በስመ-ንብረት ዝውውር ክፍያ አፈጻጸም ባጋጠሙ ችግሮችላይ የመፍትሄ ሀሳብ መሰጠቱ ተገለጸ

በስመ-ንብረት ዝውውር ክፍያ አፈጻጸም ባጋጠሙ ችግሮችላይ የመፍትሄ  ሀሳብ መሰጠቱ ተገለጸ፡፡

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት 5ኛ ዙር ሁለተኛ    አመት የስራ ዘመን ጥር 19 ቀን 2009 ዓ/ም ባካሄደው 10ኛ መደበኛ ስብሰባ    በስመ-ንብረት ዝውውር ክፍያ አፈጻጸም ባጋጠሙ ችግሮች ዙሪያ ቢሮው ባቀረበው ማሻሻያ ውሳኔ መሰጠቱን አስታወቀ፡፡

ውይይቱ የተጀመረው በህግና አስተዳድር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የፍትህ ቢሮ ሀላፊ ሲሆኑ በክልሉ ቴምብር ቀረጥ አዋጅ  ቁጥር 31/1991 አንቀጽ 3/12 ስር በልዩ ሁኔታ በጋብቻ በጋራ በተፈሩ ሀብትና ንብረቶች ስመ-ንብረት ዝውውር ላይ የባል/ሚስት ድርሻን የቴምብር ቀረጥ ክፍያን የማይመለከት መሆኑን የሚጠቅስ አንድ ንዑስ አንቀጽ ቢቀመጥ፣ ቋሚ ኮሚቴው አክሎም በከተማ ልማት ፣ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ የተሻረው መመሪያ ህጋዊ አሰራሩን ተከትሎ በመመሪያ ቢሻርና ከዚሁ ጋር ተያይዞም ስመ-ንብረት ዝውውር ሲፈጸም ሚስት/ባል ከራሱ ወይም ከራሱ ድርሻ ውጭሊኖር የሚችልን የንብረት ስመ-ንብረት ማጠቃለያን አጋጣሚ መንግስት ገቢ ማግኘት ስለአለበት ከድርሻውጭ ያለው ንብረት የሚከፈልበት መሆኑን በአዋጁም ሆነ በመመሪያው ተብራርቶ ቢቀመጥ የሚል የውሳኔ ሀሳብ ኮሚቴው ማቅረቡን ገልጸዋል፡፡

በዚህ  መሰረት ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ ባልና ሚስት ሆነው በጋብቻ በጋራ ሀብትና ንብረት አፍርተው ቆይተው በተለያዩ ምክንያቶች የባልን ወይም የሚስትን ንብረት ድርሻ በስም ለማድረግ በስመ-ንብረት ዝውውር ወቅት የሚከፈሉ የታክስና የአገልግሎት ክፍያዎች ዝውውር ተጨማሪ ጥቅም በማያገኙበት የሃብትና ንብረት ባለቤት ሆነው በቆዩ የትዳር አጋሮች በአንዳቸው ስም ተመዝግቦ በመቆየቱ ብቻ 2% የቴምብር ቀረጥ ታክስ እና 3%ደግሞ የአገልግሎት ገቢ ከንብረቱ ጠቅላላ ዋጋ ታስቦ መከፈሉ አድሏዊና ኢ-ፍትሀዊ መሆኑና ጉዳዩም በዋናነት ጫና እየፈጠረ ያለው በሴቶች የንብረት ባለቤትነት ላይ መሆኑን ጉዳዮን የፍትህ ቢሮና ህግና አስተዳድር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ካቀረበው የውሳኔ ሀሳብ የተረዳ መሆኑን ምክር ቤቱ ማስተካከያ መደረግ እንዳለበት ተስማምቷል፡፡ በመሆኑም  የሀብትና ንብረት ባለቤት ሆነው በቆዩ የትዳር አጋሮች በአንዳቸው ስም ተመዝግቦ በመቆየቱ 2% የቴምብርና ቀረጥ ታክስ እና 3%የአገልግሎት ክፍያ ከንብረቱ ጠቅላላ ዋጋ ታስቦ እንዲከፍሉ ማድረግ ፍትሃዊ ባለመሆኑ በፍችና በሞት የሚደረግ የስመ-ንብረት ዝውውር ከቀረጽ ነፃ እንዲሆን፣ከዚህ ጋር በተያያዘም፣በከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ያወጣው መመሪያ ቁጥር 4/2006 ዓ/ም አንቀጽ 14/4 በባል ወይም በሚስት ስም የተመዘገበ ንብረት ክፍፍል ሲደረግ አንደኛው ወገን የሚያጠቃልለው ሲሆን የሚከፈለው 3% የአገልግሎት ክፍያ እንዲሻር መስተዳድር ም/ቤቱ ወስኗል፡፡

 

የዳያስፖራና ህዝብ ግንኙነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

 

የአብክመ መስተዳድር ምክር ቤት ከክልሉ በተለያዩ ከተሞች ህብረተሰቡ ለሚያነሳቸው የመኖሪያ ቤት አቅርቦትና አሰጣጥ ችግሮችን የሚፈታ መመሪያ አዘጋጀ፣

የአብክመ መስተዳድር ምክር ቤት ከክልሉ በተለያዩ ከተሞች ህብረተሰቡ  ለሚያነሳቸው የመኖሪያ ቤት አቅርቦትና አሰጣጥ ችግሮችን የሚፈታ መመሪያ አዘጋጀ፣

ከዚህ በፊት ነባርና አዲስ የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበራትን የመኖሪያ ቤት ግንባታና ቦታ አቅርቦት፣አሰጣጥና ግንባታን ለመወሰን የወጣው መመሪያ ቁጥር 9/2005 ዓ.ም ላይ በአፈጻጸሙ ላይ ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት እና አብዛኛውን ህብረተሰብ የቤት ባለቤት ማድረግ አስቸጋሪ መሆኑን በማመን፡-

1. በመሪና በንዑስ ማዘጋጃ ቤቶች ታዳጊ ከተሞች እስከ 250 ካ.ሜ

2. በሜትሮፖሊታንት ከተሞች እስከ 100 ካ.ሜ

3. በአነስተኛ እና በመካከለኛ ከተሞች እስከ 150 ካ.ሜ የቦታ መጠን እንዲሰጥ የቦታ አሰጣጥ መመሪያ መስተዳድር ምክር ቤቱ አውጥቷል፡፡

የዲያስፖራና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

 

ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት

 

121ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ

121ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ

 

መግቢያ፡-

የአድዋ ጦርነትየካቲት 23 ቀን 1988 . በኢትዮጵያና ኢጣሊያ መካከል የተካሄደ ውጊያ ሲሆን አንደኛው የኢትዮጵያና ጣሊያን ጦርነት ክፍል ነው። ኢትዮጵያ አሸናፊነት የጣልያን የቀኝ ግዛት ማስፋፋት ተኮላሸ።

የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክብር ማኅተም፤ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎ ቀንዲል ነው፡፡ የመላው ዓለም ተፈጥሮአዊ ግብር እና ሰብአዊ ክብር የታደሠው፤ በእውነትና በፍትህ ህልውናና ምልዓት ላይ የተሰካ ትልቅ ጥርስ የተነቀለው በአድዋ የታላቅ ህዝቦች ታላቅ ድል ነው፡፡

የአድዋ ድል ለመጀመሪያ ጊዜ የተከበረው በሠባተኛ ዓመቱ 1895 . (.. 1903) ከአንድ መቶ ዘጠኝ ዓመታት በፊት አሁን አዲስ አበባ ፒያሳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ያለበት ሥፍራ ምኒሊክ አደባባይ ነው፡፡ በክብረ በዓሉ (በድል በዓሉ) ላይ ዲፕሎማቶችና የውጪ አገር መንግሥታት ተወካዮች አርበኞች የመንግስት ባለሥልጣኖች ብዙ ሺህ ፈረሰኞችና ሥፍር ቁጥር (ወፈ ሠማይ የሆኑ) ኢትዮጵያውያን ከሊቅ እስከ ደቂቅ መገኘታቸውን፤ ከፈረሰኞቹ ብዛት የተነሳ ፀሐይ በአቧራ እስከመጋረድ መድረሷን ጳውሎስ ኞኞ የኢጣሊያና የኢትዮጵያ ጦርነት በተሰኘ መጽሐፉ ላይ ጽፎአል፡፡ እንዲሁም ተክለፃዲቅ መኩሪያን የመሳሰሉ ኢትዮጵያውያን የታሪክ ተመራማሪዎችና የውጪ አገር ዜግነት ያላቸው ፀሐፍትና ተመራማሪዎች በተለያዩ መፃሕፍቶቻቸው ይሄንን አሣምረው ጽፈውታል፡፡

አድዋ

የኢትዮጵያዊያን ኩራት

‹‹እግዚአብሔር በቸርነቱ እስካሁን ጠላትን አጥፍቶ አገር አስፍቶ አኖረኝ፡፡ እኔም በእግዚአብሔር ቸርነት ገዛኹ፡፡ እንግዲህ ብሞት ሞት የሁሉም ነውና ስለ እኔ ሞት አላዝንም፡፡ ደግሞ እግዚአብሔር አሳፍሮኝ አያውቅም፤ ወደፊትም ያሳፍረኛል ብዬ አልጠራጠርም፡፡ አሁንም አገር የሚያጠፋ፣ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት እግዚአብሔር የወሰነልንን ባሕር አልፎ መጥቷል፡፡ እኔም ያገሩን ከብት ማለቅ የሰውን ድካም አይቼ እስካሁን ዝም ብለው ደግሞ እያለፈ እንደ ፍልፈል መሬት ይቆፍር ጀመር፡፡ ‹‹አሁንም በእግዚአብሔር ረዳትነት አገሬን አሳልፌ አልሰጠውም፡፡ የአገሬ ሰው ካሁን ቀደም የበደልሁህ አይመስለኝም፡፡ አንተም እስካሁን አላስቀየምኸኝም፡፡ ጉልበት ያለህ በጉልበትህ ዕርዳኝ፡፡ ጉልበት የሌለህም ለልጅህ፣ ለምሽትህ፣ ለሃይማኖትህ ስትል በሐዘን ዕርዳኝ፡፡ ወስልተህ የቀረህ ግን ኋላ ትጣላኛለህ፣ አልተውህም ማርያምን ለዚህ አማላጅ የለኝም፡፡ ዘመቻዬም በጥቅምት ነውና የሸዋ ሰው እስከ ጥቅምት እኩሌታ ድረስ ወረይሉ ከተህ ላግኝህ፤” አሉ፡፡

 

የውጫሌ ውልና የአድዋው ዘመቻ ዝግጅት

አፄ ምኒልክ የአፄ ዮሐንስን መተማ ላይ መሞት እንደሰሙ ወዲያውኑ በሚያዝያ ወር የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መሆናቸውን ካረጋገጡ በኋላ፣ በተለመደው ብልህነታቸውና ዲፕሎማሲያቸው በመጠቀምና የጊዜውን አመቺነት በመመልከት ከወዳጃቸው ከኢጣሊያ መንግሥታት ጋር መነጋገር ጀመሩ፡፡ አፄ ምኒልክ ለዚህ ጉዳይ የሚተማመኑበት ኢጣሊያዊው ካውንት አንቶኔሊ ነበር፡፡ ይህ ሰው በአፄ ዮሐንስ ዘመነ መንግሥት ምኒልክ ከኢጣሊያ መንግሥት መሣሪያና ጥይት እንዲያገኙ ያደረገና በዚህ ዘዴውም አፄ ዮሐንስን ለመቋቋምና ኢትዮጵያን ለመከፋፈል ተጠቅሞበታል፡፡

እዚህ ላይ በኢጣሊያና በሸዋ መንግሥት መካከል ወዳጅነት ለመፍጠር አንቶኔሊ የተከተለውን ፖሊሲ የተቃወመውና በኢጣሊያ አገር ከፍተኛ ተሰሚነት የነበረው ጄኔራል ባልዲሴራ ብቻ ነበር፡፡ ባልዲሴራ የአፄ ዮሐንስን ሕልፈት ካወቀ በኋላ ለኢጣሊያ ታላቁ ጠላት የሸዋ መንግሥት እንደሚሆን በመገመቱ፣ ለሸዋው ንጉሥ ለአፄ ምኒልክ ምንም ዓይነት መሣሪያና ጥይት በተጨማሪ እንዳይሰጥ አጥብቆ ተቃውሞ ነበር፡፡

ምኒልክ የኢትዮጵያን ዘውድ ለመያዝ እንዲችሉ የኢጣሊያን ድጋፍና ዕርዳታ ለማግኘት አንቶኔሊን በጠየቁት ጊዜ፣ ለኢጣሊያኖች የተጨበጠ ውለታ ካላሳዩ በስተቀር አንቶኔሊ የሚፈልጉትን የኢጣሊያንን ድጋፍ ሊጠይቅላቸው እንደማይችል አስታወቀ፡፡ በዚህም ምክንያት ከአንድ ስምምነት ላይ ደርሰው ዝነኛ የሆነው የውጫሌ ውል በአንቶኔሊ ተረቅቆ ሚያዝያ 25 ቀን 1881 . በውጫሌ ከተማ ተዋዋሉ፡፡ አፄ ምኒልክም ውሉን ፈርመው ስምምነቱ በኢጣሊያ ሚኒስትሮች እንዲፀድቅ የአክስታቸው ልጅ ራስ መኮንንን በአምባሳደር ደረጃ ወደ ሮም ላኩ፡፡ የውጫሌ ውል የተፈረመው አሰብ ከተያዘ ከሃያ ዓመት በኋላ ነበር፡፡

እንደ ስዊድናዊው የታሪክ ምሁርና ጸሐፊ ጥናት የውጫሌ ውል በኢጣሊያ መንግሥት ተረቆ ለአንቶኔሊ የተሰጠው መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ጥናት ደግሞ ምኒልክ 17ኛው የውሉ ክፍል ቀርቶ 12ኛው ክፍል ላይ ሐሳብ እንዲጨመር ማሳሰባቸውንና አንቶኔሊ ግን ‹‹ከፈለጉ እሺ ግን ከውጪ ለሚያደርጉት ግንኙነት የንጉሥ ጓደኛ ቢያገኙ ምን ክፋት አለበት?›› በማለቱ ምኒልክ የአንቶኔሊ የማስመሰል ንግግር እንደ እውነት ቆጥረው እንደተውት ያረጋግጣል፡፡ የውጫሌን ውል በመጀመሪያ አደገኛነቱን የገለጹት አለቃ አጽሜ ጊዮርጊስ ሲሆኑ፣ ራሳቸው በጻፉት ያልታተመ መጽሐፋቸው እንደገለጹት ለምኒልክ እንዲህ ሲሉ በደብዳቤ አመለከቱ፡፡‹‹… የተጻፈው ውል ወደ ኢጣሊያ አገር የሚሄደው ማለፊያ ነው፡፡

 

ብቻ 17ኛውን ክፍል ይመልከቱት፡፡ ዛሬ በሚዛን ብትመዘን የብር ተመን አትሆንም፡፡ ካንድ ዓመት በኋላ ግን ከሺህ ቶን ፈረሱላ እርሳስ ይልቅ ትከብዳለች…›› አፄ ምኒልክ ይኼ ደብዳቤ እንደደረሳቸው አንቶኔሊን አስጠርተው እንደገና ስለ ውሉ 17 ክፍል ጠየቁት፡፡

አንቶኔሊ አሁንም ግልጽ ባልሆነ አነጋገር አፄ ምኒልክን እንዲህ በማለት አታለላቸው፡፡ ‹‹ታዲያ ይህ ምን ክፋት አለው (17ኛውን የውሉን ክፍል ማለት ነው) እኛ የእርስዎ አሽከርና ፖስተኛ መሆናችን ነው እንጂ…›› ሲላቸው ነገሩ ለጊዜው በዚሁ የቀረ መሰለ፡፡ የውጫሌ ውል ሃያ ክፍሎች ሲኖሩት በአንቀጽ 3 የኢጣሊያ ግዛት በነበረችው ማለትም በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል የወሰን ድንበር የሚያመላክት ሲሆን፣ በአንቀጽ 17 የተደረገው ስምምነት በኢትዮጵያና በኢጣሊያ መካከል አለመግባባት የፈጠረና ኋላም ለአድዋ ጦርነት መነሻ የሆነ አንቀጽ ነው፡፡ ይኼ አንቀጽ በአማርኛ እንደሚለው፡- ‹‹የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ከአውሮፓ ነገሥታት ለሚፈልጉት ጉዳይ በኢጣሊያ መንግሥት አጋዥነት መላላክ ይቻላቸዋል፤›› የሚል ሲሆን፣ ፍችውም ኢትዮጵያ ከወደደች በኢጣሊያ በኩል ግንኙነት ታደርጋለች ነው፡፡ በኢጣሊያንኛ ግን ግዴታም ጭምር እንዲያመለክት ተደርጎ ተጽፎ ነበር፡፡

ራስ መኮንን አንቶኔሊንና አርባ የኢትዮጵያ ልዑካንን አስከትለው ነሐሴ 22 ቀን 1881 . ሮም ከተማ ሲደርሱ ታላቅ የሆነ አቀባበል ተደረገላቸው፡፡ በወቅቱ የኢጣሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲኞር ክሪስፒ የውጫሌን ውል አንዳንድ ነገሮች አስተካክለው የሞግዚትነቱን ጉዳይ ሳይነኩ ተጨማሪ ውል መስከረም 21 ቀን 1882 . አፀደቁ፡፡ ይኼ ውል በመፅደቁ አፄ ምኒልክ ደግሞ በምላሹ አራት ሚሊዮን ፍራንክ ከኢጣሊያ ባንክ በኢጣሊያ መንግሥት ዋስትና ብድር እንዲያገኙ ተፈቀደላቸው፡፡

ጥቅምት 1 ቀን 1882 .. የኢጣሊያ መንግሥት ለአውሮፓ መንግሥታትና ለሕዝባቸው በጋዜጣ ኢትዮጵያ በኢጣሊያ ሞግዚትነት ሥር የምትተዳደር መሆኗን በይፋ አስታወቁ፡፡ ራስ መኮንን ይህንኑ የኢጣሊያ ጋዜጦች ዕትም በፕሮፌሰር አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ (በወቅቱ በኢጣሊያ ተማሪ የነበሩ ኢትዮጵያዊ ናቸው) በኩል አይተው ተቃውሞአቸውን ገለጹ፡፡ አንቶኔሊም ሁኔታውን ለማስተባበል ሞክሮ ለተማሪው አፈወርቅም ማስጠንቀቂያ እንዲደርሳቸው ተደረገ፡፡ እንግዲህ ይህ ሁሉ የሚያሳየው የኢጣሊያ መንግሥት የውጫሌ ውል 17ኛው አንቀጽ በሚስጥር እንዲያዝ መፈለጉን ነበር፡፡ በውጫሌው ውል 17ኛው አንቀጽ ላይ የነበረውን የትርጉም ስህተት ሆን ብለው ኢጣሊያኖች ኢትዮጵያን ቅኝ ግዛታቸው ለማድረግ እያወቁ ያደረጉት ማታለል መሆኑ ያበሳጫቸው አፄ ምኒልክ፣ 17ኛውን የውሉን ክፍል ፈጽመው የማይቀበሉት መሆናቸውን ለአንቶኔሊ ገለጹለት፡፡

 

በዚህ ምክንያት አንቶኔሊ በእጁ የነበረውን የውሉን ኮፒ በአፄ ምኒልክ ፊት ቀዶ ‹‹ውሉ ዋጋ የሌለው እንደሆነና ጦርነትም የማይቀር ነው›› በማለት ደንፍቶ ሲወጣ እቴጌ ጣይቱ ከት ብለው ስቀው፣ ‹‹ጦርነቱን የዛሬ ሳምንት አድርገው በዚህ ሚደነግጥልህ የለም…›› ብለው በታላቅ ቁጣ እንደመለሰሉለት ተጽፏል፡፡ አንቶኔሊም ከሦስት ቀናት በኋላ የኢጣሊያን አምባሳደር አስከትሎ ከአዲስ አበባ ወደ አገሩ ጉዞውን በመቀጠሉ በኢጣሊያና በኢትዮጵያ መካከል የነበረው የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ተቋረጠ፡፡ አፄ ምኒልክም በዚህ ላይ ሳይቆሙ አከታትለው አስፈላጊውን ዕርምጃ በመውሰድ ለኢጣሊያ ንጉሥ ኡምቤርቶ ኢትዮጵያ የኢጣሊያ ጥገኛ እንደማትሆን ግልጽ ደብዳቤ በመላክ ለማይቀረው የነፃነት ጦርነት ዝግጅታቸውን በይፋ ጀመሩ፡፡

የአድዋው ጦርነት ዘመቻና ዝግጅት

አፄ ምኒልክ መስከረም 7 ቀን 1888 . ከዚህ ቀጥሎ ያለውን የክተት አዋጅ በይፋ በነጋሪት አስነገሩ፡፡ ‹‹እግዚአብሔር በቸርነቱ እስካሁን ጠላትን አጥፍቶ አገር አስፍቶ አኖረኝ፡፡ እኔም በእግዚአብሔር ቸርነት ገዛኹ፡፡ እንግዲህ ብሞት ሞት የሁሉም ነውና ስለ እኔ ሞት አላዝንም፡፡ ደግሞ እግዚአብሔር አሳፍሮኝ አያውቅም፤ ወደፊትም ያሳፍረኛል ብዬ አልጠራጠርም፡፡ አሁንም አገር የሚያጠፋ፣ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት እግዚአብሔር የወሰነልንን ባሕር አልፎ መጥቷል፡፡ እኔም ያገሩን ከብት ማለቅ የሰውን ድካም አይቼ እስካሁን ዝም ብለው ደግሞ እያለፈ እንደ ፍልፈል መሬት ይቆፍር ጀመር፡፡

‹‹አሁንም በእግዚአብሔር ረዳትነት አገሬን አሳልፌ አልሰጠውም፡፡ የአገሬ ሰው ካሁን ቀደም የበደልሁህ አይመስለኝም፡፡ አንተም እስካሁን አላስቀየምኸኝም፡፡ ጉልበት ያለህ በጉልበትህ ዕርዳኝ፡፡ ጉልበት የሌለህም ለልጅህ፣ ለምሽትህ፣ ለሃይማኖትህ ስትል በሐዘን ዕርዳኝ፡፡ ወስልተህ የቀረህ ግን ኋላ ትጣላኛለህ፣ አልተውህም ማርያምን ለዚህ አማላጅ የለኝም፡፡ ዘመቻዬም በጥቅምት ነውና የሸዋ ሰው እስከ ጥቅምት እኩሌታ ድረስ ወረይሉ ከተህ ላግኝህ፤” አሉ፡፡ የሩቁንም አገር የጎጃሙንም፣ የደንቢያውንም፣ የቋራውንም፣ የበጌምድሩንም ከጨጨሆ በላይ ያለውን አገር ሁሉ አሸንጌ ድረስ ክተት ብለው አዘዙ፡፡ የሰሜንና የወልቃይት ጠገዴንም ሰው መቀሌ ድረስ ክተት ብለው አዘዙ፡፡ ከዚህ በኋላ ራስ መኮንን የሐረርጌን ጦር ይዘው በመስከረም እኩሌታ አዲስ አበባ ገቡ፡፡ ከጊቤ በታች ያለው አገር ጦር የወለጋው ሹም ፊታውራሪ ተክሌ ጦራቸውን ይዘው ገቡ፡፡

አፄ ምኒልክ አዋጃቸውን በመስከረም ወር ካስነገሩ በኋላ ለአገር ጥበቃ አጎታቸውን ራስ ዳርጌ ሣህለ ሥላሴን ሾመው እርሳቸው በጥቅምት 2 ቀን 1888 . ከአዲስ አበባ ተነስተው በጊዳ በኩል አድርገው ጥቅምት 18 ቀን ወረይሉ ከተማ ገቡ፡፡ ከዚያም ራስ ሚካኤልን፣ ራስ ወሌን፣ ራስ መኮንንን፣ ራስ መንገሻ አቲከምን፣ ራስ አሉላን፣ ዋግሹም ጓንጉልን፣ ደጃች ወልዴን፣ ፊታውራሪ ገበየሁን፣ ፊታውራሪ ተክሌን፣ ሊቀ መኳስ አድነውን፣ ቀኛዝማች ታፈሰን ‹‹ቀድማችሁ ወደ አላጌ ዝመቱ የሚቀላችሁ ከሆነ ወጉት፡፡ የሚከብዳችሁ ከሆነ ላኩብኝ፤›› ብለው አስቀድመው መላካቸውን ጸሐፊ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ ሲያረጋግጡ፣ አንዳንድ ጸሐፊዎች ደግሞ፣ ‹‹እኔ እስክመጣ ድረስ ከባችሁ ተቀመጡ እንጂ አትዋጉ፤›› በማለት ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ያመለክታሉ፡፡

 

የአድዋ ድል የጥቁር ሕዝቦች ነፃነት ብሥራት

በአፍሪካ የጦርነት ታሪክ ውስጥ ሁለት የተከበሩና የተደነቁ ጦርነቶች አሉ፡፡ አንደኛው ከሁለት ሺሕ ዓመታት በፊት ሰሜን አፍሪካዊው ሐኒባል-

አውሮፓውያንን ድል ያደረገበት ጦርነት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ከሁለት ሺሕ ዓመታት በኋላ ኢትዮጵያውያን ጀግኖች በአድዋው ጦርነት ወራሪውን የኢጣሊያንን ሠራዊት ድል ያደረጉበት ጦርነት ነው፡፡ የካቲት 23 ቀን 1888 .. ንጋት ላይ የአገሬን ነፃነት፣ ክብሬንና ታሪኬን አላስደፍርም ያለ ወገን በአንድ በኩል፣ በሌላ በኩል ደግሞ በእብሪት የተወጠረና ለሺሕ ዘመናት ታፍራና ተከብራ በነፃነት የቆየችውን ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ለመያዝ ያሰፈሰፉ ናቸው፡፡

ዘመናዊ የጦር መሣሪያን እስከ አፍንጫው የታጠቀ የኢጣሊያ የጦር ሠራዊት ከንቱ የሆነ ህልሙን አንግቦ በአድዋው ላይ ተጋጠሙ፡፡ በአድዋው ጦርነት ላይ በጀግንነት ከተዋጉትና ካዋጉት አፄ ምኒልክ፣ የጦር ሹማምንቶቻቸው፣ መኳንንቶቻቸውና ሠራዊታቸው ባሻገር በተለይ የእቴጌ ጣይቱ ጀግንነትና የጦር ብልኃትም በእጅጉ መጠቀስ የሚገባው ነው፡፡ እቴጌ ጣይቱ በጦር ዕቅድ አመንጪነታቸው፣ በጀግንነታቸውና በጥንካሬያቸው በምሳሌነት የሚጠቀሱ ሴት ነበሩ፡፡ እቴጌይቱ በሳል፣ ብልህ፣ ደፋርና ጀግና ሴት ነበሩም፡፡ በባለቤታቸውን በአፄ ምኒልክ አመራር ወቅትም በፊት ለፊትም ሆነ በጀርባ ሆነው በሳልና ውጤታማ የሆነ አመራር ይሰጡ የነበሩ ታላቅ ሴት እንደነበሩ የታሪክ ድርሳናት ይመሰክሩላቸዋል፡፡

እሑድ የካቲት 23 ቀን 1888 . በአድዋ የጦር አውድማ ለእናት አገራቸው ነፃነትና ክብር ሕይወታቸውን ለመስጠት ያልሳሱ ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ከጠላቶቻቸው ጋር አንገት ለአንገት ተናንቀው በአፍሪካ ምድር የነፃነትን ክቡር ሚስጥር በክቡር ደማቸው በአድዋ ተራሮች ላይ ጻፉ፡፡ የአድዋ ተራራ በኢትዮጵያውያን ጀግኖች ለሰው ልጆች ነፃነት በፈሰሰ ክቡር ደም አሸብርቃና ተውባ በአፍሪካና በመላው ዓለም ከፍ ብላ፣ ደምቃና ገና ታየች፡፡ ኢትዮጵያ በልጆቿ አይበገሬነት፣ ተጋድሎና ቆራጥነት በዓለም ምድር ዳግመኛ የነፃነት ምድር፣ የጥቁር ሕዝቦች የአይበገሬነት ተምሳሌት ሆና ዳግም በክብር ተሞሸረች፡፡ የዓለም ጋዜጦች ከአፍሪካ እስከ አሜሪካ፣ ከአውሮፓ እስከ እስያ፣ ከጀማይካ እስከ ካሪቢያን በአንድ ድምፅ ይህን ታላቅ የሆነ የአባቶቻችንን የነፃነት ተጋድሎ ሊያበስሩ ብዕሮቻቸውን ቀሰሩ፡፡ የአድዋውን ድል በመላው ዓለም ያሉ ጋዜጦች ሁሉ በመጀመሪያ ገጻቸው የምኒልክና የጣይቱን ፎቶግራፍ ፊት ለፊት በማውጣት ወሬውን ለዓለም ሁሉ አደረሱት፡፡

የአድዋ ድል የኢትዮጵያዊነት አንድነት ልዩ ህብር የጠላቶቻችንን ‹‹የከፋፍለህ ግዛው›› ተንኮል ሳይበግረው፣ የኢትዮጵያ መሳፍንቶች ጊዜያዊ ጠላትነት፣ ዘር፣ ጎሳ፣ ሃይማኖት፣ ፆታ፣ ወዘተ ሳይለያየው የአንዲት ኢትዮጵያ አንድነትና የሰንደቅ ዓላማችን ክብር ጎልቶ የወጣበት ድላችን ነው፡፡

ስለዚህም በልዩ የነፃነት ክብርና ልዕልና አድዋን ልንዘክረው ይገባናል፡፡ ለዛሬ ነፃነትና ክብር ምክንያት የሆነን የበርካታ አባቶቻችንና እናቶቻችን ደም የፈሰሰበት አጥንት የተከሰከሰበት ክቡር የነፃነት ሕይወት ነው፡፡

" ክብር እና ሞገስ ለጀግኖች አባቶቻችን! "

 

የመረጃ ምንጭ፡-ውክፔዲያ (https://am.wikipedia.org )

 

 

 

የአብክመ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የግማሽ አመት ዕቅድ ክንውን መገምገሙ ተገለጸ፡፡

የአብክመ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የግማሽ አመት ዕቅድ ክንውን መገምገሙ ተገለጸ፡፡

የካቲት 17/2009 ዓ/ም ጠቅላላ ሰራተኛው በተገኘበት የጽ/ቤቱ የ6 ወር ዕቅድ አፈጻጸም ተገመገመ፡፡

የጽ/ቤቱ ሪፖርት በዝርዝር የቀረበው በዕቅድ ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ኃላፊ በሆኑት በወ/ሮ ጥሩ ውበት ሲሆን የጽ/ቤቱ ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ተሰማ ደምሴም ሪፖርቱን መነሻ በማድረግ ጠቅላላ ሰራተኛውን አወያይተዋል፡፡ የጽ/ቤቱ ምክትል ኃላፊ እንደገለጹት ባለፉት 6 ወራት በተቋሙ ውስጥ ያሉት ሁሉም ሂደቶች የለውጥ ስራዎችን በአግባቡ ለመፈጸም ጥረት ማድረጋቸውን ገልጸው በቀጣይም በJEG መሰረት የተመደቡትን ሰራተኞች የዕውቀት፣የክህሎትና የአመለካከት ክፍተቶችን ለመሙላት የተለያዩ ስልጠናዎች መስጠት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡ እያንዳንዱ ሂደትም አፈጻጸሙ ያለበትን ደረጃ የሚገልጽ መለኪያ ማስቀመጥ እንደሚያስፈልግና የጽ/ቤቱን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የተቀናጀ ጥረት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡

በመጨረሻም ሰራተኛው ሪፖርቱን በዝርዝር ካዳመጠ በኋላ የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን በመስጠት ግምገማው ተጠናቋል፡፡

የዳያስፖራና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

 

ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዳያስፖራው ሊሳተፍባቸው የሚችሉና በጥናት የተለዩ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ፕሮፋይል (ዝርዝር)

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዳያስፖራው ሊሳተፍባቸው የሚችሉና በጥናት የተለዩ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ፕሮፋይል (ዝርዝር)

· የማር ማቀነባበሪያ ፋብሪካ /Honey Processing Factory/

· ስጋ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ /Meet processing/

· ምስማር ማምረቻ ፋብሪካ/Nail Producing Factory/

· የፕላስቲክ ቁልፍ ማምረቻ ፋብሪካ/Button Producing Factory/

· የፕላስቲክ ዝናብ መከላከያ ኮት ማምረቻ ፋብሪካ/Rain Coat Producing Factory /

· የዶሮ እርባታ ቁሳቁሶች ማምረቻ ፋብሪካ /Poultry Farm Equipment  Producing Plant/

· የፕላስቲክ ወለል ንጣፍ ፋብሪካ /PVC Floor Making Plant/

· የብረት ቧንቧ  ማምረቻ ፋብሪካ /Steel Pipe Producing Factory/

· የብረት ክምችት ፋብሪካ /Steel Profile Factory/

· የእንስሳት መድሃኒት ማምረቻ ፋብሪካ /Animal Medicine Producing Factory/

· የሰም ሻማ ማምረቻ ፋብሪካ /Wax Candle Producing Factory/

· ሽቦና የሽቦ ውጤቶች ማምረቻ ፋብሪካ /Wire And Wire Products Producing Factory/

· ውቭን ኬሻ ማምረቻ ፋብሪካ /H.D.P.E Woven Sacks Producing Factory/

· ባለ3 ጎማ ተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ፋብሪካ /3-Wheelers Assembly Plant/

· የአትክልት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ /Dehydrated Vegetable Processing Factory/

· ፒቪሲ ኬብል ማምረቻ ፋብሪካ /PVC Cable Producing Factory/

· የቆርቆሮ ኮንቴነር ማምረቻ ፋብሪካ /Tin Container Producing Factory /

· የቀርቀሃ ፈርኒቸር ማምረቻ ፋብሪካ /Bamboo Furniture Producing Factory/

· የድንጋይ መፍጫ ማምረቻ ፋብሪካ /Grinding Stones Production/

· ከብረት የተሰራ የማይዝግ መታጠቢያ ገንዳ ማምረቻ ፋብሪካ /Galvanized Iron Bathtubs Factory/

· የፕላስቲክ ማስተማሪያ ዕቃዎች ማምረቻ ፋብሪካ /Injection Molded Plastic Education Material Manufacturing Plant/

· Iron And Steel  Cot Making Plant

· የፕላስቲክ ዚፐር ማምረቻ ፋብሪካ  /Plastic Zipper Making Plant/

· የፕላስቲክ ወንበርና ጠረጴዛ ማምረቻ ፋብሪካ /Plastic Chairs And Tables Producing Plant/

· የፕላስቲክ ገተርና ኮንዲውት ማምረቻ ፋብሪካ /Plastic Gutters Down Pipes And Conduits Making Plant/

· የፕላስቲክ ንጽህና ዕቃዎች መገጣጠሚያ ማምረቻ ፋብሪካ /Plastic Sanitary Materials Assembly Producing Plant/

· የፕላስቲክ ታንክ ማምረቻ ፋብሪካ /Plastic Tank Producing Plant/

· ብሎን መፈብረክ  /Bolts And Nuts Producing Plant/

· የኮምፒተር መገጣጠሚያ  ፋብሪካ /Computer Assembly Plant/

· የዶሮ ምግብ ማምረቻ ኢንዱስትሪ /Poultry Feed Processing Industry)

· ፕላስቲክን እንደገና ለመጠቀም ማቀነባበሪያ ፋብሪካ (Recycled Plastic Processing Plant/

· የልብስ መስፊያ  ክር ማምረቻ ፋብሪካ  /Sewing Thread Producing plant/

· የቴሌቭዥን መገጣጠሚያ ፋብሪካ /Television Set Assembly Plant/

· የኤሌክትሪክ እቃዎች  ማምረቻ ፋብሪካ /Switch,Plug,And Socket Producing plant/

· ብረታ ብረት ማምረቻ ፋብሪካ /Small Scale Foundry Plant/

· የእብነ በረድ ምርት ማምረቻ /Marble Producing Plant/

· የፍራፍሬ ማቀነባበሪያና ማሸጊያ ማምረቻ /Fruit Processing And Canning Plant/

· የሌዘር ምርቶች ማምረቻ /Leather Products Producing Plant/

· በቆሎ ስታርች አምራች ፋብሪካ  /Maize Starch Producing Plant/

· የድርና ማግ ማምረቻ (Polyster Production Plant)

· የልብስ ስፌት መገጣጠሚያ አቅራቢና ማምረቻ /Sewing Machine Assembly Supplier Producing Plant/

· የእግር ሹራብ ማምረቻ /Socks Production Plant/

· የሹራብ ማምረቻ /Sweater Producing Plant/

· የትራክተር መገጣጠሚያ አቅራቢ /Tractor Assembly Supplier/

· የአልሚ ምግብ ማምረቻ /Nutrient Food Producing plant

· የጥጥ ሀር ማቀነባበሪያ /Cotton Polyester Processing/

· የኤሌክትሪክ አምፑል ማምረቻ ፋብሪካ /Electric Bulb Producing Plant/

· የጅፕሰም ማምረቻ /Gypsum Producing Plant/

· ORS ማምረቻ ፋብሪካ /ORS Producing Plant/

· የቀርቀሃ ዉጤቶች ማምረቻ /Bamboo Products Producing Plant/

· የብርድ ልብስ ማምረቻ ፋብሪካ /Blanket Producing Plant/

· ከተፈጨ አጥንት ማዳበሪያ ማምረቻ ፋብሪካ /Fertilizer Producing Factory From Grinded Bones/

· የወተት ምርት ማምረቻና ማቀነባበሪያ ፋብሪካ /Milk Products Producing And Processing Plant/

· ኤክስፖርትና ኤክስፖርት የሚሆኑ ዘመናዊ የጋርመንት ምርት ማምረቻ /Export Standard Modern Garment Products Producing Plant/

· የማዳበሪያ ማምረቻ ፋብሪካ /Organic Fertilizer Producing Plant /

· ፓስታና መካሮኒ ማምረቻ ፋብሪካ /Pasta And Macaroni Producing Factory/

· የመድሃኒት ፋብሪካ /Medicine Factory/

· የሰብል መዉቂያ (Mechanical Thresher)

· Steel Sabrication And Iron Work Plant

· በሰው ሃይል የሚሰራ ትራክተር /Establishment of Assembly & Fabrication of Walking Tiller/Tractor Plant/

· የደን ውጤቶች ማምረቻ /Plywood Producing Plant/

· የጠመኔ (Chalk) የማምረቻ ፋብሪካ

· የኤሌክትሪክ ውሃ ማሞቂያ

· የእህል ወፍጮ ማምረትና መገጣጣም

· የብረታ ብረት ፋብሪካ /Galvanized Iron Sheet Product Fabrication Plant/

· የፀረ-ተባይ ኬሚካሎች ፋብሪካ /Aerosol Insecticide Producing Plant/

· የማተሚያ ቀለሞች ፋብሪካ /Print Ink Making Plant/

· የሽንት ቤት ወረቀቶች /ሶፍት ማምረት ፋብሪካ/ /Soft Tissues Producing Plant/

· የሽንት ቤት ማጽጃ ሳሙና ፋብሪካ /Detergent Producing Plant/

· የቀለምና ቫርኒሽ ፋብሪካ /Paints Varnish And Pigment Making Plant/

· የወረቀት ካርቶን ማምረቻ ፋብሪካ /Straw Pulp And Yellow Board Making Plant/

· የቆዳና የፀጉር ቅባቶች ማምረቻ ፋብሪካ /Cosmetic Products Producing Plant/

· የዳቦና ኬክ ማቡኪያ እርሾ ማምረት ፋብሪካ /Baking Powder Production Plant/

· የህክምና ማምረቻ ድርጅት /Disposable Surgical Gloves/

· ዱቄትና ፈሳሽ የእቃ ማፅጃ ሳሙና ማምረት /Synthetic Detergent Production/

የካቲት/2009 ዓም

የዳያስፖራና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

 

የመረጃ ምንጭ፡-የአብክመ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን

Last Updated on Thursday, 23 February 2017 14:57
 


Page 10 of 17
Content View Hits : 9428383

Comments

  • Hmm іt looҝs like your website ate mmy first comme...
  • Thank you, I've recently been searching for inform...
  • Hmm іt looҝs like your website ate mmy first comme...
  • Hmm іt looҝs like your website ate mmy first comme...
  • Saved as a favorite, I really like your site! Feel...

Latest News

Who is online

We have 128 guests and 13 members online

Entertainment