የሶማሊያ አገር ከፍተኛ አመራሮችና የምክር ቤት አባላት በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መዲና ባህርዳር በፌዴራሊዝም ስርዓት ዙሪያ የልምድ ልውውጥ አካሄዱ፡፡

ሶማሊያ አገር ከፍተኛ አመራሮችና የምክር ቤት አባላት በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መዲና ባህርዳር በፌዴራሊዝም ስርዓት ዙሪያ የልምድ ልውውጥ አካሄዱ፡፡

ከጎረቤት አገር ሶማሊያ ከፍተኛ አመራሮችና የምክር ቤት አባላት ጋር የተካሄደውን የልምድ ልውውጥ በንግግር የከፈቱት የአማራ ብሄራዊ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ የተከበሩ አቶ ይርሳው ታምሬ እንደገለፁት አገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት 25 ዓመታት በፌዴራሊዝም ስርዓት ቆይታለች በዚህም የህዝቦችን መፈቃቀር፤ የህዝቦችን የመልማት ፍላጎትና አቅም ለማጠናከር በመቻላችን አገራችን በልማት ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ከሚገኙ ሃገራት መካከል አንዷ ልትሆን ችላለች ብለዋል፡፡

እንደ አቶ ይርሳው ገለፃ በፌዴራሊዝም አወቃቀር ከተደራጁ ክልሎች መካከል አንዱ የሆነው የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሃገሪቱ የኢኮኖሚና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ውስጥ ጉልህ ድርሻ ያለው ክልል ነው፡፡
በመሆኑም ክልሉ ባለፉት 25 ዓመታት የክልሉን ህብረተሰቡን ተጠቃሚና ተሳታፊ ለማድረግ የሄደባቸውን እንቅስቃሴዎች በተመለከተ መልካም ነገሮችን ብቻ ሳይሆን በፌዴራሊዝም ስርዓት ውስጥ ስንቆይ የገጠሙንን ተግዳሮቶች ጭምር አውቃችሁ ከወዲሁ እንድትዘጋጁ የሚጠቅም እና እኛም ከእናንተ ልምድ የምንወስድበት በመሆኑ የልምድ ልውውጡ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳድር /ቤት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የርዕሰ መስተዳድሩ ከፍተኛ የህግ አማካሪ አቶ መርሃ ፅድቅ መኮንን እና የክልሉ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ጥላሁን መሓሪ ክልሉ ያለበትን አጠቃላይ ደረጃ የሚገልፅ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ከጎረቤት አገር ሶማሊያ ከፍተኛ አመራሮችና የምክር ቤት አባላት ጥያቄዎች ቀርበው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በጎረቤት አገር ሶማሊያ የሃገር ውስጥ ሚኒስትርና የፌዴራሊዝም ቋሚ ሚኒስትር ሴክሬታሪያት እንዲሁም የልዑካን ቡድኑ መሪ አቶ አብዱላሂ መሃመድ ሁሴን እንደገለጹት ባጠቃላይ በፌዴራሊዝም ስርዓት ውስጥ በህግ አውጭው፤ በህግ ተርጓሚው፤ በህግ አስፈጻሚው የአሰራር ስርዓት ዙሪያና እንዲሁም የፌዴራሊዝም ስርዓት ለብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች እኩልነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ያለውን ጠቀሜታ ለመረዳት ችለናል በመሆኑም ለኢትዮጵያን መንግስትና የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምስጋናችንን ከፍተኛ ነው ብለዋል ፡፡

 

በመጨረሻም የልዑካን ቡድኑ አባላት በባህር ዳር ከተማ የተለያዩ የልማት ስራዊችን ጎብኝተው ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡

 

የሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ማጣራትን በተመለከተ የተደረሰበት ደረጃና ውሳኔ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ውሳኔ መሰጠቱ ተገለጸ፡፡

የሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ማጣራትን በተመለከተ የተደረሰበት ደረጃና ውሳኔ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ውሳኔ መሰጠቱ ተገለጸ፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት 5 ዙር 3 አመት የስራ ዘመን ሐምሌ 21 ቀን 2009 / ባካሔደው 2 መደበኛ ስብሰባ በክልሉ ውስጥ ሀሰተኛ የትምህርት፣ የመንጃ ፈቃድ፣ የስራ ልምድና የብቃት ማረጋገጫ  ማስረጃዎች ማጣራትን በተመለከተ የተደረሰበት ደረጃና ውሳኔ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ውሳኔ መስጠቱን ገለጸ፤

ውይይቱ የተጀመረው የስቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አወቀ እንየው ባቀረቡት  ማብራሪያ ሲሆን፤ በማብራሪያቸውም በሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በኩል በተጠናው ጥናት መሰረት በክልሉ ውስጥ ሀሰተኛ የትምህርት፣ የመንጃ ፈቃድ፣ የስራ ልምድና የብቃት ማረጋገጫ  ማስረጃዎች መኖራቸው በመረጋገጡ በተደራጀ መልክ እርምጃ ለመውሰድ ያስችል ዘንድ የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት መመሪያ ማውጣቱን ገልጸዋል፡፡  እንደ ምክትል ኃላፊው ገለጻ በመመሪያው መሰረት በመጀመሪያው የይቅርታ ምዕራፍ ከሰኔ 15 እስከ ሐምሌ 14 ቀን 2009 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ሰራተኞችና ኃላፊዎች ራሳቸውን የሚያጋልጡበት ጊዜ ሲሆን ይህንን ጊዜ በመጠቀም 468 የክልሉ የመንግስት ሰራተኞች ራሳቸውን ማጋለጣቸውንና በመመሪያው መሰረት እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን፤  እንዲሁም በሁለተኛው ምዕራፍ ማለትም ከሐምሌ 15 እስከ ነሐሴ 14 ቀን 2009 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በጥቆማ መልክ መረጃ ለማሰባሰብ የሃሳብ መስጫ ሳጥንና ነጻ የስልክ መስመር አገልግሎት የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዚህ መሰረት በመጀመሪያው ምዕራፍ ራሳቸውን ሲያጋልጡ በነበረበት ወቅት ብዙዎቹ በመጨረሻው ቀን የመጡ በመሆኑ ከዚህ በመነሳት ራስን ለማጋለጥ የተሰጠው ቀነ ገደብ ቢራዘም የበለጠ ተነሳሽነት ይኖረዋል የሚልና በሌላ በኩል ደግሞ ጊዜው በተራዘመ ቁጥር መዘናጋትን ሊፈጥር ስለሚችል መራዘም የለበትም የሚል ሃሳብ እንዳለና፣ በሌላ በኩል ደግሞ ቋራና ሳሃላ ወረዳዎች በተለያየ ምክንያት መረጃው ዘግይቶ ስለደረሳቸው የመጀመሪያውን የይቅርታ ጊዜ መጠቀም ስላልቻሉ መራዘም የሚችልበት ሁኔታ እንዲመቻች የቀረበ ጥያቄ በመሆኑ መስተዳድር ምክር ቤቱ በቀረቡት ጉዳዮች ላይ መክሮ አቅጣጫ እንዲያስቀምጥ ጠይቀዋል፡፡

 

መስተዳድር ምክር ቤቱ በቀረቡት ሃሳቦች ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን በማንሳት ሰፊ ውይይት ካካሄደ በኋላ የሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ይዘው ያለአግባብ እየተጠቀሙ ያሉ የክልሉ ሰራተኞችና አመራሮች በተደራጀ መንገድ እርምጃ ለመውሰድ እየተካሄደ ባለው እንቅስቃሴ የመጀመሪያው የይቅርታ ምዕራፍ ለተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም የቀረበውን ሃሳብ በተመለከተ የተጀመረውን ሥራ ተጨማሪ ጊዜ ሰጥቶ ማራዘም ሳያስፈልግ ግብረ-ሃይሉ ባስቀመጠውና በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ውሳኔ መሰረት መቀጠል እንዳለበት፤ በሌላ በኩል ደግሞ ከመጀመሪያውም ቢሆን በተለያየ ምክንያት መረጃው ዘግይቶ የደረሳቸው ቋራና ሳሀላ ወረዳዎች ለሌሎች የተሰጠውን የይቅርታ ምዕራፍ ጊዜ መጠቀም ስላለባቸው መረጃው ከደረሳቸው ቀን ጀምሮ ያለው ጊዜ ተይዞ ለሌሎች የተሰጠውን የመጀመሪያውን የይቅርታ ምዕራፍ ጊዜ ያህል እንዲጠቀሙ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

 

የአማራ ክልል የስነ-ህዝብ ጉዳዮች ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ መካሄዱ ተገለጸ፡፡

የአማራ ክልል የስነ-ህዝብ ጉዳዮች ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ መካሄዱ ተገለጸ፡፡

ሀምሌ 12 ቀን 2009 ዓ.ም የአማራ ክልል የስነ-ህዝብ ጉዳዮች ምክር ቤት "የሰው ሃብት ልማት ለስነ-ህዝብ መልካም አጋጣሚ የላቀ ደረጃ ተጠቃሚነት" በሚል መሪ ቃል መደበኛ ጉባኤውን አካሄደ፡፡

ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የአንድ አገር እድገት መሰረታዊ መለኪያ የህዝቡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ነው፣ የአንድ አካባቢ አገር ሊያሰኘው የሚችለው መሰረቱ ህዝብ በመሆኑ የስነ-ህዝብ ጉዳዮች ምክር ቤት አባላት በጉባኤው ላይ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ሃሳባቸውን ገልጸዋል፡፡

የአማራ ክልል ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ በድሉ ድንገቱ የክልሉ የስነ-ህዝብ ጉዳዮች ተግባራት አፈጻጸም ከስነ-ህዝብ ፖሊሲው አንጻር ያለበትን ደረጃ በሪፖርታቸው ገልጸው በክልሉ የውልደትና ሞት መጠን እየቀነሰ መጥቷል አማካኝ የመኖር ዕድሜ እየጨመረ ነው፤ የህዝብ ቁጥር የዕድገት ምጣኔም እንደ አሮፖያን ዘመን አቆጣጠር በ1994 ከነበረበት 3 በመቶ አሁን 1.74 በመቶ ደርሷል ብለዋል፡፡

አቶ በድሉ እንደገለጹት በትምህርት፣በጤና እና በስርዓተ-ጾታ ጉዳዮች እድገት የታየ ሲሆን፤ በከተሜነት ምጣኔ ወደ ኋላ መቅረት ይታያል፤ ከጤናው ዘርፍ ጋር በተገናኘም የመቀንጨር ምጣኔ 46.3 በመቶ ነው ከሁሉም ክልሎች የበለጠ ነው ይህ በምክር ቤቱ አባላት በኩል በአሳሳቢነት የሚታይ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

በተያያዘም ለ4ኛ ጊዜ በሚካሄደው የህዝብና ቤት ቆጠራ በክልል ያለውን ዝግጅት የሚያሳይ ሪፖርት ቀርቧል፡፡ የምክር ቤት አባላትም አስተያየታቸውን አንስተዋል፡፡

 

የአማራ ክልል የስነ-ህዝብ ጉዳዮች ምክር ቤት በ2006 ዓ.ም በአዋጅ መቋቋሙ ይታወሳል፤ ከተቋቋመበት ጊዜ አንጻር እንቅስቃሴው የሚመሰገን ቢሆንም በቀጣይ ከዚህ በተሻለ መደራጀት እንዳለበት የምክር ቤቱ አባላት አሳስበዋል፡፡

 

የአማራ ክልል ምክር ቤት ለ2010 በጀት አመት 37 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር አጸደቀ

የአማራ ክልል ምክር ቤት 2010 በጀት አመት 37 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር አጸደቀ

የአማራ ክልል ምክር ቤት 5 ዙር 2 ዓመት የስራ ዘመን 7 መደበኛ ጉባኤ 4 ቀኑ የቀጣይ አመት በጀቱን አጽድቋል፡፡

 


የአማራ ክልል ምክር ቤት 7 መደበኛ ጉባኤው 2010 በጀት አመት 37ቢሊዮን 693ሚሊዮን 142 ሺህ 155 ብር አድርጎ አጽድቋል፡፡ካለፈው አመትም 15 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

 

አዲስ የተከፈሉ 11 ወረዳዎች ወደ ስራ እንዲገቡ መወሰኑ ተገለጸ

አዲስ የተከፈሉ 11 ወረዳዎች ወደ ስራ እንዲገቡ መወሰኑ ተገለጸ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት 5ኛ ዙር 2ኛ አመት የስራ ዘመን ሰኔ 16 ቀን 2009 ዓ/ም ባደረገው 22ኛ መደበኛ ስብሰባ አዲስ የተከፈሉ ወረዳዎችን ወደ ስራ ለማስገባት አስፈላጊውን ነገር ለማሟላት ውሳኔ መሰጠቱን አስታወቀ፡፡

ውይይቱ የተደረገው ሰብሳቢው በሰጡት የመነሻ ሀሳብ ሲሆን ባለፈው ዓመት በአዲስ ተደራጅተው በዚህ ዓመት የአስተዳደር ሲቪል ሰርቪስ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብርና አፈ-ጉባዔ ጽ/ቤቶች አደረጃጀት ተፈቅዶላቸው ወደ ስራ እንዲገቡ የተፈቀደላቸው 11 ወረዳዎች በቀጣይ ከሀምሌ 1/2009 ዓ/ም በሙሉ አቅም ስራ መጀመር ስላለባቸው በጀታቸውም ከዚህ አኳያ ታይቶ በቀመር ድጋፍ ሊደረግላቸው የሚገባ በመሆኑ ወረዳዎቹ በተመጠነ ሁኔታ አደረጃጀት እንዲሰራላቸው ወረዳዎቹ ሲደራጁም በተመጠነና ጥቂት የሰው ኃይል እንዲይዙ በሚያደርግ አግባብ እንዲደራጁ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ መዋቅሩን አዘጋጅቶ እንዲያወርድና ፈጥነው ወደ ስራ የሚገቡበትን ሁኔታ እንዲያመቻች ሆኖ የሚደራጁት ሴክተሮችም ዋና ዋና አገልግሎት የሚሰጥባቸው ሆነው እንዲደራጁና አስፈላጊ ናቸው ተብለው የተፈቀዱ መደቦችን ባካተተ ሁኔታ መዋቅሩ እንዲሰራ ለምክር ቤቱ የውሳኔ ሀሳብ መሆኑን ቀርቧል፡፡

 

መስተዳድር ምክር ቤቱም በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ ከተወያየ በኋላ በቀረበው አቅጣጫ መሰረት የወረዳዎች መዋቅር በተመጠነ አግባብ ተሰርቶ ከሀምሌ 1/2009 ዓ/ም ጀምሮ 11ዱ ወረዳዎች በሙሉ አቅም ወደ ስራ እንዲገቡ እንዲደረግ ወስኗል፡፡

 


Page 7 of 17
Content View Hits : 9428377

Comments

  • Hmm іt looҝs like your website ate mmy first comme...
  • Thank you, I've recently been searching for inform...
  • Hmm іt looҝs like your website ate mmy first comme...
  • Hmm іt looҝs like your website ate mmy first comme...
  • Saved as a favorite, I really like your site! Feel...

Latest News

Who is online

We have 132 guests and 13 members online

Entertainment