በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ሰራተኞችና አመራሮች 10ኛውን የሰንደቅ ዓለማ ቀን በፓናል ውይይት አክብረዋል

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የርዕሰ መስተዳድር /ቤት ሰራተኞችና አመራሮች 10ኛውን የሰንደቅ ዓለማ ቀን በፓናል ውይይት አክብረዋል፡፡

በምክትል ኤጀንሲ ስራ አስኪያጅ ደረጃ የዳያስፖራና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አውላቸው ማስሬ "የኢትዮጵያ ህዝቦች ትግልና ሀገራዊ ህዳሴያችን" በሚል ርዕሰ ጉዳይ የመወያያ ጽሁፍ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በፓናል ውይይቱ የተገኙት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ያየህ አዲስ ሰንደቅ ዓላማ የአንድ አገር ህዝቦች የማንነት መገለጫ ሲሆን በአንድ ወቅት ከፍ ወዳለ የስልጣኔ ማማ የወጣቸው ሀገር በታሪክ አጋጣሚ በተፈጠረ አለመረጋጋት የኢኮኖሚ ድቀት የድህነት መገለጫ ሆና ቆይታለች ብለዋል፡፡

አገራችን ኢትዮጵያ ከነበረችበት የቁልቁለት ጉዞ ወደ ዕድገት ማማ እየገሰገሰች ያለች ሀገር መሆን ችላለች ያሉት አቶ ያየህ አዲስ በኢኮኖሚ ዕድገት፣ በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እንዲሁም ብዝሃነትን በማስተናገድ በኩል በአለም አቀፍ ደረጃ ተጠቃሽ ሀገር መሆን ችላለች ሰንደቅ አላማዋም ከፍ ብሎ መውለብለብ ጀምሯል ብለዋል፡፡

አክለውም ይህን ክብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ሁሉም በተሰማራበት የስራ ዘርፍ ውጤታማ ስራ በመስራት አባቶቻችን ያስተማሩን ለሰንደቅ አላማ መስዋዕትነት መክፈል አዲሱ ትውልድ የሰንደቅ አላማን ፋይዳ እንዲረዳ በማድረግ ድህነትን በማሸነፍ ሰንደቅ አላማችን ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ማድረግ ከሁሉም ዜጋ የሚጠበቅ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

 

በፓናል ውይይቱ ከተገኙት ተሳታፊዎች መካከል አቶ መርሀጽድቅ መኮነን እና አቶ ሞገስ አያሌው እንደተናገሩት ትውልዱ የአዲሲቷን ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ መርሆችና እሴቶች አንግቦ እና ሰንደቋን ጨብጦ አገሩን ቀጣይነት ወዳለው ከፍታ ማማ እያወጣት ይገኛል፤ ዋነኛ ጠላታችን የሆነውን ድህነትን ለማሸነፍ በተያያዝነው ጠንካራ ትግል የህዝቦች የአንድነት ህብረቀለም ሆና እያገለገለች ያለችውን ይህቺው ሰንደቅ ዓላማችን በመሆኗ ልንጠብቃት፣ ልንንከባከባትና አስፈላጊም ከሆነ የህይወት መስዋዕትነት ልንከፍልላት የምትገባ ቅርሳችን ናት ብለዋል፡፡

 

የአማራ ክልል መንግስት ከሰሜን ሱዳን ገዳሪፍ ግዛት ጋር በንግድ፣ ልማትና በኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ዙሪያ ላይ ውይይት ማካሄዱ ተገለጸ

የአማራ ክልል መንግስት ከሰሜን ሱዳን ገዳሪፍ ግዛት ጋር በንግድ፣ ልማትና በኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ዙሪያ ላይ ውይይት ማካሄዱ ተገለጸ፡፡

የአማራ ክልል መንግስት ከሰሜን ሱዳን ገዳሪፍ ግዛት ዋና አስተዳዳሪ እንጂነር መርጋኒ ሳሊህ እና በዋና አስተዳዳሪው የሚመራው የሰሜን ሱዳን ገዳሪፍ ግዛት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በንግድ፣ በልማትና በኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ዙሪያ ላይ በባህር ዳር ተገኝተው ውይይት ማካሔዳቸውን የአብክመ ርዕሰ መስተዳድር አሳወቀ፡፡

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በምክክር መድረኩ እንደተናገሩት የገዳሪፍ ግዛት ከፍተኛ የልዖካን ቡድን እና የአማራ ክልል አቻው ከሁለቱ ጎረቤት ሀገሮች አልፎ በዓለም አጀንዳዎች ሊመክር የሚገባው በመሆኑ በዋናዋና ጉዳዮች ላይ ግልጽና አጭር ውይይት በማድረግ ሁለቱን ቀጠናዎች የሚጠቅሙ የቀጣይ አቅጣጫዎችን ጭምር ማስቀመጥ ይገባናል ብለዋል፡፡

አቶ ገዱ አያይዘውም የሁለቱ ሀገሮች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ረጅም ጊዜ ያስቆጠረና የቆየ ወዳጅነት ያለው በመሆኑ አልፎ አልፎ የሚፈጠሩ ትንንሽ ችግሮች የሁለቱም ግዛቶች አመራሮች በውይይት ሊፈቱት የሚገባ እንጅ ወደ ከፋ ነገር ሊሄድ አይችልም ብለዋል፡፡

የሰሜን ሱዳን ገዳሪፍ ግዛት ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር መርጋኒ ሳሊህ ሳይድ አህመድ በበኩላቸው ልማታችሁ ጥሩ እየሄደ መሆኑን እናደንቃለን በተለይ በአባይ ወንዝ ላይ የሚሰራው ስራ ማሳያ ነው ካሉ በኋላ በሰሜን ሱዳን ገዳሪፍ ግዛት እና በአማራ ክልል  በኩል ያለው ግንኙነት ጥሩ መሆኑን ገልጸው በትምህርት፣ በጤና፣ ነጻ ገበያ ለማቋቋም በሚኖረው የነጻ ገበያ ልውውጥ ነጻ እንዲሆን፣ ህገ- ወጥ የንግድ ልውውጥ እንዳይኖር ማንኛውም ችግር እንዳይፈጠር ተቀናጅተን እንሰራለን ብለዋል፡፡

ዋና አስተዳዳሪው አክለውም በሁለቱም አካባቢ ጥሩ የሆነ ግንኙነት ስላለ የሽርክና ማህበር ለማቋቋም እንፈልጋለን፣ በእናንተ በኩል ኢንቨስት ማድረግ የሚፈልግ ካለ እንፈቅዳለን እኛ ወደ እናንተ ኢንቨስት ለማድረግ ፈቃደኛ ነን በማለት ገልጸዋል፡፡

በዋና አስተዳዳሪው የተመራው ልዑካን ቡድን የገዳሪፍ ፖሊስ አዛዥ የመከላከያ ሠራዊት ኃላፊ እና የደህንነት ኃላፊው ጀኔራል መሀመድ ጦይብ በኢትዮጵያ እየተሠሩ ያሉ ልማቶች እንዳስደሰታቸው ገልጸው፣ የሁለቱ ቀጠናዎች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ታሪካዊና በወንድማማችነት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ በመሆኑም በደንበር አካባቢ በተለይ ከአርሶ አደሩ ጋር የሚያጋጥመንን አለመግባባቶች አመራሮች በግልጽ ተወያይተን አቅጣጫ አስቀምጠን ግንኙነታችን በልማትና የሁለቱን ቀጠናዎች ጥቅሞች በሚያሳድጉ ጉዳዮች ላይ መሆን አለበት ብለዋል፡፡

 


በአማራ ክልል በኩልም ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ የማዕከላዊ ጎንደር ዋና አስተዳዳሪ፣የክልሉ ግብርና፣ የባህልና ቱሪዝም፣ የአስተዳደርና ጸጥታ፣ የፖሊስና የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ ኃላፊዎች በምክክሩ ላይ የተገኙ ሲሆን፣ በሁለቱ ቀጠናዎች ያሉ ህዝቦች ለሚፈጠረው ችግር ሁሉ ለሚመለከተው አካል መረጃ በመስጠት በውይይት እንዲፈታ የማድረግ ኃላፊነት እንዳለባቸው አሳስበው፡፡

 

በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የቤት መስሪያ ቦታ አሰጣጥ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ ውሳኔ መሰጠቱ ተገለጸ

በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የቤት መስሪያ ቦታ አሰጣጥ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ ውሳኔ መሰጠቱ ተገለጸ፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር ም/ቤት 5ኛ ዙር 3ኛ አመት የስራ ዘመን ነሀሴ 19/2009 ዓ/ም ባደረገው 4ኛ መደበኛ ስብሰባ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ አሰጣጣጥ ማሻሻያ ረቂቅ መመሪያ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ መሰጠቱ ተገለጸ፡፡

ስብሰባው የተጀመረው የከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ ባቀረቡት ማብራሪያ ሲሆን በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በማህበር ተደራጅተው የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ለማግኘት የሚያስችላቸው መመሪያ ቁጥር 22/2007 ዓ/ም በመስተዳድር ም/ቤቱ የወጣ ቢሆንም እስከ አሁን ድረስ ጥያቄ ያቀረቡና የመመሪያውን መስፈርት አሟልተው የተመዘገቡ ዳያስፖራዎች እንደሌሉና ለመመዝገብ ዋናው ምክንያትም በመመሪያው ላይ የተቀመጡትን የቤት አይነቶች የግንባታ ወጭ ቅድሚያ 100% በመክፈል በዝግ አካውንት በባንክ ለማስቀመጥ አቅማችንን ያገናዘበ ባለመሆኑ ይሻሻልልን የሚል ጥያቄ ያላቸው በመሆኑ ቢሮው ከዳያስፖራ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ጋር በጋራ በመነጋገር መመሪያው ላይ ማሻሻያ ተደርጎ የቀረበ መሆኑን ገልጸው ማሻሻያው በዋናነት ከክፍያና ከቦታ መጠን ጋር የተያያዘ እንደሆነ አብራርተው ማሻሻያው እንዲጸድቅላቸው ጠይቀዋል፡፡

መስተዳድር ም/ቤቱም በቀረበው ጉዳይ ላይ የተለያዩ ሀሳቦችን በማንሳት በሰፊው ከተወያየ በኋላ በወጣው መመሪያ ላይ አላሰራ ያሉ ችግሮችን ፈትሾ ማሻሻያ ማድረግ ተገቢ በመሆኑ የቀረበው በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ አሰጣጥ ማሻሻያ ረቂቅ መመሪያ በቀረበበት መልኩ ተሻሽሎ ተግባራዊ እንዲደረግ ወስኗል፡፡

 

 

 

የአማራ ክልል አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ፡፡

የአማራ ክልል አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ፡፡

አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት ነሐሴ 29 ቀን 2009 ዓ.ም ባካሄደው 5ኛ ዙር ሦስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የ2010 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ1 ሺህ 981 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን ገለፀ

 

ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎችም የወንጀልን አስከፊነት የተገነዘቡና ከወንጀል ድርጊት ለመታረም ያላቸውን ዝግጅት በመመዘን የይቅርታ መስፈርቱን ያሟሉ ሲሆኑ፣ ወደ ህብረተሰቡ ሲቀላቀሉ ሰላማዊና አምራች ዜጋ እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚገባም ተናግረዋል።

 

የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ሠራተኞችና አመራሮች በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እና በወቅታዊ የበሽታው ስርጭት ዙሪያ ውይይት አደረጉ

የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ሠራተኞችና አመራሮች በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እና በወቅታዊ የበሽታው ስርጭት ዙሪያ ውይይት አደረጉ፡፡

ነሐሴ 18/2009 ዓ.ም በአማራ ክልል የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ሠራተኞችና አመራሮች ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ያለበትን ደረጃ በተመለከተና በወቅታዊ የበሽታው ስርጭት ዙሪያ ውይይት ማድረጋቻው ተገለጸ፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የኤች አይ ቪ/ኤድስ ዘርፈ ብዙ ምላሽ ማስፋትና ማጠናከር ባለሙያ አቶ መልካሙ ዳኛው እንደገለጹት የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል የሚደረገው እንቅስቃሴ ተቀዛቅዟል፡፡ በዚህም በሽታው ጠፍቷል በሚል ደረጃ መዘናጋት እየተፈጠረ ሰዎች ወደ ስህተት እየገቡ ነው፡፡ የቫይረሱ ስርጭት የመቀነስ አዝማሚያ ቢያሳይም አንዳንዶቹ ጠፍቷል በሚል ልቅ ወሲባዊ ግንኙነት በመፈጸም የቫይረሱን ስርጭት እንደገና በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያገረሽ እያደረጉት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በተለይ የትራንስፖርት ኮሪዶር በሚባሉ ታላላቅ ከተሞች የተጠናን የጥናት ውጤት መነሻ በማድረግ የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ለአብነት ምንጃር ሸንኮራ 4.5%፣ምዕራብ አርማጮሆ 4.4%፣ባህር ዳር 3.7%፣ደቡብ አቸፈር 3.1% የስርጭት መጠን እንዳላቸው አብራርተዋል፡፡

በጥናቱ ከተካተቱ ከተሞች መካከል በሴተኛ አዳሪዎች ደረጃ ይበልጥ  ተጋላጭ  በሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ያለው የስርጭት ሁኔታ አስደንጋጭ ውጤት የተመዘገበው በባሕር ዳርና በኮምቦልቻ ከተሞች ሲሆን በጥናቱ መሰረት በባሕር ዳር 32%፣ በኮምቦልቻ ደግሞ 29% ሴተኛ አዳሪዎች በደማቸው ውስጥ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ያለባቸው መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

የአገራችንን ልማት ለማፋጠን ዋነኛው የሰው ሀብት ልማት ከመሆኑ አንጻር ኤች.አይ.ቪን መግታት የልማቱ ኃይል የሆነውን ህብረተሰብ መታደግና ጤንነቱን መጠበቅ ከልማቱ ተነጥሎ የሚታይ ጉዳይ  አይደለም፡፡ በመሆኑም የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል ሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶች የኤች.አይ.ቪን መከላከልና መቆጣጠር ፕሮግራምን እንደ መደበኛ ስራ በማቀድ መስራት፣በጀት መመደብ፣አፈጻጸሙን መገምገምና ጉዳዩን የጋራ ማድረግ የሚገባቸው መሆኑን አቶ መልካሙ  አመልክተዋል፡፡

በሌላ በኩል የተላላፊ በሽታዎች ክትትል ባለሙያ የሆኑት አቶ ተክለ ኃይማኖት ስለ አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት/አተት/ ምንነት የመወያያ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡ አቶ ተክለ ኃይማኖት  እንደገለጹት አተት ከተቅማጥ በሽታዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን፣ በአይን በማይታዩ ተሕዋስያን  የሚመጣ በሽታ ነው፡፡ በመሆኑም በፍጥነት በመዛመት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሞት ሊዳርግ የሚችል በሽታ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የአተት በሽታ ዋናው ምልክት በድንገት የሚከሰት ብዛት ያለው አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ሲሆን አተት ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችንና ፈሳሽን በተደጋጋሚና አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ስለሚያስወጣ የሰውነት ፈሳሽንና ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን መጠን ያዛባል፡፡ በመሆኑም የሰውነት ድርቀት፣ የአፍ መድረቅ፣ የአይን መሰርጎድ፤ የእንባ መድረቅ፤ የሽንት መቀነስ፣ የቆዳ መሸብሸብና፣ የእግር መቀረጣጠፍ፣ አጠቃላይ የሆነ የድካም ስሜት ያስከትላል ብለዋል፡፡

ይህን የአተት በሽታ መከላከ በውሃ ማከሚያ መድሃኒት የታከመ ውሃ መጠቀም ምግብን በሚገባ አብስሎ በትኩስነቱ መመገብ የምግብ ዕቃዎች ንጽህና መጠበቅ መፀዳጃ ቤትን በአግባቡ መጠቀም እጅን በወሳኝ ወቅቶች በሣሙና በሚገባ መታጠብ ማናቸውንም ከቤት የሚወጣ ደረቅ ወይም ፈሳሽ ቆሻሻ ውሃን እንዳይበክል በአግባቡ በተመደበለት ስፍራ ማስወገድ በዚህ በሽታ የተያዘ ሰው በፍጥነት ወደ ሕክምና ተቋም መዉሰድ እና ከበሽተኛው ከሚወጣ ፈሳሽ ጋር ንክኪ ያላቸውን እቃዎችና ቦታዎችን በአግባቡ ማጽዳት ሲሆን እነዚህን የመከላከያ መንገዶችን ተግባራዊ በማድረግ የአተትን መተለለፊያ ሰንሰለት ማቋረጥ ይቻላል በማለት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ሠራተኞችም በቀረበው ጽሁፍ ላይ አስተያየቶችን ሰጥተዋል፣ጥያቄዎችንም አቅርበው በባለሙያው ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡

ነሀሴ 18/2009 ዓ.ም

የዳያስፖራና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

 


Page 6 of 17
Content View Hits : 9428076

Comments

  • Goood day! D᧐ you use Twitter? I'd like tto follow...
  • Very good post! We will be linking to this particu...
  • I am really loving the theme/design of your weblog...
  • I as well as my pals happened to be following the ...
  • It's a shame yyou dоn't have a donate button! I'd ...

Latest News

Who is online

We have 120 guests and 15 members online

Entertainment