የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ለተለያዩ የዞን የከተማና የወረዳ አመራሮችና ባለሙያዎች የስራ ስልጠና መሰጠቱ ተገለጸ፤

የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ለተለያዩ የዞን የከተማና የወረዳ አመራሮችና ባለሙያዎች የስራ ስልጠና መሰጠቱ ተገለጸ፤

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ለ153 ለተለያዩ የዞን የከተማና የወረዳ የህዝብ ቅሬታ ሰሚ አመራሮችና ባለሙያዎች ከየካቲት 29/2010 ዓ.ም እስከ መጋቢት 2/2010 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ከተማ ስልጠና መስጠቱን አስታወቀ፡፡

የስልጠናው ዓላማ በአዲሱ አመዳደብ የተነሳ ሰልጣኙ በብዛት በአዲስ ምደባ የመጣ ስለሆነ የህዝብን ቅሬታ በአግባቡ አጣርቶ ለደንበኞቻችን ተገቢና ግልጽ የሆነ አሰራር ተከትሎ በአጭር ጊዜ ውስጥ ርዕቱና ተገቢ የሆነ ውሳኔ እንዲሰጥ ታስቦ ነው፡፡

በስልጠናው የቀረቡት ጽንሰ ሀሳቦች ስምንቱ የመልካም አስተዳደር መርሆዎች በደንብ ቁጥር 130/2007 በተካተቱት የምርመራ ማጣራት ስርዓቶችና በማህበራዊ ተጠያቂነት አሀዝ ካርድ አሰራር ዙሪያ አስመልክቶ ዘርዘር ያለ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

የክልሉ የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሰይድ እሸቴ እንዳሉት በዚህ ተከታታይ ሶስት ቀን ውስጥ የተሰጣችሁን የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ወደየስራ ቦታችሁ ተመልሳችሁ ወደ ስራ ስትገቡ በርካታ የህዝብ ቅሬታ በየወረዳዎች ስላሉ ደንበኞቻችንን ባግባቡ በመቀበል በግልጽነት፣ በተጠያቂነት፣ በቅልጥፍናና ፍትሀዊ በሆነ አሰራር ማስተናገድ አለባችሁ በሚል አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል፡፡

በስልጠናው ወቅት አስተያየት ከሰጡት ተሳታፊዎች መካከልም አቶ አማኑኤል ይትባረክ ከጎንደር ከተማ የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ኃላፊ ወ/ሮ የሽእመቤት ይላቅ ከምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ከተማ የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ኃላፊ የሆኑት እንደተናገሩት የተሰጠን ስልጠና አቅም የፈጠረልንና የማናውቃቸውን ህጎችና ደንቦች እንዲሁም መመሪያዎችን በሚገባ ስለጨበጥን ወደየ አካባቢያችን ተመልሰን ህዝባችንን ለማገልገል ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡

መጋቢት 03/2010 ዓ.ም

የዳያስፖራና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት

 

ማርች 8/ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን/ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዋለ፡፡

ማርች 8/ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን/ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዋለ፡፡

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓልን በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ መዋሉን የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ገለጸ፡፡

የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት አመራሮችና ሠራተኞች ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓል መከበር ያለውን ፋይዳ፣ ቀኑን ለምን ማክበር እንደአስፈለገ፣ ትልቅ ተሞክሮና ፈር ቀዳጅ ስራ ያከናወኑ ሴቶችን ገድልና ተሞክሮ እያነሱ ተወያይተዋል፡፡

ማርች 8/ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ሴቶች በጾታቸው የሚደረስባቸውን መድሎና ጭቆና ለማስቀረትና ለማስወገድ ካደረጉት ትግል ጋር ተያይዞ የሚከበር በዓል መሆኑ ተገልጿል፡፡

በሴቶች ላይ በተለይ ከጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ጋር ተያይዞ የሚደርሱ ጥቃቶችና መጤ ባህሎችን ለመከላከል፣ የሴቶችን ተሳታፊና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ስራ መስራት እንዳለባቸው ተወያይተዋል፡፡

ሴቶች የአገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማስቀጠል በሚደረገው ጥረት በሙሉ እውቀትና አቅማቸው አስተዋጽዖ ማበርከት እንደሚጠበቅባቸውም ተናግረዋል፡፡

በሴቶች ዙሪያ አሉ የሚባሉ ችግሮችን በማንሳት፣አቅም በፈቀደ መጠን ማርች 8 እያስታወሱ መፍታት እንዳለባቸው ተግባብተዋል፡፡

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ107ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ42ኛ ጊዜ "በተደራጀ የሴቶች ተሳትፎና ንቅናቄ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እናረጋግጣለን" በሚል መሪ ቃል በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል፡፡

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር 1911 መከበር የጀመረ ሲሆን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እውቅና የተሰጠው 1975 መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።

የካቲት 30/2010 ዓ.ም

የዳያስፖራና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት

 

የህዝብ ቅሬታ ሰሚ የክልል መጀመሪያ ደረጃ ቅሬታ ሰሚ ባለሙያዎችን ስልጠና መሰጠቱ ተገለጸ፤

የህዝብ ቅሬታ ሰሚ የክልል መጀመሪያ ደረጃ ቅሬታ ሰሚ ባለሙያዎችን ስልጠና መሰጠቱ ተገለጸ፤

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ለ34 የክልል ቢሮዎች መጀመሪያ ደረጃ ቅሬታ ሰሚ ባለሙያዎች ከየካቲት 10-11/2010 ዓ.ም በእንጅባራ ከተማ ስልጠና መስጠቱን አስታወቀ፡፡

የክልሉ ህዝብ ቅሬታ ሰሚ ኃላፊ አቶ ሰይድ እሸቴ እንደተናገሩት የስልጠናው ዓላማ መጀመሪያ ደረጃ ቅሬታ ሰሚዎች በJGE ምደባ መሰረት በአብዛኛው አዲሶች ስለሆኑ ለውሳኔ አሰጣጥ እንዳይቸገሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠት አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ አያይዘውም ሰልጣኞቹም ትኩረት ሰጥተው በመከታተል ያልገባቸውን በመጠየቅ በንቃት እንዲሳተፉ አጽንኦት ሰጥተው አሳስበዋል፡፡

በስልጠናው የቀረቡት ዋና ዋና ጭብጦች የ2010 ዓ.ም የ6 ወር ዕቅድ አፈጻጸም የሁለተኛው የህዝቦች አስተያየትና የዳሰሳ ጥናት በደንብ ቁጥር 130/2007 አሰራርና ከደንብ ቁጥር 75/2003 ጋር ያለው ተዛምዶና ልዩነትን አስመልክቶ ሰፋ ያለ ማብራሪያ በማቅረብ ሰልጣኞቹ ልዩነታቸውንና አንድነታቸውን ተገንዝበው ውሳኔ ለመስጠት እንዳይቸገሩ እና ግልጽነትን ይዘው እንዲሄዱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት የተሰጣቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከስልጠናው ተሳታፊዎች መካከል ስልጠናውን አስመልክተው አስተያየት ሲሰጡ ከስልጠናው በቂ ትምህርት አግኝተናል እስከ ዛሬ ስንሰራ የነበረው በገባን ልክ እንጅ በደንቡ መሰረት ባለመሆኑ ስተታችንን ወስደናል ከዚህ በኃላ በትክክል በመስራት የህብረተሰቡን እናረካለን በማለት ገልጸዋል፡፡

የካቲት 12/2010 ዓ.ም

የዳያስፖራና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት

 

 

በዳያስፖራ ፖሊሲ፣ አዋጅና ደንብ ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት ስልጠና ተሠጠ

በዳያስፖራ ፖሊሲ፣ አዋጅና ደንብ ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት ስልጠና ተሠጠ

የአብክመ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በዳያስፖራ ፖሊሲ፣ አዋጅና ደንብ ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት የካቲት 10/2010 ዓ.ም በደብረ ታቦር ከተማ ስልጠና መስጠቱን አስታወቀ፡፡

ስብሰባውን በንግግር የከፈቱት የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ም/ኃላፊ አቶ ተሠማ ደምሴ እንደገለጹት የክልሉ መንግስት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በክልላቸው በተለያዩ የልማት መስኮች የሚያደርጉትን ተሳትፎ ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፤ በመሆኑም ጥሪ የተደረገላችሁ ባለድርሻ አካላት በዳያስፖራ ፖሊሲ፣ አዋጅና ደንብ ዙሪያ በሚገባ በመገንዘብ የነቃ ተሳትፎ እንድታደርጉ በማለት አሳስበዋል፡፡

የስልጠናውን ጹሑፉ ያቀረቡት የዳያስፖራ፣ ህዝብ ግንኙነትና ፕሮቶኮል ጉዳዮች ኃላፊ አቶ አውላቸው ማስሬ እንደገለጹት የዳያስፖራ ፖሊሲው የተዘጋጀው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የውጭ ጉዳይና አገራዊ ደህንነት ፖሊሲና ስትራቴጂን መነሻ በማድረግና በዳያስፖራው ጉዳዮች ዙሪያ የቆዩ መመሪያዎችንና አፈፃፀሞችን በዝርዝር በማጥናት፣ የተለያዩ ጽሁፎችንና የተሞክሮ ልውውጥ መድረኮችን እንዲሁም የሌሎች አገሮች ጠቃሚ ልምዶችን በግብአትነት በመጠቀምና ከዳያስፖራው የተሰጡ አስተያየቶችን በማካተት ነው ብለዋል ፡፡

ይህ ፖሊሲ የአገሪቱን ልማትና የዴሞክራሲ ስርዓት ለማስቀጠል ጠንካራ የዳያስፖራ ግንኙነት መመስረትና ተሳትፎውን ማሳደግ የሚኖረውን ጉልህ ሚና ግምት ውስጥ አስገብቶ የተቀረጸ በመሆኑ መንግስት በውጭ የሚኖረውን የህብረተሰብ ክፍል/ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን/ በሚገኙባቸው አገሮች መብታቸው ተጠብቆ እንዲኖሩና ከትውልድ አገራቸው የሚያስፈልጋቸውን አገልግሎቶች በኢምባሲዎችና ቆንስላ ጽ/ቤቶች በኩል እንዲያገኙ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል በማለት ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

የዳያስፖራ ፖሊሲው ዋና ዓላማ በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከትውልድ ሀገሩ ጋር ያለውን ትስስር በማጠናከር በአገሩ ልማት፣ ሰላምና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ጠንካራ ተሳታፊ ሆኖ ራሱን ጠቅሞ ትውልድ አገሩንም በመጥቀም በጋራ ማደግ የሚያስችል አመቺ ሁኔመፍጠር መሆኑን ኃላፊው አክለው ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ኃላፊው እንደገለጹት የክልሉ መንግስት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በክልላቸው በተለያዩ የልማት መስኮች የሚያደርጉትን ተሳትፎ ለማሳደግ የሚደረገውን ድጋፍ ለማጠናከር እንዲቻል በርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የዳያስፖራ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት መደራጀቱን ገልጸው በየደረጃው የሚገኘው የኢንቨስትመንት መዋቅር ዳያስፖራው በውጭ አገር ቆይታው ያፈራውን ሀብት በክልሉ ውስጥ በተለያዩ ኢንቨስትመንት እንዲሳተፉ በማድረግ ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል እንዲፈጥሩና የውጭ ምንዛሬን እንዲያሳድጉ ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

 

የፌዴራል አቃቤ ሕግና የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረጉ

የፌዴራል አቃቤ ሕግና የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረጉ
የኢፌዴሪ የመንግስት ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በወንጀል ተጠርጥረው የተከሰሱና ጉዳያቸው በፌዴራል ደረጃ ሲታይ የነበረ 598 ተከሳሾችን ክስ ማቋረጡን የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር ምክር ቤት ደግሞ 2 ሺህ 905 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ጠቅላይ አቃቤ ሕግና ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍርዴ ቸሩ እንደገለጹት ባለፉት ሁለት እና ሶስት ዓመታት በክልሉ ተከስተው በነበሩ ግጭቶች በወንጀል ተጠርጥረው በፌዴራል ደረጃ ምርመራ የተጣራባቸው፣ ክሣቸው በሂደት ያለ እና ፍርድ የተወሰነባቸው 598 ሰዎች መንግስት በወሰነው ውሣኔ መሠረት የፌዴራል አቃቤ ሕግ ክሣቸው እንዲነሣ ወስኗል፡፡

ምንም እንኳ በተለያዩ ጊዜያቶች በተለያዩ ደረጃ በወንጀል መሣተፋቸው ቢረጋገጥም ክሣቸው ተቋርጦ መዝገቡ እንዲዘጋ ለየፍርድ ቤቶች የክስ ማንሻ ደብዳቤ ተላልፏል ብለዋል፡፡

አቶ ፍርዴ አክለውም የክልሉ መንግስት በዓመት ሁለት ጊዜ ለሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ያደርጋል፡፡ በመሆኑም ግማሽ ዓመቱን መሠረት በማድረግ 2,923 ሕግ ታራሚዎች ጉዳያቸው ተጣርቶ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት ከጥር 23 ቀን 2010 . ጀምሮ ይቅርታ እንዲደርግላቸው ወስኗል፡፡

 

የይቅርታ አሰጣጡ ፍትሃዊና ከአድሎ የፀዳ እንዲሆን መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡ በዚህ መሠረት የታራሚዎች የቆይታ ጊዜ፣ የዕድሜ መግፋት፣ በቆይታ ጊዜያቸው የተፀፀቱ መሆኑን፣ እንዲሁም በግድያና በግድያ ሙከራ የተሣተፉ ደግሞ ከተጎጅ ቤተሰቦች ጋር መታረቃቸው የቴክኒክ ኮሚቴው ካረጋገጠ በኋላ መስፈርቱን ላሟሉት ይቅርታ ተሰጥቷል ያሉት አቶ ፍርዴ ዘር ማጥፋት፣ ሙስና፣ አስገድዶ መድፈር፣ ሕገ-ወጥ የመሣሪያ ዝውውር እና መሰል ወንጀሎች በሕገ-መንግስቱ ይቅርታ የማያሰጡ ናቸው ብለዋል፡፡

 


Page 2 of 17
Content View Hits : 9234386

Comments

  • Yes! Finally something about website. Here is my w...
  • I was rеcommended this web site by my cousin. I am...
  • Its like yoᥙ rеad my mind! You appeaг to know ѕso ...
  • I was rеcommended this web site by my cousin. I am...
  • I was rеcommended this web site by my cousin. I am...

Latest News

Who is online

We have 117 guests and 6 members online

Entertainment