የኳራንታይን አገልገሎት ክፍያ ተመን መጽደቁ ተገለጸ፡፡

የኳራንታይን አገልገሎት ክፍያ ተመን መጽደቁ ተገለጸ፡፡

የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት 5ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን ህዳር 15 ቀን 2010 ዓ.ም ባደረገው 10ኛ መደበኛ ስብሰባ የኳራንታይን አገልገሎት ክፍያ ተመን ማጽደቁን ገለጸ፡፡

የአማራ ክልል የእፅዋት፣ ዘርና ሌሎች የግብርና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥርና ኳራንታይን ባለስልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሙሉጌታ ደባሱ እንደገለጹት የዕፅዋት፣ ዘርና ሌሎች  የግብርና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥርና ኳራንታይን ባለስልጣን በመስክ የዘር ጥራት ቁጥጥር፣ ላብራቶሪ ፍተሻ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የአገልግሎት ክፍያ እንዲያስፈጽም በዘር ደንብ ቁጥር 661/2008 እና በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዕቃና የአገልግልት ክፍያ መመሪያ ቁጥር 7/2004 የተፈቀደ ቢሆንም በመደበኛነት የማይከናወንና ለእቃውና ለአገልገሎቱ የሚጠይቀው የተናጠል ዋጋ ከብር 50 በላይ በሚሆንበት ጊዜ በመመሪያው አንቀጽ 6(3) (ሐ) በተደነገገው መሰረት የመንግስት  መስሪያ ቤቶች ማንኛውም የእቃ እና የአገልግሎት ክፍያ ማስከፈል የሚቻለው ለገንዘብና ኢኮኖሚ  ትብብር ቢሮ የውሳኔ ሃሳብ ቀርቦ መስተዳድር ምክር ቤቱ ሲፈቅድ ብቻ በመሆኑ መስተዳድር ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ መክሮ እንዲፈቅድ የቀረበ ጥያቄ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ዋና ሥራ አስኪያጁ  አክለውም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያቀረበው የእፅዋት ዘር የብቃት ማረጋገጫና ተያያዥ አገልግሎቶች የክፍያ ተመን በፌዴራል ፀድቆ በደቡብና በኦሮሚያ ክለሎችም እየተሰራበት ያለና ተግባሩም ተመሳሳይ መሆኑን አብረርተዋል፡፡

መስተዳድር ምክር ቤቱም በቀረበው ሃሳብ ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን በማንሳት በጉዳዩ ላይ በስፋት ተወያይቶ፣ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ በመስክ የዘር ጥራት ቁጥጥር፣ ላቦራቶሪ ፍተሻና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የአገልግሎት ክፍያ ማስፈፀም በመሆኑ ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የአገልግሎት ክፍያ ማስፈፀም እንዳለበት በመስማማት፣ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ጥያቄና በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በኩል ተደግፎ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ መሰረት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀድቆ በወጣው የዕፅዋት ዘር  የብቃት ማረጋገጫና የተያያዥ አገልግሎቶች የክፍያ ተመን ደንብ ላይ የተቀመጠው የአገልግሎት ክፍያ ተመን በክልሉም ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

ታህሳስ 25/2010 ዓ.ም

የዳያስፖራና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

 

ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት

 

የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ፈንድ ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ መውጣቱ ተገለጸ

የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ፈንድ ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ መውጣቱ ተገለጸ፡፡

የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት 5ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን ህዳር 15 ቀን 2010 ዓ.ም ባደረገው 10ኛ መደበኛ ስብሰባ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ፈንድ ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ መስጠቱን ገለጸ፡፡

የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሠፋ በላይ እንደገለጹት የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ፈንድ መቋቋም ያስፈለገበት በህብረተሠቡ ውስጥ ያለውን እርስ በርስ የመረዳዳት ባህል በማጎልበት በክልሉ ውስጥ ለሚከሰቱ ድንገተኛና አስቸኳይ የእርዳታ ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት አደጋውን ለመቀነስና የሠው ህይዎትም ሆነ ንብረት ከጥፋት ለመታደግ ለሚያግዝ በቂ የሆነ የመጠባበቂያ ሃብት ክምችት ለመያዝ የሚያስችል ክልል አቀፍ ስርዓት ለመዘርጋት ነው ብለዋል፡፡

በፈንዱ ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንቡ ላይ በየአንቀፁ የሠፈሩትን የፈንዱ ዓላማዎች፣ የገቢ ምንጮች፣ ስለ ፈንዱ አስተዳደር፣ አመራርና ተጠሪነት፣ ስለፈንዱ አጠቃቀም መመዘኛዎች፣ በፈንዱ ስለሚሠጥ ዕርዳታና ድጋፍ፣ ስለክልሉ አደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ኮሚቴ የአባልነት ጥንቅርና ተዋጽኦ እንዲሁም ሌሎች በደንቡ የተካተቱ ሃሳቦችን በዝርዝር በማቅረብ፣ ረቂቅ ደንቡ በክልሉ ፍትህ ቢሮና በርዕሰ መስተዳድሩ ዋና የህግ አማካሪ በተገቢው መንገድ ታይቶ የቀረበ  በመሆኑ መስተዳድር ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ መክሮ ረቂቅ ደንቡን እንዲያፀድቅላቸው ኃላፊው ጠይቀዋል፡፡

መስተዳድር ምክር ቤቱም ከቀረበው ማብራሪያ በማንሳት በጉዳዩ ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችንና በማነሳት ሠፊ ውይይት ካካሄደ በኋላ፡- በየጊዜው አደጋ ሲደርስ ሃብት የማሰባሰብ ስራ ከመስራት አደጋ ከመድረሱ በፊት አስቀድሞ ለመከላከል ታስቦበት ራሱን የቻለ ከመንግስት፣ ከለጋሽ ድርጅቶች፣ ከግለሰቦች ለአደጋ መከላከል የሚሆን ሃብት ማሰባሰብ የሚያስችል ፈንድ ሊቋቋም እንደሚገባ በማመን የቀረበው የአብክመ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ፈንድ ማቋቋሚያ ደንብ የመስተዳድር ም/ቤቱ ደንብ ሆኑ እንዲወጣ በሙሉ ድምፅ ተወስኗል፡፡

ታህሳስ 25/2010 ዓ.ም

የዳያስፖራና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

 

ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት

 

ከኦሮሚያና ከሶማሊያ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ ተሰጠ

ከኦሮሚያና ከሶማሊያ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ ተሰጠ

የአማራ ብሔራዊ  ክልላዊ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት 5ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን ጥቅምት 5 ቀን 2010 ዓ.ም ባደረገው 7ኛ መደበኛ ስብሰባ ከኦሮሚያና ሶማሌ ክልል በርዕስ በርስ ግጭት ለተፈናቀሉ ዜጎች መልሶ ለማቋቋም ይቻል ዘንድ ድጋፍ እንዲሰጥ መወሰኑን ገለጸ፡፡

መስተዳር ምክር ቤቱ በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች በወቅቱ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት በተፈናቀሉ ወገኖች ላይ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ እነዚህን ወገኖች ለማቋቋምና ለመደገፍ በሚደረገው እንቅስቃሴ የክልሉ መንግስት የችግሩን አስከፊነት በመረዳት 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ መደረጉን ገልጿል፡፡

 

መስተዳር ምክር ቤቱ ከችግሩ ስፋት አንጻር የድጋፍ መጠኑ እንደ ክልል የሚወሰን ቢሆንም በሀሳብ ደረጃ ከሌሎች ክልሎች ጋር ምክክር የተደረገ መሆኑንና ገንዘቡም በፌደራል ድጋፉን አማክሎ ለሚያሰባስበው አካል ገቢ የሚደረግ መሆኑን እና ከሁለቱም ክልሎች ለተፈናቀሉ ወገኖች ማቋቋሚያ የሚውል ብር 10 ሚሊዮን በፌደራል ደረጃ ድጋፉን ለሚያስተባብረው አካል ገቢ እንዲደረግ መስተዳድር ምክር ቤቱ ወስኗል፡፡

 

የጣና ሀይቅና አካባቢ ደህንነት ፈንድን ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ ደንብ

የጣና ሀይቅና አካባቢ ደህንነት ፈንድን ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ ደንብ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት 5ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን ጥቅምት 17 ቀን 2010 ዓ/ም ባካሄደው 8ኛ መደበኛ ስብሰባው የጣና ሀይቅና አካባቢ ደህንነት ፈንድ ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ ደንብ ማውጣቱን አስታወቀ፡፡

የአካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን በጣና ሀይቅ ላይ የተከሰተውንና ወደፊት ሊከሰት የሚችለውን መጤ አረም ለመከላከልና ለማጥፋት የሚውል ሀብት ስለሚያስፈልግ ይህንን ሀብት በአግባቡ ለመሰብሰብ የሚያስችል ህጋዊ ደንብ ማውጣት አስፈላጊ መሆኑን በመግለጽ በረቂቅ ደንቡ ላይ በየአንቀጹ የቀረቡትን ዝርዝር ጉዳዮች ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡

መስተዳድር ም/ቤቱም ከቀረበው ማብራሪያ በመነሳት የተለያዩ ሀሳቦችንና አስተያየቶችን በማንሳት ሰፊ ውይይት ካካሔደ በኋላ የጣና ሀይቅ ህልውና አደጋ ላይ መውደቅ ወደፊት መመለስ የማይቻል ጥፋት ሊያስከትል ስለሚችል ይህንን አስቀድሞ ለመንከባከብ መደገፍ የሚፈልጉ ሀይሎች ስላሉ የፈንዱ መቋቋም አስፈላጊ በመሆኑ ላይ በመስማማት፤

የአባይ ተፋሰስ ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ፣ የክልል ወጣቶች ማህበር ሊቀመንበር፣ የክልል ሴቶች ማህበር ሊቀመንበር፣ የክልሉ ንግድ ዘርፍ ማህበራት ፕሬዝዳንት እና በርዕሰ መስተዳድሩ የሚሰየሙ ከ3 ያልበለጡ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የስራ አመራር ቦርድ አባል ሆነው እንዲካተቱ፤

ለተፋሰሱ እንክብካቤ የገንዘብ አስተዋጽኦ ማድረግ ለሚፈልጉ ማናቸውም የህብረተሰብ ክፍሎችና ድርጅቶች ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ቋሚ የበጀት ቋት ማደራጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ከመንግስት፣ ከህብረተሰቡ፣ ከግል ሴክተሩ፣ ከምርምርና ትምህርት ተቋማት የተውጣጣ በበላይነት የጣናን ፈንድ የሚያስተዳድር ተጠያቂነት ያለው በቦርድ የሚመራ ፈንድ የተቋቋመ መሆኑን ለህብረተሰቡ በሚዲያ መግለጽ እንደሚገባ ምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡

የጣና ደህንነት ፈንድ ጽ/ቤት እስኪቋቋምና ስራ እስኪጀምር ድረስ አካባቢ ደንና ዱር እንስሳ ጥበቃ ባለስልጣን የሚያደራጁት አካውንት እንዲከፈት ማድረግ ሀብቱን የማፈላለግ እና የተሰበሰበውን ሀብት ስራ ላይ የማዋልና ሌሎችን ስራዎች በኃላፊነት ይዞ ከወዲሁ መስራት እንዳለበት በመስማማት የጣና ሀይቅና አካባቢ ደህንነት ፈንድ ደንብ ለክልሉ ም/ቤት ቀርቦ ከፀደቀበት ከጥቅምት 17 ቀን 2010 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ወስኗል፡፡

 

 

 

የአማራ እና የትግራይ ህዝቦች የጋራ ምክክር መድረክ መካሄዱ ተገለጸ

የአማራ እና የትግራይ ህዝቦች የጋራ ምክክር መድረክ መካሄዱ ተገለጸ፡፡

"አብሮነታችን ለሰላማችን፤ ሰላማችን ለአብሮነታችን" በሚል መሪ ቃል የአማራ እና የትግራይ ህዝቦች የጋራ ምክክር መድረክ በጎንደር ከተማ ከህዳር 9-10/2010 ዓ.ም ጀምሮ መካሄዱን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገለፁ፡፡

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በመክፈቻ ንግግራቸው እንደተናገሩት የአማራና የትግራይ ህዝቦች ከጥንት እስከ ዛሬ በአጥንትና በደማቸው የገነቡት ኢትዩጵያዊነት ድር እና ማግ ሆኖ በአንድነት ተሳስረው ከመኖራቸው በላይ በእምነት፣ በባህልና ኗኗራቸው ብዙ የጋራ ታሪክ የገነቡ ህዝቦች ናቸው ብለዋል።

የትግራይ እና የአማራ ህዝቦች የሚያኮራ የግንኙነት ታሪክ ስናወሳ የጥንቱን ብቻ አይደለም በቅርብ ጊዜ በተካሄደው የሰላምና የዲሞክራሲ የትግል ሂደትም እነዚህ በጋራ ለህዝቦች ነፃነትና እኩልነት በአንድ ላይ ቁመው አኩሪ መስዋዕትነት ከፍለው ጨቋኙን መንግስት ገርስሠው ከመላው ኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ጋር በአንድነት አዲስ ስርዓት መስርተዋል፡፡ የእነዚህ ህዝቦች ማንነት ሲጀመርም በብዙ መልኩ የተቆራኘ ነው ፡፡ የአማራና ትግራይ ህዝቦች በመልካም ጉርብትና ለዘመናት አብረው ከመኖራቸው ባሻገር በእምነት፤ በባህል፤ በአኗኗራቸውና በአይነት ብዙ የጋራ እሴቶቻቸው ተሳስረው የጋራ ታሪክ የገነቡ ህዝቦች ናቸው በማለት ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪ ርዕሰ መስተዳድሩ እንደተናገሩት የአማራ ህዝብ ስራ ወዳድ፣ በላቡ የሚኖር፣ ሀይማኖቱን ጠባቂ፣ እንግዳ ተቀባይ፣ ነፃነቱን አፍቃሪ እና በኢትዪጵያዊነቱ የማይደራደር ህዝብ ነው። በቀጣይም ይህን እሴቱን ጠብቆ በመሄድ ከሌሎች ህዝቦች ጋር የጋራ ቤታችን ኢትዩጵያ ሰላም ፣ዴሞክራሲና ፍት የተረጋገጠባት ሀገር እንድትሆን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን አጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።


የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አባይ ወልዱ በበኩላቸው እንደተናገሩት የአማራ እና የትግራይ ህዝቦች ከጥንት ጀምረው ለኢትዩጵያ ነፃነት በጋራ እየተፋለሙ ገናና ታሪክ ማስቀጠል የቻሉ ህዝቦች ናቸው። ይህን ታሪካዊ ትስስራቸውን ለማስቀጠል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ ከመቸውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በሌላ በኩል ክቡር አቶ በረከት ስምኦን  በህዝብ ለህዝብ መድረኩ "በእኩልነት ላይ የተመሰረተ ፌደራላዊ ስርዓታችን ለሀገራችን ልማት፣ ሰላም እና ዴሞክራሲ ግንባታ አስፈላጊ ነው።" በሚል ባቀረቡት የመወያያ ፅሁፍ ላይ አልፎ አልፎ በሀገራችን የተከሰቱ ግጭቶች ዋነኛ መንስኤ እድገቱን ሊሸከም የሚችል ብቃት ያለው አመራር እጦት እንጂ የፌደራሊዝም ስርዓቱ የፈጠረው ችግር እንዳልሆነ ገልፀዋል።

 

በመጨረሻም በተካሄደው የህዝብ ለህዝብ መድረክ የሁለቱም ክልል ተሳታፊዎች ጥያቄዎችን በማንሳት፣ አስተያየት በመስጠት፤ የጎንደር ከተማ አስተዳደር እና ክፍለ ከተሞች በትግራይ ክልል ለሚገኙ ከተሞች የተለያዩ የማስታወሻ ሽልማቶችን በማበርከት፣ እንዲሁም ባለ 8 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

 


Page 5 of 17
Content View Hits : 9427859

Comments

  • It's a shame yyou dоn't have a donate button! I'd ...
  • Ꮤow that ѡas unusual. I just wrߋte an very long co...
  • I do truѕt all the ideas you've introduced on your...
  • Ꮤow that ѡas unusual. I just wrߋte an very long co...
  • Ꮤow that ѡas unusual. I just wrߋte an very long co...

Latest News

Who is online

We have 135 guests and 15 members online

Entertainment