የክልል አመራሮች ከቻግኒ ከተማ ነዋሪዎች ጋር በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር ዙሪያ ምክክር አካሄዱ፤

አመራሮቹ የአሻጋሪ ልማት የዘላቂ ዕገት ዕቅዱ አተገባበር በቻግኒ ያለበትን ደረጃ በመስክ የተመለከቱ ሲሆን ፤ በዛሬው ዕለትም ከነዋሪው ጋር ምክክር አካሄደዋል።

‎በምክክር መድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ይበልጣል ሰይድ፦ ክልላችን ከቅርብ አመታት ወዲህ የፀጥታ ችግር ገጥሞት የቆዬ ሲሆን አመራራችን ከህዝቡና ከፀጥታ ሀይሉ ጋር ተቀናጅቶ በመስራቱ አንድም ቀን የማህበራዊ አገልግሎቶች ፤ የመንግስት ተቋማት ፤የንግድ እንቅስቃሴው ሌሎች ድርጅቶች ተቋማት ሳይዘጉ አገልግሎት ሲሰጡ ቆይቷል በማለት ተናግረዋል።

‎ክልላችን በፀጥታ ችግር ውስጥም ሆኖ የአሻጋሪ ልማት ዘላቂ ዕድገት ዕቅድ አቅዶ ወደ ስራ ገብቷል ፤ ከተማ አስተዳደራችንም ይህንኑ ዕቅድ በመተግበር ላይ ይገኛል በማለት ተቀዳሚ ከንቲባው አያይዘው ተናግረዋል።

‎የርዕሰ መስተዳድሩ አማካሪ የሆኑት አቶ አስናቀ ይርጉ በበኩላቸው፦ የቻግኒ ከተማ ህዝብና መንግስት ተቀናጅቶ ሰላሙን ማስጠበቁ እና በህብረተሰብ ተሳትፎ ብሎም በመንግስት ሀቅም የተከናወኑ ልማቶችን አይተናልና በርቱልን አሁን ላይ ያሉትን የከተማችሁን ሰላም ፣ ልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባር አጠናክራችሁ እንድታስቀጥሉ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ አማካሪ የሆኑት ዶ/ር መስፍን አበጀ እንደተናገሩት ብልፅግና ፓርቲ ቃል የሚገባ ሳይሆን አቅዶ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ፕሮጀክቶችን የሚጨርስ ፓርቲ መሆኑን ገልጸው የተጀመሩ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ጨርሶ አሳይቷል።

በቅርብ የተጀማመሩትም በተቀመጣላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ፓርቲያችን ስራ ላይ ነው። ህዝብ ከመንግስትና ፓርቲያችን ጎን ሊቆም ይገባልም ብለዋል።

ዶ/ር መስፍን አበጀ አያይዘውም አሻጋሪ ዕቅዱ የህዝብን ጥያቄና የክልሉን የመልማት ፍላጎት መልስ የሚሰጥ ይሆናል በማለትም ተናግረዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top