

የአማራ ክልል በ2007 ዓ.ም 5.5 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን ገለፀ።

የአብክመ መስተዳደር ምክር ቤት ሰኔ 27/2006 ዓ.ም ባካሄደው 4ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 26ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የገቢዎች ባለስልጣን ኃላፊ ባቀረቡት ማብራሪያ የበጀት ዓመቱ የክልሉ የገቢ ዕቅድ መነሻ የተደረገው የዕድገትና ትራንስፎርማሽን ዕቅድ/GTP/  መሆኑንና የ5ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመኑ መጨረሻም የገቢ ዕቅድ 5 ቢሊዮን ይድርሣል በሚል እንደተያዘ ገልፀው፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ  የ2007 በጀት ዓመት የገቢ ዕቅድ ወደ 6 ቢሊዮን ማደግ እንዳለበት የፖለቲካ አመራሩም የጋራ ስምምነት በተደረገበት መሠረት የት ላይ ማረፍ አለበት? ዋና ዋና የገቢ አይነቶች ምንድን ናቸው? የሚለውን መጀመሪያ ለመለየት እንደተሞከረና ከዚህ አኳያ የሥራ ግብር፣ ከንግድ ትርፍ ግብር እና ከተጨማሪ እሴት ታክስ የሚገኘው ገቢ ከ80-90 በመቶ የሚሆነው የክልሉ መደበኛ ገቢ ከነዚህ የግብር አይነቶች ላይ የሚያርፍ በመሆኑ እነዚህ ላይ እርብርብ ማድረግና በየትኛውም ወረዳ /ከተማ/  ምን ያህል ድርሻ አላቸው የሚለውን ቀመር በመያዝ እያንዳንዱን ወረዳና ከተማ ለማየት እንደሞከረና ከዚህም በተጨማሪ በወቅቱ የሚሰሩ የተለያዩ መሠረት ልማቶች/ኘሮጀክቶችን/ መሠረት በማድረግ የታቀደ መሆኑን ኃላፊው አብራርተዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ የገቢ ዕቅድን ለመወሰን ከቀረቡት አማራጮች ውስጥ፤ ከክልል መደበኛ ገቢና ከከተሞች አገልግሎት የሚገኝ፤ የግብር ከፋዮችም ቁጥር እየጨመረ በመሄዱ ይህንን ምቹ ሁኔታ ተጠቅመን መሰብሰብ እንችላለን በማለት ዝርዝር ሃሣቦችን አቅርበዋል።

በመስተዳድር ም/ቤቱ ከቀረበው ማብራሪያ በመነሣት የተለያዩ ጥያቄወችንና አስተያየቶችን አንስቶ ሰፊ ውይይት ካካሄደ በኋላ ጉዳዩ በጥንቃቄ ተዘጋጅቶ የቀረበ በመሆኑ የ2007 ዓ.ም የገቢ ዕቅዱ ግብር መሰብሰብ የሚያስችሉ ተግባሮች ላይ በማተኮር 5.5 ቢሊዮን ብር ለመሰበሰብ ወሰኗል።

 

እነሱም፦ አብዛኛው ነጋዴ ካሽሪጅስተር ማሽን እንዲጠቀም በተለይ ደረጃ ሀ እና ለ ግብር ከፍይ ነጋዴዎች በሙሉ እንዲጠቀሙ የማድረግ ሥራ ላይ ማተኮር እንደሚገባ የገቢ ጉዳይ የሁሉም ጉዳይ ነው፤ ማንኛውም ገቢ የሚያገኝ አካል ሁሉ ግብር መክፈል አለበት፣ ገቢን የመሰብሰብ አቅም እንጂ በክልሉ ውስጥ ገና ያልተሰበሰበ ብዙ ሀብት ያለመሆኑ በበጀት ዓመቱ ይህ የሚጠናበት ሆኖ ቀጣይ ከዚህ በላይ ማሰብ እንደሚገባ የገቢ ሪፎርሙ ሥራችን በአግባቡ በመምራትና በመፈፀም ወደ ተሟላ ሥራ በመግባት ንቅናቂ መፍጠር የሁሉም ባለድርሻ አካላትን ርብርብ ይጠይቃል ሲል ም/ቤቱ መክሎ ገልጿል።

 

የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል በደማቅ ሁኔታ መከበሩ ተገለጸ

የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል በደማቅ ሁኔታ መከበሩ ተገለጸ

የ7ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል «በህዝቦች ተሳትፎ ትጋት ድህነትን ድል በመንሳት ብሔራዊ ክብሯንና ሰንደቃላማዋን ከፍ ከፍ በማድረግ ላይ ያለች አገር ኢትዮጵያ» በሚል መሪ ቃል የፖናል ውይይት መካሄዱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት አስታወቀ።

በርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የዳያስፖራና ህዝብ ግንኙነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አውላቸው ማስሬ እንደገለጹት ሰንደቅ ዓላማ የአንድ ህዝብና አገር ሉዓላዊ ክብርና ኩራት መገለጫ፤ አንዱን አገር ከሌላው አገር ለይቶ ለማመልከት የሚረዳ ምልክት መሆኑና ሁሉም ሀገሮች ለየራሳቸው ሰንደቅ ዓላማ ልዩ ፍቅር፣ ክብርና ሞገስ እንደሚሰጡ ገልጸዋል። ከዚህም በተጨማሪ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ መገለጫዎች፣ የሰንደቅ ዓላማ በዓላት ታሪካዊ ዳራና ዓለም ዓቀፍ ልምድ፣ የመለስ ውርስና የሰንደቅ ዓላማ ዕሴቶች እንዲሁም የሰንደቅ ዓለማ አያያዝና አጠቃቀም በሚሉት ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ለፖናሉ ተሳታፊዎች መነሻ ጽሁፍ አቅርበዋል። በፖናል ውይይቱም የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ከፍተኛ አመራሮችና የጽ/ቤቱ ሰራተኞች መገኘታቸውን ገልጽዋል።

 

ከፖናሉ ተሳታፊዎች መካከል የርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰሎሞን ዘውዴ እና የርዕሰ መስተዳድሩ የህግ አማካሪ የሆኑት አቶ መርሀጽድቅ መኮነን በሰጡት አስተያየት ይህ በዓል መከበሩ እኛ ኢትዮጵያዊያን ለበርካታ ዘመናት የአገራችንና የሰንደቅ ዓላማችን ክብር ለዘመናት አስጠብቀን እንደቆየነው ሁሉ ተተኪው ትውልድም ይህንን ታሪክ ጠብቆ በመቆየትና አገራችንን ወደ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ ለማሰለፍ በሚደረገው እንቅስቃሴ በንቃት በመሳተፍ የበኩሉን ድርሻ እንደሚገባ ገልጸዋል።

 

የ6 ወር የመልካም አስተዳድር እቅድ ክንውን ተገመገመ

የ6 ወር የመልካም አስተዳድር እቅድ ክንውን ተገመገመ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የ6 ወር የመልካም አስተዳድርና የሲቪል ሰርቪስ /BSC/ የስራ እንቅስቃሴን አስመልክቶ የቢሮ ኃላፊዎች የዞንና የከተማ አስተዳድር ኃላፊዎች ባሉበት የ1 ቀን ሙሉ የፈጀ ውይይት በርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ቁጥር 17 አዳራሽ ተካሄደ።

ክቡር አቶ ገዱ አንድርጋቸው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ስብሰባውን ሲከፍቱ እንደተናገሩት ዛሬ የምንወያየው በ6 ወሩ ውስጥ የተከናወኑትን የመልካም አስተዳድር ተግባሮች እንዴት ተከናወነ ምን ጠንካራ ጐኖች ነበሩ የተገኙ ተሞክሮዎችስ ምን ምን ናቸው።

ወደፊት ሊስተካከሉ የሚገቡ ድክመቶች ምንም ናቸው። በሲቪል ሰረባንቱ በኩል እየተከናወኑ ያሉ የሠራዊት ግንባታ የ1ለ5 እና የልማት ቡድን እንቅስቃሴ የውጤት ተኮር /BSC/ በሁለተኛ ሩብ ዓመት እንዴት እየተኬደበት እንደሆነ በዝርዝር አይቶ በውይይት በማስፋት ወደ አንድ ውሣኔ እንድንደርስ የሚያመለክት ሪፖርት ይቀርባል ብለዋል።

ዝርዝር ሪፖርቱም በህዝብ ቅሬታ ሰሚ ኃላፊና በሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ አንድ በአንድ ቀርቦ አቶ አወቀ እንየው ሲያቀርቡ ሪፖርቱ የሚያተኩረው ዞኖችን ማዕከል ያደረገ እንደሆነና በኮማንድ ፖስት የታቀደውን ተግባራት አፈፃፀማቸው ከዞን ዞን ያለውን ጥንካሬ ድክመት የሚያሣይ ነበር በአሁኑ ሰዓት በክልል መ/ቤቶች የሚገኘትን በተመለከትነው የሰራዊት አካል የሆነው የህዝብ ክንፍ አደራጅቶ በመምራት በኩል ጀምር ስራ ያለ ቢሆንም የህዝብ ክንፋንም ለይቶ አለማወቅና የመደናገር ሁኔታዎች እንዳሉ ታይተዋል።

ከሪፎርሙ የተገኙ ውጤቶች አሉ አደረጃጀቶችን በመጠቀም ሥራዎች ለማሳለጥ የተከሄደው እርቀት ጥሩ ነው ለምሣሌ፦በክህሎት፣ በእውቀትና በአመለካከትም ለውጥ እንዳለና ተደራሣሽነት እየፈጠረ መምጣቱን ለመረዳት ተችሏል ብለዋል።

አቶ ሰይድ እሸቴ እንዳቀረቡት በ6 ወሩ ውስጥ 89000/ሰማኒያ ዘጠኝ ሽ/ አቤቱታ የቀረበ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ከ45000 በላይ አቤቱታ መፍታሔ ማግኘቱን ተናግረዋል። ይህ ቁጥር የሚያሣየው በገጠርም በከተማም የቀረቡ ናቸው።

በአብዛኛው ዞኖችና ወረዳዎች በአካል ከቦታው ድረስ በመሄድ በተሰጠ ድጋፍ ጥንካሬዎችና ድክመቶችን በማሣየት ማስተካከያ የተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።

 

ከተሣታፊዎች የቀረቡ ሃሣቦች የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርሙን አስመልክቶ ሠራተኛው የሚያነሣቸውን ችግሮች በሚያሣይ መልኩ የቀረቡ ሰለሆነ አስተማሪ ነበሩ ማለት ይቻላል ነገር ግን ትኩረታቸው በግለሰብ ደረጃ ላይ ያተኩረ ነው ብሎ በኃላ በመሰረታዊ ልማት በትምህርት በጤና በኩል ብዙ ያልተቀረፉ ችግሮች መነሣት ነበረባቸው አልተነሱም ወደፊት ትኩረት ቢሰጥበት ጥሩ ነው ሲሉ ገንቢ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

 

የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት የክልሉን የ2006 በጀት ዓመትየመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት የልማት እና መልካም አስተዳደር እቅድ አፈፃፀም ገመገመ

የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት የክልሉን የ2006 በጀት ዓመት የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት የልማት እና መልካም አስተዳደር እቅድ አፈፃፀም ገመገመ

መስተዳድር ምክር ቤቱ ጥር 27/2006 ዓ.ም ባካሄደው 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 5ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የክልሉ ካቢኔ በ2006 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የነበረው አፈፃፀም ምን ደረጃ ላይ እንዳለ በማወቅ ቀጣይ ባሉት ወራቶች ቀሪ ሥራዎችን በመለየት እና የጋራ ግንዛቤ በመፍጠር መፈፀም የሚቻልበትን ስልት መቀየስ ዋና ሥራ ነው በማለት አጀንዳውን የከፈቱት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ናቸው።

ይህ የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በክልሉ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ተጠቃሎ የቀረበ ሲሆን ሪፖርቱም የእቅዱን መነሻ ሁኔታዎች፤ እቅዱን ለመፈፀም የተቀመጡ አቅጣጫዎችን፣ የዓመቱ ቁልፍ ተግባራት እቅድ አፈፃፀም በዝግጅት ምዕራፍና በትግበራ ምዕራፍ፣ የግማሽ ዓመቱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት እቅድ አፈፃፀም በዋና ዋና ሴክተሮች፣ የበጀት ዓመቱ የገቢ እና ወጭ አፈፃፀም ሁኔታ እንዲሁም የቀጣይ የትኩረት ነጥቦች የሚሉ መነሻ ሀሳቦችን መሠረት በማድረግ ዝርዝር ሪፖርቱን ያቀረቡት የክልሉ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ግርማ ተስፋዬ ናቸው።

መስተዳድር ምክር ቤቱም የቀረበውን ሪፖርት ግልጽነት እና አንኳር ጉዳዮች ላይ ማተኮሩን በጥንካሬ አይቶ፤ የታዩ ጥንካሬዎችን እና ክፍተቶችን ያመላከተ ነው፤ በመሆኑም ጥንካሬያችንን የበለጠ የምናጐለብትበት ክፍተታችንን የምንሞላበት ነው ሲል ም/ቤቱ አክሎ ገልጿል።

ሪፖርቱን መነሻ በማድረግ መስተዳድር ም/ቤቱ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና መልካም አስተዳደር ተግባሮች አፈፃፀም ዙሪያ የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን በማንሳት ሠፊ ውይይት ካካሄደ በኋላ የቀጣይ 6 ወራት የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

ሰለሆነም የተለያዩ ተቋማት የግንባታ ሥራዎች ሀብትን በአግባቡ ያለመጠቀም፣ የመጓተት እና የጥራት ችግር ያለባቸው በመሆኑ ችግሮችን በመለየት መፍታት፤ በኢንቨስትመንት እና በኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ የተጀመሩ ተግባሮችን ማጠናከር፤ የማዕድን ዘርፍ የሥራ እድል የሚፈጥር እና ልማትን የሚያፋጥን በመሆኑ ከአደረጃጀት ጀምሮ በመፈተሽ ወደ ሥራ መግባት፣ ከመብራት ጋር ተያይዞ ያለውን ችግር ለመፍታት ትኩረት ሰጥቶ መስራት፤ የልማት ሠራዊት ግንባታ ጅማሮውን አጠናክሮ መቀጠልና ከፍተኛ አመራሩ ትኩረት ሰጥቶ ሁሉንም ተቋማት መደገፍ፣ ከግብርና አኳያ ያለው ጥንካሬ ወጥነት እንዲኖረው መረባረብ ይገባል ሲል በኢኮኖሚ ዘርፍ ያለውን የትኩረት አቅጣጫ ም/ቤቱ አመላክቷል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ በማህበራዊ እና መልካም አስተዳደር ዙሪያም የፀረ-ኪራይ ሰብሳቢነት ትግሉን አጠናክሮ ለማስቀጠል በየደረጃው ያለው አመራር ትኩረት ሰጥቶ መስራት፤ ከፍትህ ቢሮ አኳያ ህግ የማስከበርና አቅም የመገንባት ሥራ በዋናነት መሠራት ያለባቸው ተግባሮች በመሆናቸው በፍትህ እና በህግ አስከባሪ አካላት መካከል ያለውን ቅንጅት ማጠናከር፤ ከጤና አንፃር አገልግሎቱን ለማሻሻል የደብረብርሃን ሆስፒታልና መሠል ተቋማትን ተሞክሮ ማስፋት፣ ሁለንተናዊ የጤና አፈፃፀም ለማሻሻል አመራሩ ሁሉንም ተቋማት የመከታተልናየመደገፍ ብቃቱን ማሻሻል፤ ከሳዑዲ አረቢያ ተመላሾችን በተመለከተ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጉዳዩን በተደራጀ መልክ በመያዝ ከዞኖች ጋር መስራት፤ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ መሠራት ያለባቸው ሥራዎች ከአመራሩ ጀምሮ ያለውን ኃይል በንቃት በማሳተፍ እና በማጠናከር ሁሉም የሚመለከታቸዉ አካላት የሚፈለግባቸውን መወጣት እንዲችሉ ማድረግ የሚሉ የትኩረት ነጥቦች በምክር ቤቱ ቀርበው የጋራ መግባባት ተደርሶባቸዋል።


በአብክመ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት

በህዝብ ግንኙነት ዋና የሥራ ሂደት የተዘጋጀ

 

Last Updated on Monday, 24 February 2014 11:09
 


Page 17 of 17
Content View Hits : 9428102

Comments

  • Wow, his piece of writing iіs fastidious, my siste...
  • Goood day! D᧐ you use Twitter? I'd like tto follow...
  • Very good post! We will be linking to this particu...
  • I am really loving the theme/design of your weblog...
  • I as well as my pals happened to be following the ...

Latest News

Who is online

We have 107 guests and 15 members online

Entertainment