የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት

መፍጠር፣ መፍጠን እና በጥራት መሥራት የሁልጊዜም የስራ መመሪያችን ሊሆን ይገባል፡፡

በሰሜን ሸዋ ዞን በደብረ ብርሃን ከተማ በነበረን ቆይታ የመኪና መገጣጠሚያ እንዲሁም የብርጭቆና የጠርሙስ ማምረቻዎችን ተመልክተናል።

በቆይታችን ያየናቸው ፋብሪካዎች የሀገር ውስጥ ግብዓትን በመጠቀምና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬን እያዳኑ ነው፡፡

ከብየዳ ጀምሮ ትላልቅ የኤሌትሪክ አውቶቡሶችን እየገጣጠመ የሚገኘው የፊቤላ ኢንዱስትሪያል መኪና መገጠሚያ በቀን 12 መኪና ማምረት በሚያስችል አቅም አለው፡፡ መገጣጠሚያው በቅርቡ ያስጀመረው አዲስ የቀለም መቀቢያ በርካታ ቀናትን ይወስዱ የነበሩ ስራዎችን በሰዓታት ለማከናወን አስችሏል፡፡

በአንድ ቀን 450 ሺህ ጠርሙስ የሚያመርተው ዴዴ ቦትል የብርጭቆና የጠርሙስ ማምረቻ ደግሞ 86 በመቶ የሚሆነውን ግብዓት ከሀገር ውስጥ ተጠቅሞ ለበርካታ የመጠጥ እና የመድሃኒት ፋብሪካዎች ጥቅም የሚሰጡ ጠርሙሶች ያመርታል፡፡

በኢንዱስትሪዎቹ የተመለከትናቸው አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴዎች በየዘርፉ በጥራትና በፍጥነት በመትጋት የምናልመውን እድገት በአጠረ ጊዜ እንደምናሳካ የሚያሳዩ ናቸው፡፡የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top