የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አረጋ ከበደ “በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እምርታ” በሚል መሪ መልዕክት ለክልሉ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ሥልጠና ላይ በሰጡት ማጠቃለያ የግብርና እና ገጠር ትራንስፎርሜሽን በተመለከተ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦

ሕልማችን ሊያሳክ የሚያስችል ጸጋ አለን፣ መሬት፣ አየር፣ የማዕድን ሃብት፣ ትኩስ ጉልበት ያለው ወጣት እና ሌሎች ሃብቶች አሉን፤ ሌሎች ሀገራት የማያገኙት ዕድልም አለን።

👉ከተለመደው አሠራር መውጣት እና ፈጠራን በመጠቀም እያንዳንዱን ሥራዎች ውጤታማ ለማድረግ መሥራት ይጠበቃል።

👉ኋላቀር የኾነ የማረሻ ዘዴን እና የአሥተራስ መንገድን በቴክኖሎጂ በመቀየር ግብርናውን ከዕለት ጉርስ የተሻገረ እንዲኾን ማድረግ ያስፈልጋል።

👉የግብርና ትራስፎርሜሽን ለማምጣት ባሕላዊ አሠራሮችን እንቀንስ፣ ዘመናዊ አሠራሮችን እንጨምር ነው።

👉መሪዎች ለውጥ የሚያመጣ፣ እሴት የሚጨምር ሥራ መሥራት የግብርና ምርት እና ምርታማነትን ሊያሳድጉ የሚችሉ ሥራዎችን መሥራት ይጠበቅባቸዋል።

👉በግብርናው ዘርፍ ለውጥ ሲመጣ የገጠር ትራንስፎርሜሽን ማምጣት ይቻላል፤ የገጠር ትራንስፎርሜሽን ለማምጣት ቀዳሚው ጉዳይ ዘመናዊ ግብርናን መፍጠር አስፈላጊ ነው።

👉ከፍጆታ አልፎ ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚኾን እና ለውጭ ገበያ የሚያቀርቡ አርሶ አደሮችን መፍጠር ይኖርበታል።

👉ከችግር ለመውጣት የሚቆጭ፣ ችግርን የሚሻገር እና ያለን ጸጋ የሚጠቀም መሪ ያስፈልጋል።

👉ራዕይ ያለን፣ ግብ ያስቀመጥን ነን፤ የምንፈታው ችግር፤ የምናሳካው ውጤት አለን፤ ብዙ ጸጋዎች አሉን፣ በቁርጠኝነት ከሠራን እናሳካዋለን።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top